[[
ከባህር ወለል በላይ ከ1,300 እስከ 1,500 ሜትር ከፍታ ላይ ስትገኝ የአርባ ምንጭ ከተማ አየር ንብረት በተለምዶ ቆላማ የሚሉት አይነት ሲሆን፤ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠኗ 240c ነው፡፡ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኗ 900 ሚሊ ሜትር ሆኖ ግንቦት፣ ሰኔ፣ መስከረምና ጥቅምት ወራት ከፍተኛ የዝናብ መጠን በዓመቱ ውስጥ የሚመዘግብባቸው ወራት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ስፍራ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን መንትያዎቹ የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ፤በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያ እና የተፈጥሮ ደኖችን ሌሎች ከህሊና ጓዳ የማይፋቅ ትዝታን ጥለው የሚያልፉ ሃብቶች ባለቤት ናት
በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ከተማ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን ፤ የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያን በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት እና የተፈጥሮ ደኖችን ይገኛሉ፡፡
የዞኑን አስደናቂ የቱሪስት መስህቦች እንግዶቻችንን በማስጎብኘት ከታዋቂ የዓሳ ምርታችን ፣ ከማንጎ ፤ ከሙዝ እና በአፕል ማሳችን እየተንሸራሸርን የማይረሱ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ
ከተፈጥሯዊ መስህቦች መካከል በጥልቀታቸውና በስፋታቸው እንዲሁም በልዩ አቀማመጣቸው ማራኪና ውብ ከሆኑት የስምጥ ሽለቆ ሃይቆች መካከል በመጀመሪያ ደረጃ የሚቀመጡት የአባያና የጫሞ ሃይቆች እያንዳንዳቸው ለምግብነት አገልግሎት የሚውሉ ዓሳዎችን ከማስገኘታቸው ባለፈ ተደራሽና ተመራጭ የቱሪዝም ክልል ናቸው፡፡ ከ514 ካ.ሜትር እስከ 1110 ካ.ሜትር ስፋትና ከ9 ሜትር እስከ 13 ሜትር ጥልቀት አላቸው፡
Medre Genet Arba Minch ምድረ ገነት አርባምንጭ ምድረ ገነት አርባ ምንጭ ፌስ ቡክ የጋሞ ጐፋ ዞን ባህል … የተፈጥሮ ሐብት ስፖርት … ለዞኑ እድገት የሰሩ ግለሰቦች ይመሰገኑበታል … ሙዚቃ … የጉዞ ማስታወሻ … ጥያቄ ና መልስ አዝናኝና አስተማሪ ጹሑፎች ቪድዮ ይቀርቡበታል እርሶም ምድረ ገነት አርባ ምንጭ 2 ወይም ጋሞ ጐፋ አርባ ምንጭ ፌስቡክን ላይክ እና ሼር ያድርጉ To connect with Please Visit / Like our page. LIKE, TAG & SHARE for inspiring us., sign up for Facebook todayhttps://www.facebook.com/doctor484dx?ref=hl
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጋሞጐፋ ዞን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.