ጊዜ

ጊዜ ኩነቶችን (ክስተቶችን) ለመደርደር፣ ቆይታቸውን ለማነጻጻር፣ በመካከላቸውም ያለፈውን ቆይታ ለመወሰን በተረፈም የነገሮችን እንቅስቃሴ መጠን ለመለካት የሚያገለግል ነገር ነው። ጊዜ በፍልስፍና፣ ሃይማኖት፣ ሳይንስ ውስጥ ብዙ ጥናት የተካሄደበት ጽንሰ ሃሳብ ቢሆንም ቅሉ እስካሁን ድረስ በሁሉ ቦታ ለሁሉ የሚሰራ ትርጓሜ አልተገኘለትም።

ጊዜ
የዓለማችን የጊዜ ቀጠናወች (ሰዓት ክልል)

የጊዜ መተግበሪያ ትርጉም ለዕለት ተለት ኑሮ ጠቃሚነቱ ስለታመነበት ከዘመናት በፊት ጀምሮ እስካሁን ይሰራበታል። ይህ መተግበሪያ ትርጉም ለምሳሌ ሰከንድን በመተርጎም ይጀምራል። ማለት በቋሚ ድግግሞሽ የሚፈጠሩ ኩነቶችን/ክስተቶችን በማስተዋል የተወሰነ ድግግማቸውን አንድ ሰከንድ ነው ብሎ በማወጅ የመተግበሪያ ትርጉሙ (ለስራ የሚያመች ትርጉሙ) ይነሳል። ለምሳሌ የልብ ተደጋጋሚ ምት፣ የፔንዱለም ውዝዋዜ ወይም ደግሞ የቀኑ መሽቶ-ነግቶ-መምሸት ወዘተ.. እነዚህ ኩነቶች እራሳቸውን በቋሚነት ስለሚደጋግሙ ከነሱ በመነሳት ሰዓትንና ደቂቃን ማወጅ ይቻላል (መሽቶ ሲነጋ 24 ሰዓት ነው፣ ልብ ሲመታ ወይም ፔንዱለም አንድ ጊዜ ሄዶ ሲመለስ አንድ ሰኮንድ ነው፣ ወዘተ..) ። የመተግበሪያ ትርጉሙ ተግባራዊ ጥቅም ይኑረው እንጂ «ጊዜ በራሱ ምንድን ነው?» ፣ ወይም ደግሞ «ጊዜ አለ ወይ?» ወይም ደግሞ «ጊዜ የሚባል ነገር በራሱ አለ ወይ?» ለሚሉት ጥያቄወች መልስ አይሰጥም።

በአሁኑ ወቅት ጊዜ በሁለት አይነት መንገድ ይታያል፦

    1. አንደኛው አስተሳሰብ ጊዜ ማለት የውኑ አለም መሰረታዊ ክፍል ሲሆን፣ ማንኛውም ኩነት (event) የሚፈጠርበት ቅጥ ነው። እንግሊዛዊው ሳይንቲስት ኢሳቅ ኒውተን ይህን አስተያየት ስለደገፈ ኒውተናዊ ጊዜ ተብሎ ይታወቃል ጊዜ እንግዲህ ባዶ አቃፊ ነገር ሲሆን ኩነቶች በዚህ ባዶ አቃፊ ነገር ውስጥ ይደረደራሉ ማለት ነው። መስተዋል ያለበት ይህ ጊዜ የተባለው አቃፊ ነገር ኩነቶች ኖሩ አልኖሩ ምንግዜም ህልው ነው።
    2. ከላይ የተጠቀሰውን የጊዜ ጽንሰ ሃሳብ የሚቃወም አስተያየት ሁለተኛው አስተያየት ሲሆን ማንኛውንም አይነት «አቃፊ» የተባለ የጊዜ ትርጉምን ይክዳል፣ እንዲሁም ቁስ አካሎች በዚህ «ጊዜ» በሚባል አቃፊ ነገር ውስጥ መንቀሳቀሳቸውን ይክዳል፣ የጊዜ ፍሰት አለ የሚለውን አስተሳሰብንም ያወጋዛል። ይልቁኑ በዚ በሁለተኛው አስተያየት ጊዜ ማለት አእምሮአችን የውኑን አለም ለመረዳት ከፈጠራቸው ህንጻወች (ቁጥርንና ኅዋን ጨምሮ) አንዱ ሲሆን ሰወች ኩኔቶችን ለመደረደር እና ለማነጻጸር የሚረዳቸው ምናባዊ መዋቅር ነው ይላል። ይህን ሃሳብ ካንጸባረቁት ውስጥ ሌብኒትዝካንት, ይገኙበታል። ካንት እንዳስተዋለ፦ ጊዜ ማለት ኩኔትም ሆነ ነገር አይደለም ስለዚህም ጊዜን መለካትም ሆነ በጊዜ ውስጥ መጓዝ አይቻልም ።

