የኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራ

OCTOBER 30, 2015ARCCHPRLEAVE A COMMENT

የኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራ

OCTOBER 30, 2015ARCCHPRLEAVE A COMMENT


የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የኮንሶ መልከዓ ምድር ባህላዊ ዓለም አቀፍ ቅርስ  የአስተዳደር ዕቅድ ሰነድ አስመልክቶ ለ3 ቀናት በኮንሶ ወረዳ ካራት ከተማ ከሰኔ 25-27 ቀን 2007 ዓ.ም ባዘጋጀው አውደ ጥናት የሰነዱን ክለሳ አደረገ፡፡ አውደ ጥናቱ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊዎችን ጨምሮ ሳይንቲስቶች ፣የኮንሶ ወረዳ አመራር አካላት ፣የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሙያዎች እና በኮንሶ ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተዉጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የኮንሶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት  ወቅት በአገራችን የኮንሶ ህዝብ የአኗኗር ዘይቤና መገለጫው የሆነው ታታሪነቱን መሰረት በማድረግ በመልከዓ-ምድርና ባህላዊ እሴቶች ጥበቃ በአለም አቀፍ ደረጃ እዉቅና ማግኘቱ የኮንሶ ህዝብ የአገር በቀል ዕውቀት ዉጤት ቢሆንም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት  ከፍ ያለ የዕውቀት አሻራ ያረፈበት በመሆኑ ለአስተዳደር እቅድ ሰነድ ክለሳው እየተደረገ ላለው ርብርብ አጋዥ ሆናል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዝሃነት ባላቸው ታሪካዊ፣ባህላዊና ተፈጥሮአዊ መስህቦች የተሞላች መሆኗ በአለም አቀፍ ቅርስነት ደረጃ የተመዘገቡ አስር ቅርሶች ፣ የሰው ልጅ መገኛነቷን የሚመሰክሩ በርካታ ቅሬተ አካላት ፣ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች እምቅ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች  እና አስደናቂ ባህል፣ቋንቋ እንዲሁም የራስዋ የሆነ የቀን አቆጣጠር ማሳያዎች ናቸው፤ከነዚህም ውስጥ  የኮንሶ መልከዓ ምድር ቅርስ ሲሆን ይህ  የኮንሶ መልከዓ-ምድር በርካታ ማራኪ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶች የያዘ በዋናነትም በውስጡ የተለያዩ ባህላዊ እርከኖች የሚሰሩበት፣በካብ የታጠሩ መንደሮች የተቀለሱበት፣ባህላዊ ጎጆዎን፣ጥብቅ ደኖችን፣ሀውልቶችና ባህላዊ ኩሬዎች የያዘና ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ ከመሆኑ ባለፈ አሁንም ባህላዊ ሂደቱን ጠብቆ እየተጓዘ ያለና የተለያዩ ተመራማሪዎችንና ሳይንቲስቶች ቀልብ የሚስቡ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦቿ የሚደነቁ ሲሆኑ ይህም መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የአገራችን ዘጠነኛ ቅርስ አድረጎ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 2003 ዓ.ም መመዝገቡ ይታወሳል፤ይሁን እንጂ ቅርሱ ለአለም ህብረተሰብ ከሚሰጠው ፋይዳ አንጻር በአግባቡ ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ እሴቶቹ ሳይቀየሩና ሳይበረዙ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በሚደረገው ጥረት ዉስጥ የተጋረጡ የዘመናዊነት አስተሳሰቦች ቅርሱን እንዳይጎዱት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

