ድግጣ ወይም ዝግጣ (Calpurnia aurea) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
ዘሩ በማር ለጥፍ ለተስቦ መጠቀሙ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ተዘገበ። እንዲህ ያለ ለጥፍ ከክትክታ ዘር ጭምር ለተስቦ ሊሰጥ ይችላል። አንድ ሌላ ዝግጅት ለሆድ ትል፣ ለብርቱ ተቅማጥ ወይም ለአንገት ነቀርሳ ይሰጣል፦ የድግጣ እና የክትክታ ቅጠል፣ የምድር እምቧይና የሉት ሥር፣ የቁልቋልና የቅንጭብ ላፒስ፣ ተደቅቀው በውሃ ይጠጣል።
በፍቼ ወረዳ እንደ ተዘገበ፣ ቅጠል፣ ፍሬውና ዘሩ በምግብ ውስጥ ለውሾች ውሻ በሽታ ለማከም ይሰጣል። የድግጣ ቅጠል ተደቅቆ በውሃ ለልክፈት ወይም ለቁስል ይለጠፋል። ፍሬውም ተደቅቆ ለሆድ ቁርጠት ይበላል።
በዘጌ እንደ ተዘገበ፣ የፍሬው ወይም የቅጠል ዱቄት በማር ወይም በውሃ ለቁርባ ለማከም ይጠጣል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ድግጣ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.