ቦብ ማርሊ

ሮበርት ኔስታ ማርሊ (Robert Bob Nesta Marley; የካቲት 6 1945 - ግንቦት 11 1981 እ.ኤ.አ.

) በ1970ወቹ እና 80ወቹ ከፍተኛ እውቅናን ያገኘ ግን እስካሁን ድረስ ተወዳጅነቱ የቀጠለ የጃማይካ አገር ዘፋኝ ነበር። የሬጌን ሙዚቃ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እንዲሆን ያደረገ ዋና ሙዚቀኛ ነበር። ዘፈኖቹ ባጠቃላይ መልኩ ስለ ጃማይካ ኑሮ የሚተርኩና ስለ ራስ ተፈሪያን ሃይማኖት የሚያትቱ ነበር። በሌላ አነጋገር ዘፈኖቹ ስለፍቅር ከመተረክ ይልቅ ወደ ፖለቲካና ወደ ሃይማኖት ያጋደሉ ነበር።

ቦብ ማርሊ
ቦብ ማርሊ በ1969

ቦብ ማርሊ እናቱ ሴዴላ ቡከር የምትባል ጥቁር ጃማይካዊት ስትሆን አባቱ ደግሞ ኖርቫል ማርሊ የተባለ ነጭ እንግሊዛዊ ነበር። የሙዚቃ ሕይወቱንም የጀመረው በ1960ወቹ ፒተር ቶሽ እና በኒ ዌይለር ከተባሉ ጓደኞቹ ጋር ዘ ዌይለርስ የተባለ ቡድን በመመስረት ነበር። ከዚያም ከደጋፊ ዘፋኞቹ አንዲቱ የነበረችውን ሪታ ማርሊን በማግባት 5 ልጆች አፍርቷል። ከነዚህ ውስጥ አንዱ ዚጊ ማርሊ፣ በራሱ የተዋጣለት የሬጌ ዘፈን ተጫዋች ነው። ከቦብ ማርሊ ታላቁ የሙዚቃ ስራ ኖ ውማን ኖ ክራይ ወይም ቃል በቃል ሲተረጎም «አይ ሴትዬ አታልቅሽ» የሚለው ነበር። በርግጥም ሮበርት ኔስታ ማርሊ በአገሩ በጃማይካ እንደ ታላቅ ጀግና የሚቆጠር ሰው ነው።


ህመምና ሞት

በ1980 እ.ኤ.አ. ቦብ ማርሊ በቆዳ ነቀርሳ ምክንያት ጀርመን አገር ሲታከም ቆይቶ ወደጃማይካ ለመሄድ ሲሞክር በመንገድ ላይ አሜሪካፍሎሪዳማያሚ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በ36 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ከዚያም ጃማይካ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስነ ስርዓት ራስተፈሪያውያን ባሉበት የቀብሩ ስነ ስርዓት ተፈጸመ።

Tags:

ሃይማኖትራስ ተፈሪያንሬጌጃማይካፖለቲካ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ፈረንሣይሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታእንዶድማርያምፋሲለደስተራጋሚ ራሱን ደርጋሚድረግየኢትዮጵያ ካርታመጽሐፈ ሲራክፈሊጣዊ አነጋገርውክፔዲያአምሣለ ጎአሉከተማየሉቃስ ወንጌልክርስቶስ ሠምራምሥራቅ አፍሪካየበርሊን ግድግዳአፋር (ክልል)1940ኩሽ (የካም ልጅ)ኢሎን ማስክአፍሮ እስያዊ ቋንቋዎችየሰው ልጅ ጥናትየወባ ትንኝጊልጋመሽሀንጋርኛተረት ሀየኢትዮጵያ ካርታ 1936አርሰናል የእግር ኳስ ክለብወተትደቡብ ሱዳንሚላኖየወላይታ ዞንሳላ (እንስሳ)በርበሬሀጫሉሁንዴሳፖለቲካአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)ደበበ እሸቱየአገሮች ገንዘብ ምንዛሪየሜዳ አህያአክሊሉ ለማ።ማህበራዊ ሚዲያፍቅርአዲስ ነቃጥበብጊዜብሪታኒያብር (ብረታብረት)ካርል ማርክስፈሊጣዊ አነጋገር ሀምሳሌኮሶ በሽታሰዋስውእንስላልጋሊልዮየጋብቻ ሥነ-ስርዓትቀስተ ደመናሀዲያውሃኦሞ ወንዝዛጎል ለበስአላህቴወድሮስ ታደሰካይዘንባሕላዊ መድኃኒትአንኮበርገብረ ክርስቶስ ደስታየልብ ሰንኮፍአልፍእግር ኳስጣልያንሶማሊያበገናየዮሐንስ ወንጌልድኩላገንዘብ🡆 More