ቅድስት አርሴማ

ቅድስት አርሴማ ፣ ሂርፕሲም (አርሜኒያዊት) እንዲሁም ሪሂፕሲም ፣ ሪፕሲም ፣ አርብሲማ ወይም አርሴማ ተብላ የምትጠራ ሮማዊ መሰረት ያላት ሰማዕት ነበረች። እርሷ እና ባልደረቦችዋ የሰማዕትነት አክሊል የተቀዳጁ የመጀመሪያዎቹ የአርሜንያ ሰማዕታት እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ ።

ቅድስት አርሴማ
ቅድስት አርሴማ
ቅድስት አርሴማ
ሰማዕቲት
የተወለደችው በ፫ኛው ክፍለ ዘመን
የትውልድ ቦታ ሮም ፣ጣልያን
ሌላ ስምዋ ህሪፕሲም በኢትዮጵያ የምትታወቀው በአርሴማ
የምትከበረው
  • በአርሜንያ አፖስቶሊክ ቤተክርስቲያን
  • ጆርጂያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
  • ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
  • ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
  • ሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን
  • በአሜሪካ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
የታወቀው ደብርዋ ቅድስት ህሪፕሲም ቤተክርስቲያን
ኤክሚያዝዲን በአርሜኒያ
በዓለ ንግሥ
  • መስከረም ፳፱ታኅሣሥ ፮ ቀን (ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን)
  • ሴፕቴምብር ፳፱ (ሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን)
  • ታውት ፳፱ (ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን)
  • ሴፕቴምብር ፴ (ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን)
  • ጁን ፬ (አርሜኒየን አፖስቶሊክ ቤተክርስቲያን)
ያረፈችበት ቀን መስከረም ፳፱ ቀን
ሰማዕትዋ ቅድስት አርሴማ
ቅድስት አርሴማ

እናታችን ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች ። ቤተሰቦቿ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን እንደነበሩ የገድሏ መጽሐፍ ይነግረናል ። ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቤተሰቦቿ በሚገባ የተማረች፤ የተማረችውንም በተግባር የተረጎመች፤ በጸሎት ሕይወት የምትተጋ ከቅዱሳት አንስት አንዷ ናት ።

ገድልዋ እደሚያስረዳው

ድንግል እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው ። መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና ።" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል ። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት ። ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት ። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት ። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት ። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት ። ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱስ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው ። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት ።

  • ፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት ።
  • ፪.ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት ።
  • ፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት ።

ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት ። መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር ። ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው ። በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ መቶ ሃያ ሰባት ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ ። በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ፤ ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው ። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ ። በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም ። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከበት ። ድርጥዳስ ግን ለራሱ ፈለጋት ።

የሰማዕትነትዋ መነሻ

ይቺ ታላቅ ሰማዕት በነበረችበት ዘመን በአርመን የነገሠው አረማዊ ንጉሥ ይኸው ድርጣድስ ይባላል፡፡ ይህ ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ ላይ አድሮ "ቀልጠው የተሠሩትን የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ" ብሎ የተናገረውን በመቃወም ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይንም ያመልክ ነበር ዘጸ.፴፬ ቁ.፲፯ ፡፡ በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖችን "እኔ ለማመልከው "አምላክ" ወይም ጣዖት መስገድ አለባችሁ ፤ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ትእዛዜን ጥሳችኋልና መከራ ይጸናባችኋል" የሚል ዐዋጅ በማውጣት ክርስቲያኖች ለስቃይ እዲጋፈጡ ሆ ፡፡ ጨካኙ ንጉሥ ድርጣድስ ይህን ትእዛዙን ባለማክበራቸው መከራና ስቃይ ያደረሰባቸው ክርስቲያኖች ቁጥራቸው ፻፳፯ ነበር ።

