Q / q በላቲን አልፋቤት አሥራ ሰባተኛው ፊደል ነው።
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
ግብፅኛ ወጅ | ቅድመ ሴማዊ ቆፍ | የፊንቄ ጽሕፈት ቆፍ | የግሪክ ጽሕፈት ቆፓ | ኤትሩስካዊ Q | ላቲን Q | ||
---|---|---|---|---|---|---|---|
|
የ«Q» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ቆፍ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የአመልማሎ (የሸማኔ ዕቃ) ስዕል መሰለ። ለዚህ ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ። በነዚህ ልሳናት የ/ቅ/ ድምጽ ለማመልከት ጠቀመ። ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "ቆፓ" Ϙϙ) ደረሰ፤ በግሪክኛ ግን የ/ቅ/ ድምጽ ባለመኖሩ በK ፈንታ «ኮ» እና «ኩ» ለመጻፍ በϘ ሆነ። እንዲሁም ፊደሉ በጥንታዊ ኢታሊክ አልፋቤትና በላቲን አልፋቤት ገባ፤ በኋላ ግን የϘ ጥቅም ከግሪክኛ ጽሕፈት ከቁጥሩ «ዘጠና» (90) በቀር ይጠፋ ነበር።
በሮማይስጥም በጊዜ ላይ የ«Q>> ጥቅም ከ«O» በፊት ጠፍቶ ከ«U>> በፊት ብቻ ይታይ ነበር። እስካሁንም ድረስ በአብዛኛው የምዕራብ አውሮፓ ላሳናት እንዲህ ነው። በጣልኛ፣ ፈረንሳይኛ እና እስፓንኛ ይህ «qu» /ክ/ ለመጻፍ በተለይም በ /ኬ/፣ /ኪ/ (que, qui) ይታያል። በእንግሊዝኛ የ «qu» ድምጽ እንደ /ኲ/ ያሰማል፤ በጀርመንኛም እንደ /ኲ/ ወይም /ክቭ/ ያሰማል።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ቀ» («ቆፍ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ቆፍ» ስለ መጣ፣ የላቲን 'Q' ዘመድ ሊባል ይችላል። የ፺ (90) ምልክት ደግሞ ከዘመናዊው ግሪኩ ቆፓ (90) በተቀየረው መልክ (Ϟ ϟ) ደረሰ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article Q, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.