ሳይንቲስቶችና ቴክኖሎጂስቶች ጊዜን በሰዓት ለመለካት ብዙ ጥረት አድርገዋል። ይህ ጥረት ለከዋክብት ጥናትና ለተለያዩ ያለም ዙሪያ ጉዞወች እንደመነሳሻ ረድቷል። በቋሚ መንገድ እራሳቸውን የሚደጋግሙ ክስተቶች/ኩነቶች ከጥንት ጀምሮ ጊዜን ለመልካት አገልግለዋል። ለምሳሌ ጸሃይ በሰማይ ላይ የምታደርገው ጉዞ (ቀን)፣ የጨረቃ ቅርጾች(ወር)፣ የወቅቶች መፈራረቅ(ዓመት)፣ የፔንዱለም መወዛወዝ (ሰኮንድ) ወዘተ...ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ ሰኮንድ የምትለካው የሴሲየም አረር ሲወራጭ በሚያሳየው ቋሚ ድግግሞሽ ነው።

ሬይ ከሚንግ የተባለው ልብ ወለድ ጸሃፊ በ1920 ስለ ጊዜ ሲጽፍ " ሁሉ ነገር በአንድ ጊዜ እንዳይፈጸም የሚያደርገው ነገር....ጊዜ ነው " በማለት እስካሁን ድረስ ታዋቂ የሆነችውን ጥቅስ መዝግቦ አልፏል, ይቺ አባባል በብዙ ሳይንቲስቶችም ስትስተጋባ ተሰምታለች፣ ለምሳሌ በኦቨርቤክ, እና ጆን ዊለር.

የጊዜአዊ ጊዜ አለካክ

ጊዜአዊ ጊዜ አለካክ ሁለት መልኮች አሉት እነሱም፡ ካሌንደር ና ሰዓት ናቸው። ካሌንደር የሂሳብ ንጥር ሲሆን ሰፋ ያለ ጊዜን ለመለካት የሚጠቅመን ነው። ሰዓት ደግሞ በተጨባጭ ቁሶች ተጠቅመን የጊዜን ሂደት የምንልካበት ነው። በቀን ተቀን ኑሯችን ከአንድ ቀን ያነሰን ጊዜ ለመለካት ሰዓት ስንጠቀም ከዚያ በላይ የሆነውን ደግሞ በካሌንደር እንለካለን።

ጊዜ 
አቶሚክ ሰዓት

ጊዜ በፍልስፍና

ኦግስጢን የተባለው የካቶሊክ ፈላስፋ "ጊዜ ምንድን ነው?" በማለት እራሱን መጠየቁን በመጽሃፉ አስፍሯል። ሲመልስም "ሌላ ማንም ካልጠየቀኝ መልሱን አውቀዋለሁ፣ ነገር ግን ለሌላ ሰው ለመግለጽ ብሞክር ምን እንደሆነ ይጠፋብኛል]] በማለት ካስረዳ በኋላ ጊዜ ምን እንደሆነ ከማወቅ ይልቅ ምን እንዳልሆነ ማወቁ እንደሚቀል አስፋፍቶ መዝግቧል።

