ጋብቻ በሰዎች መካከል የሚፈጠር ማህበራዊ የአንድነት ሥርዓት ወይም ህጋዊ ስምምነት ነው። ስርዓቱ የሚመሠረተው በሰርግ ስነስርአት ወይም በሌላ ዝግጅት ሊሆን ይችላል። የዚህ ተቋም አወቃቀር እንደየ ባህሉ፣ እንደየ ሃይማኖቱ እና እንደየ ጊዜው ይለያያል። በወንድ እና በሴት መካከል ለሚፈጠር ጋብቻ ወንዱ ባል የሚባል ሲሆን ሴቷ ደግሞ ሚስት ትባላለች።
ጋብቻ በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመርያ የሚታየው አዳምና ሔዋን በእግዚአብሔር ፈቃድ ሲጋቡ ነው። ይኸው ጋብቻ በእግዚአብሔር አስተያየት ሁለቱም አንድ ሥጋ በሆኑበት ጊዜ ነበረ። ይህ ማለት አዳምና ሕይዋን በአምላኩ ፈቃድ ያለ ምንም ኅጢአት ፍትወታቸውን እርስ በርስ ለማርካት ተፈቀዱ። ይህ ሁኔታ ለፍቅር፣ ለደስታና ለማዝናናት የሚገባ ብቻ ሳይሆን፣ በተለይ ልጆችን ለመውለድና በቤተሠብ ለማሳደግ ያስመቻል። ስለዚህ የባልና የሚስት ጋብቻ እንደ ቸሩ አምላክ ግል ስጦታ ይቆጠራል። ከጋብቻ ውጭ ሌላ መንገድ ሁሉ ጥፋት ስለሚያመጣ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጸንተው የሚኖሩ የትዳርን ጥቅም ብዙ አይስቱም።
በብሉይ ኪዳን በሕገ ሙሴ ዘንድ የማጫ ሥርዐት ደግሞ ይጠቀሳል። ይህ ለእጮኛይቱ ወላጆች የሚበደር መጠን ነበር፤ አሁንም ብዙ ጊዜ ከጥሎሽ ጋራ (ወደ አዲሱ ቤተሠብ ከወላጆቹ ከሚመልሰው መጠን ጋር) ይደናገራል።
በዚህ የቁርኣን አንቀፅ ከምዕመናን ባህሪያት ውስጥ አላህ እንዲቀጥል ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ ሲል ይገልፃቸዋል። ለነዚህ ምርጥ የመኖሪያ አገር (ጀነት) አላቸው። በሌላ በኩል አላህ እንዲቀጥል በርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ ሠዎች መጥፎ መኖሪያ (ጀሃነም) ተዘጋጅቶላቸዋል።
ብዙ ምሁራን አላህ እንዲቀጥል ያዘዘው ማለት ዝምድና ወይም “ሲለት አር-ረሂም” እንደሆነ ይስማማሉ። ዝምድና በተመለከተ እጅግ ብዙ የቁርአን አንቀፆችና ሀዲሶች ተጠቅሠዋል።
ስለ ኡማው አንድነት ስናስብ ብዙ ነገሮችን ማሠብ ያስፈልጋል። በተለይ የቤተሠብ አንድነት ሳይኖር የኡማው አንድነት መኖር አይታሠብም። ኢስላም ቤተሰብን በሦስት ዕርከን ያየዋል። የወላጅና የልጆች ቤተሠብ፣ የእምነት ቤተሰብና የሠው ልጅ ቤተሠብ። ሦስቱም ዕርስ በርስ የተሣሠሩ አንዳቸው ለአንዳቸው አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን፤ የደም ትስስር ያለበት ቤተሠብ ከሁሉ በላይ አስፈላጊው ነው። ስለትልቁ (የሠው) ቤተሠብ ስናስብ ትንሹ ቤተሠብ (የደም ትስስር) ያለው ሚና ወሳኝ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። በጥሩ ቤተሠብ የሚያድጉ ህፃናትና ለልጆች ትኩረት የሚሰጡ ወላጆች ከሌላው በበለጠ ይበልጥ ምርታማ፣ የተረጋጋነ ሠላማዊ ናቸው። በቤተሠብ ውስጥ ሦስት ወሣኝ ነጥቦች አሉ።
ኢስላም ሶስቱንም አክብሯል። እነዚህን ዝምድናዎች መጠበቅ የኢማን ምልክት ነው። ቃል ኪዳንን መሙላት፣ የሌሎችን መብት ማወቅ፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ እንክብካቤ፣ ክብር መስጠት ሁሉ መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ወሣኞቹ ናቸው። ነብዩ ቲርሚዚ ላይ እንደተዘገበው “ከምእመናን መካከል በኢማኑ ምሉዕ የሆነው ለቤተሠቦቹ መልካም ባህሪ የሚያሳይና ሩህሩህ ነው” ብለዋል። በሌላ ዘገባ “ከናንተ መካከል ምርጡ ለቤተሠቦቹ ምርጥ የሆነው ነው። እኔ ከናንተ የበለጠ ለቤተሠቦቼ ምርጡ ነኝ።” (ኢብን ማጃህ)
“እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአዳም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ። ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና።” (ሱረቱ ኒሣዕ 4፤1)
ቤተሠብ የትስስር መረብ ነው። አንዳንዱ ቅርብ ነው። አንዳንዱ ሩቅ ነው። ኢስላምም ቅድሚያ የሚገባቸው ቅድሚያ የሚሠጣቸውና ሚዛን እንዳይዛባ ያስጠነቅቃል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጋብቻ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.