C / c በላቲን አልፋቤት ሦስተኛው ፊደል ነው።
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
ግብፅኛ ቀመእ | ቅድመ ሴማዊ ግመል | የፊንቄ ጽሕፈት ግመል | የግሪክ ጽሕፈት ጋማ | የጥንት ኤትሩስካዊ C | ኋለኛ ኤትሩስካዊ C | ጥንታዊ ላቲን C | ||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|
|
የ«C» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ግመል» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የግመል ወይም የሚጣል ምርኩዝ ስዕል መስለ። ለምርኩዙም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት «ጋማ» (Γ γ) ደረሰ። የነዚህ ፊደላት ሁሉ ድምጽ «ግ» ነበረ። በኤትሩስክኛ ግን «ግ» የሚለው ድምጽ ስላልተለየ፣ ይህ ፊደል C እንደ K ለ«ክ» ይጠቅማቸው ነበር። የላቲን ሰዎች በፊደላቸው ደግሞ በመጀመርያ C እንደ «ግ» ወይም «ክ» ሊወክል ቻለ። በ230 ዓክልበ. ግድም አስተማሪው ስፑሪዩስ ካርቪሊዩስ ሩጋ የ«ክ» ከ«ግ» ድምጽ ለመለየት፣ «C» ትንሽ በመለውጥ አዲስ ፊደሉን «G» እንደ ፈጠረ ይባላል። ከዚህ ጀምሮ C ለ«ክ» ብቻ፣ G ለ«ግ» ብቻ ይበቃቸው ነበር።
ከዚህም በኋላ ከ500 ዓ.ም. ግድም ጀምሮ፣ «C» ከአናባቢዎቹ «E»፣ «I» ወይም «Y» ሲቀድም፣ በአሕዛብ ዘንድ እንደ «ስ» ይሰማ ጀመር። ስለዚህ ከሮማይስጥ በተወለዱት ቋንቋዎች እንደ ፈረንሳይኛ ወይም እስፓንኛ CE፣ CI እንደ «ሠ» «ሲ» ይሰማሉ፣ በእንግሊዝኛም ብዙ ጊዜ እንዲሁ ነው። በጣልኛም CE፣ CI እንደ «ቸ» «ቺ» ይሰማሉ። ሆኖም በነዚህ ልሳናት «C» ከ «A»፣ «O» ወይም «U» በፊት ሲቀድም፣ እንደ «ካ»፣ «ኮ»፣ «ኩ» ይሰማል።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ገ» («ገምል») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ግመል» ስለ መጣ፣ የላቲን 'C' ዘመድ ሊባል ይችላል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article C, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.