የጥንቶቹ ግሪክ ፈላስፎች ጊዜ ማለቂያ የለለው፣ ወደሁዋላም ሆነ ወደፊት የትየለሌ ነው ብለው ሲያስቀምጡ፣ የመካከለኛው ዘመን አውሮጳውያን ደግሞ ጊዜ መነሻም ሆነ መድረሻ ያለው አላቂ ነገር ነው በማለት አስረግጠው አልፈዋል። ኒውተን በበኩሉ በሁሉ ቦት አንድ አይሆነ ቋሚ ጊዜ እንዳለና መሬት ላይ ያለው ጊዜ ከዋክብት ላይ ካለው ጊዜ ጋር እኩል የሚጎርፍ ነው በማለት አስረድቷል። በአንጻሩ ሌብኒትዝ ጊዜ ማለት አንድ አይነትና ቋሚ ሳይሆን አንጻራዊ እንደሆነ አስቀምጧል። ካንት ባንጻሩ ጊዜን ሲተንትን "ጊዜ ማለት ከልምድ ውጭ ገና ስንወለድ አብሮን የሚወለድ ቀደምት እውቀት ሲሆን የገሃዱን አለም እንድንረዳ የሚረዳን አዕምሮአችን የሚያፈልቀው መዋቀር" ነው ብሎታል።. በርግሰን የተባለው ፈላስፋ ደግሞ ጊዜ ማለት ቁስ አካልም ሆነ የአእምሮአችን ፈጠራ አይደለም በማለት ሁለቱንም ክዷል። ይልቁኑ ጊዜ ማለት ቆይታ ማለት ሲሆን፣ ቆይታ በራሱ ደግሞ የውኑ አለም አስፈላጊ ክፍል ሲሆን ከ ፈጠራና ትዝታ ይመነጫል ብሏል።

ኢ-ውናዊ ጊዜ

ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው ግሪካዊ ፈላስፋ አንቲፎን እንደጻፈው "ጊዜ እውን ሳይሆን በርግጥም ጽንሰ ሃሳብ ወይም ልኬት" ነው ብሎታል። ፓራመንዴስ የተባለው ግሪካዊም ጊዜ፣ እንቅስቃሴና፣ ለውጥ በሙሉ የውሽት ራዕይ እንጂ በርግጥ በግሃዱ አለም ያሉ አይደሉም ብሏል። በቡዲሂስቶችም ዘንድ ጊዜ የውሸት ራዕይ ነው የሚለው አስተሳሰብ እስካሁን ይሰራበታል። ,

በተፈጥሮ ህግጋት አጥኝወች ዘንድ ግን ጊዜ እውን እንደሆነ ይታመናል። በርግጥ አንድ አንድ የፊዚክስ አጥኝወች ኳንትም ሜካኒክስ በይበልጥ እንዲሰራ እኩልዮሹ ያለጊዜ መቀመጥ አለባቸው ይላሉ። ይህ ግን ያብዛናው ሳይንቲስቶች አስተያየት አይደለም።.

ሳይንሳዊ ትርጉም

የቆየው የሳይንስ ትርጓሜው

አልበርት አንስታይን የጊዜን ትርጉም እስከለወጠበት ዘመን ድረስ የጊዜ ትርጓሜ ኢሳቅ ኒውተን ባስቀመጠው መልኩ ይሰራበት ነበር። ይህም ኒውተናዊ ሲባል ጊዜ ሁሉ ቦታ ቋሚ የሆነ፣ ምንጊዜም የማይቀየርና በሁሉ ቦታና ዘመን እኩል የሚፈስ (ለምሳሌ በከዋክብትና በመሬት ያለው ጊዜ በአንድ አይነት መንገድ ይሚፈስ/የሚለወጥ) ነው የሚል ነው።. በክላሲካል ሳይንስ የሚሰራበት ጊዜ ኒውተናዊ ነው።

