N / n በላቲን አልፋቤት አሥራ አራተኛው ፊደል ነው።
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
ግብፅኛ ጀ | ቅድመ ሴማዊ ኑን | የፊንቄ ጽሕፈት ኑን | የግሪክ ጽሕፈት ኑ | ኤትሩስካዊ N | ላቲን N | ||
---|---|---|---|---|---|---|---|
|
የ«N» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ኑን» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የእባብ ስዕል መስለ። የግብጽኛ ተናባቢ ድምጽ ምልክቶች በሚል ጽሕፈት ለዚህ ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ለድምጹ «ጀ» ነበር፤ በሴማውያን ዘንድ ግን «ን» ሆነ። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "ኑ" (Ν ν) ደረሰ።
ከ400 ዓክልበ. ግድም በፊት፣ በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት እንዲሁም በጥንታዊ ኢታሊክ አልፋቤት የ«ም» ቅርጽም እንደ «𐌌» ይምሰል እንደ ነበር የ«ን» ቅርጽ ደግሞ እንደ «𐌍» ይጻፍ ነበር። ከዚያስ የ«𐌌» (ም) ቅርጽ እንደ ዛሬ M እንደ ሆነ፣ እንዲሁም የ«𐌍» (ን) ቅርጽ የዛኔ ወደ N ተቀየረ።
በአንዳንድ ቋንቋ በተለይም በእስፓንኛው አልፋቤት ተጨማሪው ፊደል «Ñ» (/ኝ/) ከN የደረሰ ነው። በእስፓንኛ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይህ Ñ የተለየ ፊደል ሆኖ ተቆጥሯል፤ መጀመርያ ግን በጋሊስኛ ከ1220 ዓም ታውቋል።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ነ» («ነሐስ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ኑን» ስለ መጣ፣ የላቲን 'N' ዘመድ ሊባል ይችላል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article N, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.