በአዉደ-ጥናቱ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃካፊ አቶ ለማ መሰለ በበኩላቸዉ የኮንሶ ባህላዊ መልከዓ ምድር በክልሉ መንግስት፣በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ፣በአጋር ድርጅቶች፣በዘርፉ ባለሙያዎች፣በኮንሶ ወረዳ አስተዳደርና የአከባቢው ማህበረሰብ ባደረጉት ከፍተኛ ድጋፍና  ጥረት በአለም አቀፍ ቅርሰነት መመዘገብ የኮንሶ ህዝብ ማንነት፣ባህል፣ታሪክ፣የአኗኗር ዘይቤ፣ወዘተ…ከአገራችን አልፎ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕዉቅና ለማግኘት ያስቻለው ሲሆን የክልሉንና የአገራችን ገጽታ በመለወጥ ረገድም ታላቅ ድርሻ እንዳለው እሙን ነው፤  ይህ ደግሞ በራሱ የዓለም ትኩረትን በመሳብ የኮንሶ ወረዳ ዋና የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን ያደረገ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ አከባቢው ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ እድል ፈጥሯል፤በተለይም ከቱሪስት ፍሰት መጨመር ጋር ተያይዞ የቱሪስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት በአከባቢው እንዲስፋፉ መልካም አጋጣሚም ፈጥሯል፤ይህ ደግሞ የአከባቢው ማህበረሰብ ባህላዊ ዕደ-ጥበብ ምርቶቹን ለገበያ በማቅረብ፣ወደ አከባቢው በሚመጡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በመሳተፍ እና በርካታ ተግባራት ላይ በመሰማራት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን እንዲረጋገጥ አድርጓል፤ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት  በቅርሱ ህልዉና  ላይ በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች እየተጋረጡበት ስለሚገኝ ሁሉም ባለድርሻአካላት እነዚህን ቅርሶች ከአደጋ እንዲታደጋቸው ጥሪያቸውን አስተላለፏል፡፡

በዓዉደ ጥናቱም የአለም ዓቀፍ የቅርስ ስምምነት በኮንሶ ዓለም አቀፍ ቅርስ ላይ ያለው ፋይዳ፣ቀደም ሲል የነበረው የአስተዳደር ዕቅድ ሰነድ ዉስጥ የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች፣የህግ ማዕቀፎች( በደቡብ ብ/ብ/ክ/መ/ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተዘጋጀ አዋጅ ቁጥር 141/2003 የኮንሶ ባህላዊ መልከዓ-ምድር አለም ዓቀፍ ቅርስ ለመጠበቅ የወጣ አዋጅ)፣በኮንሶ ዓለም አቀፍ ቅርስ የኮንሰርቬሽንና የጥገና ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች፣የኮንሶ ዓለም አቀፍ ቅርስ የቱሪዝም አስተዳደርና የህ/ሰብ ተጠቃሚነት እና የ2003 የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶች ስምምነትና ለኮንሶ ባህላዊ መልከዓ-ምድር ያለው ፋይዳ በሚሉት ዙሪያዎች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ወይይት የተደረገባቸው ሲሆን በዋናነትም በአሁኑ ሰዓት የኮንሶ ባህላዊ መልከዓ-ምድር አለም አቀፍ ቅርስ ያለበት ደረጃ ላይ በስፋት ውይይት ተደርጓል፡፡

በዚህም የኮንሶ መልክዓ ምድር በዓለም አቀፍ ቅርስነት ለመመዝገብ ያበቋቸው መስፈርቶች  1ኛ/ ተወዳዳሪ የሌለው ወይም ቢያንስ  ለባህላዊ አሰራር  ወይም ለአለ ወይም ለጠፋ የሰው ልጆች ስልጣኔ ብቸኛ ማስረጃ በመሆኑ 2ኛ/ ለሰው ልጆች ባህላዊ አሰፋፈር  እና የመሬት አጠቃቀም የላቀ ምሳሌ በመሆን የአንድን ህብረተሰብ ባህል የሚወክል የላቀ ምሳሌ በመሆኑ  በተለይም ቅርሱ ሊቀለበስ በማይችል ሁኔታ ለጉዳት ለሚያጋልጥ ተጽዕኖ ያልተጋለጠ በመሆኑ እና 3ኛ/  በቀጥታ ወይም በተጨባጭ መንገድ  ከሁነቶች ወይም ከህያው ባህል  ወይም አስተሳሰብ ወይም እምነት፣ ስነ-ጥበብ ወይም ስነ-ጽሁፍ  ጋር በተገናኘ የላቀ ሁለንተናዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ማለትም ፡-የቅርሱ የላቀ ሁለንተናዊ  እሴት ዓለም-አቀፍ ፋይዳ ስላለው፣ቅርሱ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ በመሆኑ  ቅርሱ ሙሉዕነቱ በአግባቡ የተጠበቀ ስለሆነ፣ ቅርሱ በቂ ባህላዊ ጥበቃ የሚደረግለት እና የአስተዳደር ሥርዓት የተዘረጋለት መሁኑን ተወስቷል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ  ቅርሱን ማስመዝገብ በራሱ ውጤት ያለመሆኑ ምክንያቱም የቅርሱን ጥበቃና እንክብካቤ ማረጋገጥ እና ቅርሱን ለዘላቂ ልማት ለማዋል እና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ቀጣይነት ያላቸውን የአስተዳደር ስራዎችን መስራት አስፈላጊ ይሆናል በማለት ጽሑፍ አቅራቢዎቹ አንስቷል፡፡