ዘመናዊ ትርጓሜው

በ19ኛው ክፍለዘመን፣ የተፈጥሮ ህግን የሚያጠኑ ሰወች በነኒውተን ይሰራበት የነበረው የጊዜ ትርጓሜ የኮረንቲንና ማግኔት ን ጸባይ ለማጥናት እንደማይመች/እንደማይሰራ ተገነዘቡ። አንስታይን ሳይንቲስቶቹ የገቡበትን ችግር በማስተዋል በ1905 መፍትሄ አቀረበ። ይህም መፍትሄ የብርሃን ፍጥነትን ቋሚነት የተንተራሰ ነበር። አንስታይን እንደበየነው (postulation) በጠፈር ውስጥ የብርሃን ፍጥነት ባማናቸውም ተመልካቾች (ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ) ዘንድ አንድ ነው፣ በዚህ ምክንያት በተንቀሳቃሽ ሳጥን ውስጥ የሚፈጠጥ ኩነት የሚወስደው የጊዜ ቆይታ ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካችና ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካች አንድ አይደለም ብሏል። ለምሳሌ እሚንቀሳቀሰው ሳጥን ውስጥ ለ5 ደቂቃ ያክል ቦምብ ቢፈነዳ (ኩነት) ፣ የማይንቀሳቀሰው ከውጭ ያለ ተመልካች ቦምቡ ለ5.5 ደቂቃ እንደፈነዳ ሊያስተውል ይችላል። ሌላ ታዋቂ ምሳሌ ብንወስድ፣ ሁለት መንትያ እህትማማቾች ቢኖሩና አንዱዋ በመንኮራኩር ከመሬት ተነስጣ በብርሃን ፍጥነት በሚጠጋ ፍጥነት ጠፈርን አሥሳ ከስልሳ አመት በኋላ ብትመለስ፣ መንትያዋን አርጅታ ስታገኛት፣ ተመላሿ ግን ገና ወጣት ናት። የዚህ ምክንያቱ፣ አንስታይ እንዳስረዳ፣ የተንቀሳቃሽ ነገሮች ሰዓት ዝግ ብሎ ሲሄድ የማይንቀሳቀሱ ግን ቶሎ ስለሚሄድ ነው።

ባጠቃላይ፣ የሚንቀሳቀሱ ተመልካቾች ከማይንቀሳቀሱ ተመልካቾች ጋር የተለያየ ጊዜ ለአንድ አይነት ኩነት ይለካሉ።

ጊዜ 
ይህ ስዕል ሁለት ቅጥ ያለው ኅዋ ሦስት ቅጥ ባለው መቼት ተጣምሮ ያሳየናል። ኃላፊውና መጪው የብርሃን ኮን ቋሚ ሲሆኑ፣ የአሁኑ ጊዜ ግን አንጻራዊና ለተለያዩ ተመልካቾች የተለያየ ነው

መቼት

መቼት የሚለው ቃል ከ"መቼ" እና "የት" ቃላቶች የመጣ ሲሆን የጊዜና ኅዋን ጥምረት ያሳያል። ከድሮ ጀመሮ፣ ሰወቸ ጊዜንና ህዋን በማዛመድ ተመልከተዋቸዋል። በተለክ ከ አንስታይን የልዩ አንጻራዊነት እና አጠቃላይ አንጻራዊነት ርዕዮተ አለሞች ወዲህ የጊዜና ኅዋ ጥምረት (መቼት) ለሳይንስ እንደመሰረታዊ ነገር ያገለግላል። በርዕዮቶቹ መሰረት፣ መቼት፣ በእንቅስቃሴ ምክንያት ከአንድ ተመልካች ወደሌላ ተመልካች የሚለያይ እንጂ በአንድ ዋጋ ለሁሉ ተመልካች አይጸናም። በርዕዮቶቹ መሰረት፣ ያለፈው ጊዜ የሚባለው ብርሃን ለአንድ ተመልካች መላክ የሚችሉ ኩነቶች (ክስተቶች) ስብስብ ሲሆን ፣ መጪው ጊዜ ደግሞ አንድ ተመልካች ብርሃን ሊልክባቸው ይሚችላቸው ኩነቶች ስብስብ ነው።

