አሸንዳ፡ ወይም 'የሴቶች ቀን' የትግራይ ብሄራዊ ባህል ሲሆን በአንዳንድ በትግራይ አዋሳኝ ክልሎች ይከበራል ከዚህም ውስጥ በላሊበላ አገው አከለ ጉዛይ አካባቢዋች ሚከበር ባህል ነው። 300 ዓ.ዓ በሳባውያን ህዝብ በአክሱም ውስጥ እንደተጀመረ የታሪክ አጥኝዋች ይናገራሉ። በዓሉ በወጣት ልጃገረድ ሴቶች በትግራይ ከሚከበሩ ታላቅ በአል አንዱም ነው፣ የትግራይ ሴቶች ይህን በአል ለማክበር በጉጉት ይጠብቃሉ። አሸንዳ ቃሉ ትግርኛ ሲሆን ትርጉሙም ከሳር ዓይነት የተሰጠ ነው፣ አንድ ነጭ ሽንኩርት ቅጠል እሚመስል ሰፊ እና እረዥም ተክል ነው። ይህ ተክል አሸንዳ ተብሎ ለሚታዎቀው በዓል መነሻ ሥምም ነው።
አሸንዳ፣ ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 18 ቀን ድረስ በትግራይ ይከበራል በአሉ በቅርብ ጊዜያትም ተወዳጅነቱ በመጨመሩ በኤርትራ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋ፣ ኦሮሚያ እናም ሌሎች አካባቢዎች መከበር ጀምሯል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አሸንዳ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.