ሣህለ ሥላሴ

ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የሸዋው መስፍን የራስ ወሰን ሰገድ እና የመንዝ ባላባት የአፍቀራ ጎሌ ልጅ የወይዘሮ ዘነበ ወርቅ ልጅ ናቸው። በዘመኑ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ የሚገዛ ምኒልክ የሚባል ንጉሥ ይነግሣል የሚባል ንግርት ስለነበር፣ አባታቸው ምኒልክ ብለዋቸው ነበር። ሣኅለ ሥላሴ ትምህርታቸውን በሰላ ድንጋይ ደብር ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ አባታቸው ራስ ወሰን ሰገድ ቁንዲ ላይ ሰኔ ፩ ቀን ፲፰፻፭ ዓ/ም ላይ ሲያርፉ የሸዋን አልጋ አውርሰዋቸው አለፉ። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ‘የኢትዮጵያ ታሪክ ፦ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል በሚለው መጽሐፋቸው በገጽ ፷፭ ላይ “የራስ ወሰን ሰገድ የበኩር ልጅ አቤቶ በኩሩ የመርሐቤቴን አበጋዝነት ተሾሞ ይኖር ነበርና በአባቱ አልጋ እንዲቀመጥ ተጠርቶ ጅሩ ሲደርስ የጅሩ ጋላ /ኦሮሞ/ መንገዱን ዘግቶ ስምንት ቀን ሙሉ ስለተዋጋው ሳይመጣ ቢቆይ የወሰንሰገድ መኳንንት ባልጋው ሰው ሳይቀመጥ ብዙ ቀን የቆየ እንደሆነ የጋላ//ኦሮሞ/ ኃይል በርትቶ ሸዋን በጭራሽ የሚያጠፋው ስለመሰላቸው፣ ታናሹን ልጁን አቤቶ ሣህለ ሥላሴን ከቁሮ ገደል /ከሰላድንጋይ/ አምጥተው በተወለደ በ፲፰ ዓመቱ በአባቱ አልጋ አስቀመጡት።” በሚል ትንሽ በተለየ መልክ አስቀምጠውታል።

ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ
ንጉሠ ሸዋ
ግዛት ጥቅምት ፪ ቀን ፲፰፻፵ እስከ ጥቅምት ፴ ቀን ፲፰፻፵፰ ዓ.ም.
ቀዳሚ ራስ ወሰን ሰገድ
ተከታይ ንጉሥ ኃይለ መለኮት
ባለቤት ወ/ሮ እጅጋየሁ
ወ/ሮ ትደንቂያለሽ
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ራስ ወሰን ሰገድ
እናት ወ/ሮ ዘነበ ወርቅ ጎሌ
የተወለዱት 1824 እ.ኤ.አ.
የሞቱት ጥቅምት ፴ ቀን ፲፰፻፵፰ ዓ.ም. አታክልት
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና
ሣህለ ሥላሴ
ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ
ሣህለ ሥላሴ

ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ከብሪታኒያ መንግሥት ጋር አንጎለላ ላይ ኅዳር ፲ ቀን ፲፰፻፴፬ ዓ/ም የተፈራረሙት የወዳጅነትና የንግድ ውል በሰፊው የተዘገበ ሲሆን፤ ከፈረንሲስ ንጉሥ ጋር ደግሞ ተመሳሳይ ውል ሰኔ ፩ ቀን ፲፰፻፴፭ ዓ/ም ተፈራርመዋል።

የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ልጆች

ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የአራት ወንዶችና የአምስት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ። ከነኚህም፦

  • ከወይዘሮ በዛብሽ የሚወለዱት ልጅ በሻህ ወራድ (በኋላ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ )
  • ከወይዘሮ ይመኙሻል የሚወለዱትና የመርዕድ አዝማችነትን ማዕረግ በዓፄ ቴዎድሮስ የተሾሙት ኃይለ ሚካኤል ሣህለ ሥላሴ።
  • ልዑል ራስ ዳርጌ (አባ ገርሳ)
  • አቤቶ ሰይፉ ሣህለ ሥላሴ
  • ልጅ አስፋ ወሰን ሣህለ ሥላሴ
  • ልዕልት ተናኘወርቅ ሣህለ ሥላሴ

ዋቢ ምንጮች

  • ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤‘የኢትዮጵያ ታሪክ ፦ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል”

Tags:

1805መንዝሰኔ ፩ሸዋኅሩይ ወልደ ሥላሴአድዋኢትዮጵያጅሩ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ድንቅ ነሽዶሮፍትሐ ነገሥትአፍሪቃአማራ ክልልመስተዋድድኪሮስ ዓለማየሁደብረ ዘይትፍቅርአዲስ ነቃጥበብየፖለቲካ ጥናትህግ አውጭየኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራብሪታኒያበለስበዓሉ ግርማቴወድሮስ ታደሰጎሽአፈርየማርያም ቅዳሴቼልሲቬት ናምፈሊጣዊ አነጋገር የመጽሐፍ ቅዱስከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርሀጫሉሁንዴሳእስራኤልገድሎ ማንሣትጴንጤየተባበሩት የሀገር ንጉሳዊ አገዛዝልብነ ድንግልባህር ዛፍቀዳማዊ ምኒልክጊዜኢንጅነር ቅጣው እጅጉየሰው ልጅሴምሰይጣንነፍስሥርዓትአክሱምነፕቲዩንመድኃኒትአዶልፍ ሂትለርመለስ ዜናዊእንስላልተረት ሀአርሰናል የእግር ኳስ ክለብደቡብ ኦሞአፈ፡ታሪክአስርቱ ቃላትቀዳማዊ ዓፄ ዮሐንስተሳቢ እንስሳግብፅየንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥኢትዮጵያጋኔንኣቦ ሸማኔህብስት ጥሩነህዓፄ ቴዎድሮስቂጥኝውዝዋዜጾመ ፍልሰታአፋር (ብሔር)የጋብቻ ሥነ-ስርዓትየዓለም የመሬት ስፋትአምባሰልሄክታርሳምንትዛጎል ለበስየንቅያ ጸሎተ ሃይማኖትጥናትየማርቆስ ወንጌልቀጤ ነክሥላሴ🡆 More