የጊዜ መስፋትና መጥበብ

ጊዜ 
የባንዴነት አንጻራዊነት: ክስተት B ክስተት ና A በአረንጓዴው ማጣቀሻ ውስጥ ተሁነው ሲታዩ ባንዴ ወይም አንድ ላይ የተከናወኑ ይመስላሉ, ነገር ግን በ ሰማያዊው ማጣቀሻ ውስጥ ለሚመልከት፣ ክስተት B ከክስተት A በፊት እንደተከናወነ ይመሰክራል፣ በቀዩ ማጣቀሻ ያለ ምስክር ደግሞ ክስተት B ከክስተት A በኋላ እንደተከናወነ ይመለከታል

አንስታይን በምናባዊ ሙከራው እንዳሳየ፣ በተለያየ ፍጥነት የሚጓዙ ሰወች በሚያዩዋቸው ኩነቶች (ክስተቶች) መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት በሁሉም ተመልካቾች አንድ አይነት ሳይሆን የተለያየ ነው። ማልተ ሁለት ቦምቦች ቢፈነዱና አንዱ ተመልካች 5 ሰከንድ በሁለት ቦምቦች ፍንዳታ መካከል ቢለካ፣ ሌላኛው ደግሞ 6 ሰኮንድ ሊለካ ይችላል (እንደ ፍጥነቱ ይወሰናል)። በተረፈ የቦምቦቹ ፍንዳታ በአማካኝነት (causality) ካልተያያዙ (ማለት ያንዱ ቦምብ ፍንዳታ ለሌላው ቦምብ መፈንዳት ምክንያት ካልሆነ/መንስዔ ካልሆነ)፣ የኩነቶቹ ድርድር ሁሉ ሊለወጥ ይችላል። አንዱ ተመልካች ቀዩ ቦምብ መጀሪያ ከዚያ አረንጓዴው ሲፈንዳ ካየ ሌላው ደግሞ አረንጓዴ መጀመሪያ ከዚያ ቀዩ ሲፈንዳ ሊያስተውል ይችላላ (መረሳት የሌለበት፣ ይህ ሁሉ የሚሆነው ሰወች በብርሃን ፍጥነት አካባቢ እሚጓዙ ከሆነ ብቻ ነው)።

እንደ አንስታይን አገላለጽ፣ ሁለት ኩነቶች በ ነጥብ A እና B ቢፈጠሩ እና ነጥቦቹ በ K ስርዓት ውስጥ ታቃፊ ቢሆኑ፣ ሁለቱ ኩነቶች ባንዴ ናቸው (ባንድ ላይ ተከስቱ) የምንለው ከመሃላቸው ባለው ነጥብ M ላይ ያለ ተመልካች ሁለቱም ኩነቶች ባንድ ቅጽበት ሲከስቱ ሲያይ ብቻ ነው። ስለዚህ ጊዜ ማለት ከስርዓት K አንጻር ባንዴ የሚፈጠሩ ክስተቶችን ባንዴ እንደተፈጠሩ የሚያሳዩና በሥርዓቱ ውስጥ የማይነቀሳቀሱ ሰዓቶች ስብስብ ነው።

አንጻራዊ ጊዜና ኒውተናዊ ጊዜ

ጊዜ 
ይህ የሚያሳየው መቼትን ሲሆን በዓለም መስመር ዙሪያ በሃይል በሚፍጠነጠኑ ተመልካቾች የሚታየውን አንጻራዊ ዓለም ያሳያል። ሁለቱን የአግድም መሰምሮች የሚያልፉት የታችኞቹ ኩነቶች (በነጥብ የሚመሰሉት) (ዓላፊ ጊዜ) ለተመልካቹ ይታያሉ