በዋናነትም በአሁኑ ወቅት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያዘጋጀው የኮንሶ ባህላዊ መልከዓ-ምድር አለም አቀፍ ቅርስ ለመጠበቅ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 141/2003ኝ የሚጻረሩ በርካታ ቅርሱን ሊጎዱ የሚችሉ ድርጊቶች እየተካሄዱ መሆናቸው ለአብነትም፡-

  • መተኪያ የሌላቸዉ የኮንሶ ባህላዊ ጎጆ ቤቶች ፈርሰው በቆርቆሮ መተካታቸው፣
  • ትክል ድንጋዮችና ዋካዎች እየተነቀሉና እየተሰባበሩ መሆኑ፣
  • የስልጣን መሸጋገሪያ ምልክትና የቃል ኪዳን መገለጫዎች ልዩ ስያሜ እየተሰጣቸው መምጣት፣
  • ቅርሶቹ ከኃይማኖት ጋር ማያያዝ፣
  • በቅርሶቹ ክልል ውስጥ የተለያዩ የልማት ተግባራት ማከናወን፣
  • ለቅርሶቹ እየተደረገ ያለው ጥበቃና እንክብካቤ አነስተኛ መሆን ፣
  • መተኪያ የሌላቸው ቅርሶች መሸጥ ወዘተ…ይጠቀሳሉ፡፡

ይህ ደግሞ በአዋጁ መሰረት የቅርሶቹን ይዘት የሚቀይሩ ማንኛዉንም እንቅስቃሴ መፈጸም ወንጀል ከመሆኑም በተጨማሪ ኮንሶ ከአለም ተምሳሌትነቷ ተሰርዞ የኮንሶ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄዎች፣የቋንቋና የስራ ባህሉና እሴቶች ይጠፋሉ፡፡

ስለሆነም ሁሉም የሚመለከተው አካል ( የኮንሶ ወረዳ የኃይማኖት አባቶች፣ሽማግሌዎች፣ ማህበረሰቡ፣ ተማሪ፣ መምህሩ፣ ሴቶች፣ የፍትህ አካሉ፣ ምክር ቤቶች፣ አስፈጻሚ አካላት ማህበራት ወዘተ …) መክረዉበት፣ሁሉም የራሱ አጀንዳ አድርጎትና የቤት ስራ አድርጎ በመዉሰድ በቀጣይነትም ድጋፍ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የኮንሶን የተፋጠነ እድገት ለማስቀጠል የድርሻው እንዲወጣ የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡

የማንነታችን መገለጫ የሆኑ ቅርሶቻችን በመጠበቅ አገራችን ኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻ እናድርጋት!

Tags:

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ጋብቻባቢሎንቻይናወርቅ በሜዳበጌምድርጅማቤተ እስራኤልነነዌፌጦድግጣየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትጂራንሆሣዕና በዓልትግርኛሮማንያዮሐንስ ፬ኛቂጥኝደብረ ሊባኖስሱለይማን እጹብ ድንቅዱባይአዋሳ2ኛው ዓለማዊ ጦርነትቦትስዋናጥርኝሐረሪ ሕዝብ ክልልቦሌ ክፍለ ከተማአውሮፓየሸዋ ኣረምየራይት ወንድማማችድንጋይ ዘመን«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት»ዓለም-አቀፍ መደበኛ የመጽሐፍ ቁጥርጭላዳ ዝንጀሮዓረፍተ-ነገርሰርቨር ኮምፒዩተርቅዱስ ያሬድዓሣመዝገበ ቃላትኤፍሬም ታምሩታሪክየኦሎምፒክ ጨዋታዎችአፈ፡ታሪክብጉንጅየአድዋ ጦርነትስፖርትፕላኔትየአክሱም ሐውልትየመቶ ዓመታት ጦርነትየዓለም የህዝብ ብዛትሐሳባዊነትቱርክገንፎሙላቱ አስታጥቄዋሊያወንዝጁፒተርአበባ ደሳለኝአቡነ ባስልዮስየማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላትኪሊማንጃሮማሞ ውድነህኣብሽገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች ሀዓፄ ዘርአ ያዕቆብመኪናዋናው ገጽኩሻዊ ቋንቋዎችደብረ አቡነ ሙሴወልደያትግራይ ክልልሰዋስውአክሱምውቅያኖስመተሬ🡆 More