(ወደፊት ገስግሺ ውድ እናት ኢትዮጵያ)
የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ ለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነት በእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት መሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርን ህዝቦች ነን ለስራ በስራ የኖርን ድንቅ የባህል መድረክ ያኩሪ ቅርስ ባለቤት የተፈጥሮ ፀጋ የጀግና ህዝብ እናት እንጠብቅሻለን አለብን አደራ ኢትዮጵያችን ኑሪ እኛም ባንቺ እንኩራ።
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ -ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረተሰባዊነት - አብቢ ለምልሚ! ቃል ኪዳን ገብተዋል - ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ - ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ አንድነት - ለነፃነትሽ መስዋዕት ሊሆኑ - ለክብር ለዝናሽ! ተራመጂ ወደፊት - በጥበብ ጎዳና ታጠቂ ለሥራ - ላገር ብልጽግና! የጀግኖች እናት ነሽ - በልጆችሽ ኩሪ ጠላቶችሽ ይጥፉ - ለዘላለም ኑሪ።
በ1968 ዓ.ም፣ ዘመነ ደርግ
(ማርሽ ተፈሪ)
ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉስሽ ተባብረዋልና አርበኞችሽ አይነካም ከቶ ነፃነትሽ ብርቱ ናቸውና ተራሮችሽ አትፈሪም ከጠላቶችሽ። ድል አድራጊው ንጉሣችን ይኑርልን ለክብራችን።
በ1919 ዓ.ም፤ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (አጼ ቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ)
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.