የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህም መሣሪያዎች የጅማት፣ የትንፋሽና የምት ተብለው ወደ ሶስት ይከፈላሉ።

የክር ሙዚቃ መሣሪያዎች

እነዚህ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በንዝረት ነው።

  • በገና፡ መንፈሳዊ ዜማዎችን ለማዜም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ክራር፡ ይህ የጅማት የሙዚቃ መሣሪያ ለአያሌ ዓመታት ለደስታ፣ ለትካዜ፣ ለፍቅርና ለቀረርቶ ስንጠቀምበት የቆየ መሣሪያ ነው።
  • መሰንቆ (ማሲንቆ)፡ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኝ ጥንታዊ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ዲታ፡ በሲዳሞ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው።
  • ዱል፡ በጋምቤላ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው።

የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያዎች

እነዚህ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በትንፋሽ ኃይል ነው።

  • ዋሽንት፡ አብዛኛውን ጊዜ እረኞች በሀገር ቤት ይገለገሉበታል። በተጨማሪም በመድረክ ላይ ለክራርና ለመሰንቆ ቅኝት በመስጠትና ዜማን በማጀብ ያገለግላል።
  • አምቢልታ፡ ሶስት ዓይነት አመቢልታዎች አሉ። ስማቸውም ኡፍን፣ አውራ እና የማ ነው። በኢትዮጵያ ለክብረ በዓልና ወደ ጦር ሜዳ ለሚሄድ ሰልፈኛ የሚነፋ አድማቂ መሣሪያ ነው።
  • መለከት፡ ቀደም ባለው ጊዜ ሰዎች ተሰብስበው የመንግሥት አዋጅ እንዲሰሙ ትዕዛዝን መስጫ መሣሪያ ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ነው።
  • ድንኬ፡ በሲዳሞ ክፍለ ሀገር በወላይታ አካባቢ ለአስከሬን ማጀቢያነት የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ፖረሬሳ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ለዘፈን ማጀቢያ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ሁራ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር ያሉ ጎሳዎች የሚጠቀሙበት የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ሁልዱዱዋ፡ በሲዳሞ ክፍለ ሀገር የቀብር ሥነ ሥርዓት ለመግለጽ የሚነፋ መሣሪያ ነው።
  • ጨቻ ዝዬ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ውዝዋዜ ለማድመቅ የሚያገለግል የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ዛክ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ሸመቶ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ፋንፋ፡ በከፋ ክፍለ ሀገርና በጋሞጎፋ /ኮንሶ/ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • አዋዛ፡ በወለጋ ክፍለ ሀገር በአሶሳ አካባቢ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።

የምት ሙዚቃ መሣሪያዎች

  • ከበሮ፡ ለዘፈን ማድመቂያና ለሠርግ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ዝማሬ ቀሳውስት በሽብሸባ ጊዜ የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
  • አታሞ፡ ለሙዚቃና ለጭፈራ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ነጋሪት፡ በሰልፍ ጊዜ የሚጎሰም የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • መቋሚያ፡ ለመንፈሳዊ ዝማሬ ከከበሮው ስልት ጋር በተዛመደ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ቀሳውስት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
  • ፀናፅል፡ ለመንፈሳዊ ዝማሬ ቀሳውስት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
  • ቅል፡ ቅል በውስጡ ጠጠሮች ወይም ፍሬዎች ተጨምረውበት ለዘፈን ማድመቂያ ያገለግላል።
  • ቻንቻ፡ በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በጭፈራ ጊዜ በወገብ ላይ የሚታሰር አዳማቂ መሣሪያ ነው።
  • ካመባ፡ ከሸክላ የተሠራ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ መሣሪያ ነው።
  • ቃጭል፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመንፈሳዊ ዜማ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ቶሞ፡ በጋምቤላ ብሔረሰብ ውስጥ እውቅና ተወዳጅ የሆነ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። በተጨማሪም በኬንያኡጋንዳታንዛኒያናይጄሪያሱዳንና ዛየርም በዚህ መሣሪያ እንደሚጠቀሙ ታውቋል።
  • ጋሬ፡ በጋምቤላ ብሔረሰብ ውስጥ በእግር ላይ ታስሮ ጭፈራን የሚያደምቅ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • የግመል ቃጭል፡ ይህ መሣሪያ በተለይ ከእንጨት የሚሠራ ሆኖ ሙዚቃን ለማጀብ የሚጠቅም መሣሪያ ነው።

ተዛማጅ መጣጥፎች

ማጣቀሻ

Tags:

የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች የክር ሙዚቃ መሣሪያዎችየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያዎችየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች የምት ሙዚቃ መሣሪያዎችየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች ተዛማጅ መጣጥፎችየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች ማጣቀሻየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችኢትዮጵያ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

አል-ጋዛሊቢራደብረ ሊባኖስአቡነ ሰላማንግድፋሲለደስአፍሪቃሻሜታአንኮበርቅዱስ ገብርኤልሸዋሶማሊያደርግአፋር (ብሔር)ቤተክርስቲያንጅቡቲ (ከተማ)ጉመላዓረፍተ-ነገርፍቅር እስከ መቃብርየቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎችገድሎ ማንሣትሚካኤልየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማሉልመሬትአዶልፍ ሂትለርገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽአውሮፓጊዜዝሆንሥርዓትኃይሌ ገብረ ሥላሴየኢትዮጵያ አየር መንገድፔትሮሊየምእሳትግራኝ አህመድቻይናጉልባንቦብ ማርሊየኢትዮጵያ ካርታ 1936ጣልያንጨዋታዎችየማርቆስ ወንጌልጤፍወተትፊታውራሪልብነ ድንግልኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያንመጋቢትስነ አምክንዮሣራአዋሽ ወንዝ2004 እ.ኤ.አ.ያህዌቅዱስ ራጉኤልየኢትዮጵያ ሙዚቃጣና ሐይቅስዕልየፀሐይ ግርዶሽዓመት በዓላት እና ታሪካዊ ማስታወሻዎችእግዚአብሔርኤችአይቪድንቅ ነሽጓያቼኪንግ አካውንትወለተ ጴጥሮስአንሻንቀነኒሳ በቀለአማርኛ ልብ ወለድ መፃህፍትሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚትአገውጉግልቴወድሮስ ታደሰ🡆 More