የቅድስት አርሴማ ውሳኔ

ቅድስት አርሴማም ይህን አይታ ከክርስቲያን ወገኖችዋ ጋር ወግና ስለክርስቶስ መመስከር ጀመረች ። የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ሰማዕትነትን ልትቀበል በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት ፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት ፡፡ ሚስት ትሆነው ዘንድ አብዝቶ ተማጸናት ፡፡ እጅ መንሻና ማታለየ የዚህን ዓለም ወርቅና ብር አቀረበላት ፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን መልክ ረጋፊ ፤ የዚህ ዓለም ሀብትም ከንቱ እንደሆነ ስለምታውቅ በዓላማዋ ጸናች! ንጉሡንም "እኔ የንጉሥ ክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም ፡፡" በማለት መለሰችለት ፡፡

የንጉሡም መልስና ዕድሉ

ይህን በሰማ ጊዜ ሊያስፈራራትም ሞከረ። ዓይኑዋ አያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው ። ኣልሳካልህ ቢለው በኣደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞከር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው ። እጅግ ስላፈረ ኣስገረፋት ኣሰቃያት ኣይኑዋንም አወጣ ። በመጨረሻም አንገቱዋን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት ። ከነገሩ ሁሉ በህዋላ ድርጣድስና ባለምዋሎቹ ለኣደን በሔዱበት እርኩስ መንፈስ ወደ ኣውሬነት ቀየራቸው ። የንጉሱ እንሰሳ (አውሬ) መሆን በአርሜኒያ ታላቅ ድንጋጤ ፈጠረ ። የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ ተገልጾላት " ጎርጎሪዮስን ከተቀበረበት ካላወጣቹህ አትድኑም " ኣለቻቸው ። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት ። ቅዱሱ እንደወጣ ዕረፍት አልፈለገም ፣ ለአስራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማና የ ሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው ።ድርጣድስና ባለምዋሎቾንም ወደ በርሃ ሔዶ ፈወሳቸው ።

የቅድስት አርሴማ አጽም በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ አባቶቻችን በትውፊት ይናገራሉ ።

Tags:

ቅድስት አርሴማ ገድልዋ እደሚያስረዳውቅድስት አርሴማ የሰማዕትነትዋ መነሻቅድስት አርሴማ የ ውሳኔቅድስት አርሴማ የንጉሡም መልስና ዕድሉቅድስት አርሴማ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

መርካቶዋናው ገጽ/ለጀማሪወች/ፊደል አጻጻፍወልቃይትኃይሌ ገብረ ሥላሴየሥነ፡ልቡና ትምህርትማርያምውክፔዲያእግር ኳስክትፎለጀማሪወች/አርትዖኦሮሚያ ክልልይሖዋሽመናስሜን ኮርያኢትዮጵያየባሕል ጥናትአቤ ጉበኛመንግሥቱ ንዋይዓረፍተ-ነገርአሸናፊ ከበደምዕተ ዓመትግብረ ስጋ ግንኙነትአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስኮሶጡንቻቆለጥቂጥኝሻይ ቅጠልሥነ ምግባርየነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥአውስትራልያጫትጉሬዛአጼ ልብነ ድንግልቱርክየተባበሩት ግዛቶችአውሮፕላንንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያጥቁር አባይጌሤምገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችነብርአይሁድናየኢትዮጵያ ካርታ 1936ሴቪንግ አካውንትጂፕሲዎችቅዱስ መርቆሬዎስቡናጅማ ዩኒቨርስቲውዳሴ ማርያምየኦሎምፒክ ጨዋታዎችሣህለ ሥላሴፈረስMፋኖጉልባንፊሊፒንስሐረሪ ሕዝብ ክልልአባይአለቃ ገብረ ሐናአስተዳደር ህግመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤልዩኔስኮጸሎተ ምናሴሀዲስሥርዓት አልበኝነትምጣኔ ሀብትዐምደ ጽዮንእጸ ፋርስወንዝውዝዋዜጣይቱ ብጡልማሲንቆየኢትዮጵያ ካርታ 1459 በዝርዝር🡆 More