ሥዕሉ የሚያሳየው በአንጻራዊ እና በኒውተናዊ ጊዜ መካከል ያለውን ልዩነት ነው። ይህ ልዩነትም የሚነሳው በጋሊልዩ ለውጥ እና በሎሬንዝ ለውጥ መካከል ባለ አለመጣጣም ነው። የጋሊሊዩ ለኒውተን ሲሰራ የሎሬንዝ ለአንስታይን ይሰራል። ከላይ ወደታች የተሰመረው መሰመር ጊዜን ይወክላል። አድማሳዊው ወይም አግድሙ መስመር ደግሞ ርቀትን ይወካልል (አንድ የኅዋ ቅጥ መሆኑ ነው)። ወፍራም የተቆራረጠው ጠማማ መስመር ደግሞ የተመልካችን መቼት ይወካልል፣ ይህ መስመር የዓለም መስመር ይባላል። ትናንሾቹ ነጠብጣቦች ደግሞ አላፊንና መጪን መቼታዊ ኩነቶች ይወክላሉ።

የዓለም መሰመር ኩርባ ደግሞ የተመልካችን አንፃራዊ ፍጥነት ይሰጣል። በሁለቱም ሥዕሎች እንደምናየው ተመልካቹ ፍጥንጥን ባለ ጊዜ የመቼቱ እይታው ይቀየራል። በኒውተናዊ ትንታኔ እነዚህ ለውጦች የጊዜን ቋሚነት አይቀየሩም ስለዚህም የተመልካቹ እንቅስቃሴ ኩነቱ አሁን መፈጠሩን ወይም አለመፈጠሩን አይለውጠውም (በስዕሉ መሰረት፣ ክስተቱ በአግድሙ መስመር ማለፉን ወይም አለማለፉን )።

በአንጻራዊ ጊዜ ትንታኔ መሰረት ግን፡ "ክስተቶችን የምንመለከትበት ጊዜ ቋሚ የማይናወጥ ሆኖ ስላ፡ ማለተ የተመልካቹ እንቅስቃሴ የተመልካቹን የብርሃን አሹሪት ማለፉን ወይም አለምፉን አይለውጥም። ነገር ግን ከኒውተናዊ (ፅኑ ትንተና) ወደ አንጻራዊ ትንተና በተሻገርን ወቅት ፣ የ"ጽኑ ጊዜ" ጽንሰ ሃሳብ አይሰራም፣ በዚህ ምክንያት ሥዕሉ ላይ እንደምናየው ክስተቶች/ኩነቶች ወደ ላይና ወደታች ከጊዜ አንጻር ይሄዳሉ፣ ይህን የሚወስነው እንግዲህ የተመልካቹ ፍጥንጥነት ነው።

የጊዜ ቀስት

ከለተ ተለት ኑሮ እንደምንረዳው ጊዜ አቅጣጫ ያለው ይመስላል፦ ያለፈው ጊዜ ተመለሶ ላይመጣ ወደ ኋላ ይቀራል፣ የወደፊቱ ደግሞ ከፊትለፊት እየገሰገሰ ይመጣል። በዚህ ምክንያት የጊዜ ቀስት ካለፈው ወደ ወደፊቱ ያለማመንታት ይገሰግሳል። ሆኖም ግን አብዛኛወቹ የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት (ፊዚክስ) ህጎች የጊዜን አንድ አቅጣጫ መከተል ዕውቅና አይሰጡም። ለዚህ ተጻራሪ የሆኑ አንድ አንድ ህግጋት በርግጥ አሉ። ለምሳሌ ሁለተኛው የሙቀት እንስቃሴ ህግ እንደሚለው የነገሮች ኢንትሮፒ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም የሚለው ይገኝበታል። የስነ ጠፈር ምርምርም በዚህ አንጻር የጠፈር ጊዜ ከመጀመሪያው ታላቁ ፍንዳታ እንደሚሸሽ ሲያስቀምጥ፣ የስነ-ብርሃን ትምህርት ደግሞ የብርሃን ጨረራዊ ሰዓት በአንድ አቅጣጫ እንደሚተምም ያስቀምጣል። ማንኛውም የመለካት ስርዓት በኳንተም ጥናት፣ ጊዜ አቅጣጫ እንዳለው ያሳያል።

ጊዜ ጠጣር ነገር ነው?

