ኔዘርላንድ

ሆላንድ (ወይም ኔዘርላንድ ኔዘርላንድስ ኔደርላንድ፤ ሆላንድኛ፡ Nederland /ነድርላንት/) በአውሮጳ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው።

Koninkrijk der Nederlanden
የሆላንድ መንግሥት

የሆላንድ ሰንደቅ ዓላማ የሆላንድ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር "Wilhelmus"

የሆላንድመገኛ
የሆላንድመገኛ
ዋና ከተማ አምስተርዳም
ብሔራዊ ቋንቋዎች ሆላንድኛ
መንግሥት

ንጉሥ
ጠቅላይ ሚኒስትር
ፓርለሜንታዊ ንጉሳዊ አገዛዝ

ቪለም-አለክሳንደር
ማርክ ሩተ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
41,526 (134ኛ)

18.4
የሕዝብ ብዛት
የ2017 እ.ኤ.አ. ግምት
 
17,100,475 (59ኛ)
ገንዘብ ዩሮ (€)
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +31
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .nl

ስም

ኔዘርላንድ ብዙ ጊዜ «ሆላንድ» ሲባል፣ ይኸው ስያሜ በትክክል ግን የአንዱ ትልቅ ክፍላገር ስም ብቻ ነው። በሆላንድኛ፣ የ«ነድርላንት» ትርጒም «ታችኛ አገር» ሲሆን በብዙዎች ቋንቋዎች ያለው ስም ከዚህ ነው። የ«ሆላንድ» ትርጒም ደግሞ ከጥንታዊ ሆላንድኛ «ሆልት-ላንት» ማለት «እንጨት አገር» መጣ።

ባህል

የሥራ ቋንቋ ሆላንድኛምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች መካከል ይቆጠራል፤ እንዲሁም በግዛቱ ውስጥ የሚነገረው ሌላ ቋንቋ ፍሪዝኛ በቅርብ ይዛመዳል።

በሆላንድ ብዙ መስኖ፣ ቦይ ይታያል፣ ሕዝባዊ መጓጓዣ አገልግሎቱ ማለፊያ ነው። ብዙ ሕዝብ በብስክሌት ይጓዛሉ፣ ብዙ ጊዜም ይዘንባል። ብዙ ሰዎች በቡና ሱቅ ፊት ትቀምጠው ቡና ሲጠጡ ይታያሉ። ልማዳዊ አበሳሰሉ በጣም የተቀመመ አይደለም። ብዙ ታዋቂ አይቦች ከኔዘርላንድ አሉ።

ሁለት በዓለም ዝነኛ የሆኑ የሆላንድ ሰዎች ሬምብራንት፣ የ17ኛው ክፍለ ዘመን ሰዓሊ፣ እና ቪንሰንት ቫን ጎ፣ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ሰዓሊ፣ ናቸው። 1600ዎቹ የኔዘርላንድ ወርቃማ ዘመን ተብሏል።

ክሪኬት የተባለው የኳስ ጨዋታ ደግሞ በሆላንድ እንደሚወድድ እንደሚጫወትም በተረፈው ዓለም ብዙ ጊዜ አይታስብም። በመላው አገር የክሪኬት ቡድኖችና ብሔራዊ አሸናፊነት ውድድር አላቸው። ሆኖም እግር ኳስ፣ ፈጣን ተሽካካሪ ጫማ ስፖርት፣ እና ሆኪ (ገና የመሰለ ጨዋታ) ደግሞ ዋና ተወዳጅ መሠረት አላቸው።

ሆላንድ ኢትዮጵያን ለመርዳት በ1776 በምዕራባውያን ክርስቲያኖች የተቋቋመች ጥሩ አገር ነች ነገር ግን በ1940 በአዲሱ የዓለም ሥርዓት ተበላሽታ አሁን አምላክ የለሽ ሆናለች።

አራስ ልጅ ለሚጎበኙ ሰዎች ብስኩትና የእንሶስላ ዘር በስኳር ማቅረብ ሌላ የሆላንድ ባህላዊ ልማድ ነው። ለፋሲካ በዓል ደመራዎች ይነደዳሉ፣ የንጉሡ ልደት በዓል በሚያዝያ ፲፱ ቀን ሲከበር፣ ነጋዴዎች ብርቱካን ልብስ ለብሰው በከተሞች መሃል ገበያ ያደርጋሉ።

ኔዘርላንድ 
የኔዘርላንድ መንግሥት ከነጥገኛ ግዛቶቹ

የኔዘርላንድ መንግሥት ከኔዘርላንድ በአውሮጳ ጭምር በካሪቢያን ባህር ውስጥ ሌሎች ጥገኛ ግዛቶች አሉት፦ አሩባኩረሳው፣ ስንት-ማርትንና ካሪቢያን ኔዘርላንድ ደሴቶች ናቸው።


Tags:

ሆላንድኛአውሮጳ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ግራኝ አህመድካናዳዐቢይ አህመድቁጥርኩሽ (የካም ልጅ)መጽሐፈ ሄኖክየእብድ ውሻ በሽታስብሐት ገብረ እግዚአብሔርአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስሙዚቃቁስ አካልፈሊጣዊ አነጋገር ሀወሎየኢትዮጵያ ታሪክ፡ ኑብያ አክሱም ዛጉዬ ክፍል ፩/፲፬ሻይየዓለም የመሬት ስፋትካርል ማርክስቅጽልእስራኤልኢትዮጵያአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነትእሳትሞና ሊዛግብረ ስጋ ግንኙነትጥበቡ ወርቅዬቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊኮልፌ ቀራንዮትዝታመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስግመልጉልባንየጢያ ትክል ድንጋይሆሣዕና በዓልክራርአልበርት አይንስታይንቅዱስ ገብርኤልሚያዝያሥርዓትፕሩሲያጂዎሜትሪጀርመንተራጋሚ ራሱን ደርጋሚጋሞጐፋ ዞንባቲ ቅኝትየጅብ ፍቅርመጽሐፍ ቅዱስሥነ ዕውቀትሂሩት በቀለብጉንጅሳህለወርቅ ዘውዴአበበ በሶ በላ።ሐረርማሌዢያአባይሰምኢሎን ማስክኣለብላቢትኢንጅነር ቅጣው እጅጉየቀን መቁጠሪያየኢትዮጵያ እጽዋትሰሜን ተራራአርሰናል የእግር ኳስ ክለብገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችየምድር ጉድየንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥታይላንድውዳሴ ማርያምፌቆአያሌው መስፍንየንቅያ ጸሎተ ሃይማኖትኤቲኤምስዊዘርላንድየወታደሮች መዝሙርፀሐይ🡆 More