U / u በላቲን አልፋቤት 21ኛው ፊደል ነው።
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
ግብፅኛ ሐጅ | ቅድመ ሴማዊ ዋው | የፊንቄ ጽሕፈት ዋው | የግሪክ ጽሕፈት ኢውፕሲሎን | ኤትሩስካዊ U | ላቲን V | ||
---|---|---|---|---|---|---|---|
|
የ«U» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።
በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ው») ሲሆን በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኢው» (Υ, υ) ለማመልከት ተጠቀመ።
በኤትሩስክኛ ደግሞ «Y» ለአነባቢው «ኡ» ይወክል ነበር። በሮማይስጥ ቅርጹ ከ400 ዓም ያህል በኋላ እንደ «V» ተቀየረ፣ ይህም አንድላይ ተነባቢውን «ው» ወይም አናባቢውን «ኡ» አመለከተ።
እንዲሁም ከዘመናት በኋላ ተነባቢውን «ቭ» ድግሞ ለማመልከት ቻለ። ቅርጹም ከ«U» ጋር ይለዋወጥ ነበር። ከ1378 ዓም በታየ በአንድ አልፋቤት ለመጀመርያው ጊዜ «U» (/ኡ/) እና «V» (/ቭ/) እንደ ልዩ ልዩ ፊደላት ተቆጠሩ። በ1754 ዓም የፈረንሳይ አካደሚ በይፋ «U» እና «V» እንደ ልዩ ልዩ ፊደላት ይቆጥራቸው ጀመር።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ወ» («ዋዌ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ዋው» ስለ መጣ፣ የላቲን 'U' ዘመድ ሊባል ይችላል። እንዲሁም የላቲን F፣ V፣ W፣ እና Y ሁሉ ከ«ዋው» ደረሱ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article U, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.