የጊዜ ጠጣርነት ምናባቂ ጽንሰ ሃሳብ ነው። በዘመናዊ ፊዚክስና በ አጠቃላይ አንጻራዊነት ትምህርት ጊዜ ጠጣር አይደለም።

የፕላንክ ጊዜ ተብሎ የሚታወቀው (~ 5.4 × 10−44 ሰከንድ ሲሆን፣ ባሁኑ ጊዜ ያሉት ማናቸውም የተፈጥሮ ህግ ርዕዮተ አለሞች ከዚህ ጊዜ ባነሰ የጊዜ መጠን እንደማይሰሩ ይታመናል (ልክ የኒውተን ህጎች ወደብርሃን ፍጥነት በተጠጋ ስርዓት ውስጥ እንደማይሰሩ)። የፕላንክ ጊዜ ምናልባትም ሊለካ የሚችል የመጨረሻ ታናቹ የጊዜ መጠን ነው፣ በመርህ ደርጃ እንኳ ከዚህ በታች ሰዓት ላይለካ እንዲችል ባሁኑ ጊዜ ይታመናል። በዚህ ምክንያት የጊዜ ጠጣሮቹ መስፈርቶች የ(~ 5.4 × 10−44 ሰከንድ ቆይታ አላቸው ማለት ነው።

ማጣቀሻወች

Tags:

ጊዜ የአዊ አለካክጊዜ በፍልስፍናጊዜ ሳይንሳዊ ትርጉምጊዜ የቆየው የሳይንስ ትርጓሜውጊዜ ማጣቀሻወችጊዜሃይማኖትሳይንስፍልስፍና

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

አይሁድናጉመላወረቀትጋብቻጡት አጥቢከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርዐቢይ አህመድቦብ ማርሊአቡነ ተክለ ሃይማኖትየዮሐንስ ወንጌልየኢትዮጵያ ብርሐረርእየሱስ ክርስቶስየውሃ ኡደትአፈወርቅ ተክሌሥነ ምግባርስታምፎርድ ብሪጅ (የእግር ኳስ ሜዳ)ኦሮሚያ ክልልገበጣፈሊጣዊ አነጋገርጌሾቁርአንዩኔስኮአሸንዳጣና ሐይቅየሰው ልጅ ጥናትኢንዶኔዥያየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንዕድል ጥናትአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭቀዳማዊ ምኒልክሰን-ፕዬርና ሚክሎንመድኃኒትአማርኛ ልብ ወለድ መፃህፍትስነ አምክንዮሉልየይሖዋ ምስክሮችአዋሳቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴትምህርትያዕቆብፀሐይጎንደር ከተማሰንበትቅኝ ግዛትዘመነ መሳፍንትካዛክስታንአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስቢግ ማክጎሽአፈ፡ታሪክቅዱስ ያሬድባሕር-ዳርትንቢተ ዳንኤልአቤ.አቤ ጉበኛወላይታደብረ ሊባኖስየዓለም የህዝብ ብዛትኢትዮ ቴሌኮምኢል-ደ-ፍራንስኤቲኤምስያትልክራርኦሮምኛዓፄ ዘርአ ያዕቆብቢልሃርዝያየቃል ክፍሎችአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነትሀዲያሮማናምሩድሶዶሰምአብደላ እዝራመስተዋድድእያሱ ፭ኛ🡆 More