ሥነ ሕይወት

ሥነ፡ሕይወት ወይም ባዮሎጂ የሕይወት ጥናት ነው። ባዮሎጂ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ባሕሪ፣ ጸባይ፣ አፈጣጠር እና ከአካባቢያቸው ጋር እርስ በርስም ያላቸውን ግንኙነት ያጠናል። በባዮሎጂ ስር አጅግ በጣም ብዙ ንዑስ ጥናቶች አሉ።

የታሪክ ዝርዝር

ቃሉ «ባዮሎጂ» የግሪክ ቋንቋ ሲሆን፣ በግሪክኛ «ቢዮስ» (βίος) ሕይወት ማለት ሲሆን «ሎጎስ» (λόγος) ጥናት ማለት ነው። ሥነ-ህይወት፣ የተፈጥሮ ሰገል (ጥናት) ሲሆን የሚያጠናውም ህያው ፍጥረታትን ሆኖ፣ አቋማቸውን፣ ግብረታቸውን፣ እድገታቸውን፣ አመጣጣቸውን፣ ዝግመተ-ለውጣዊ ይዘታቸውን፣ ሥርጭታቸውን እና የመሳሰሉትን ሁሉ ያካትታል። ይህ ሥነ-ጥናት እጅግ ሰፊና ጥልቅ ሲሆን ብዙ ርዕሶችንና ንዑስ ጥናቶችን ያካትታል። ዓብይ ከሆኑት ርእሶቹ መካከል አምስት የሚሆኑትን የሥነ-ህይወት ጥናት ዋልታዎች አድርጎ መጥቀስ ይቻላል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፦

  • ህዋሳት የህይወት መሠረት ናቸው፣
  • አዳዲስ ዝርያዎችና የሚወረሱ አካላዊ ባሕርያት የዝግመተ ለውጥ ውጤቶች ናቸው፣
  • ዘረ-መልዓት የዘራዊ ውርስ መሠረታዊ መለኪያዎች ናቸው፣
  • አንድ ፍጡር የራሱን ውስጣዊ ነገሮች በመቆጣጠር የጸና እና የረጋ የመኖር ሁኔታን ይፈጥራል፣
  • ህያው ፍጡራን ጉልበትን ይጠቀማሉ ይለውጣሉም።

የሥነ ሕይወት ንዑስ-ርዕሳን የሚለዩት ፍጥረታትን በሚለኩበትና በሚያጠኑበት ዘይቤ ነው። የህያዋን ሥነ-ጥነተ-ንጥር ህይወታዊ ጥንተ-ንጥርን ያጠናል፤ የሞለኩይል ሥነ-ህይወት የተዋሰበውን ሥነህይወታዊ የሞለኩይል መዋቅር ያጠናል፤ ህዋሳዊ ሥነ-ህይወት የህይወት ገንቢ ጡብ የሆነውን የህዋሳትን ባሕርይ ያጠናል፤ ሥነ-ህይወታዊ ቅንጅታዊ ጥናት የህያዋንን የሰውነት ብልቶችና የብልቶችን መዋቅር፣ አቋማዊና ጥንተ-ንጥራዊ ግብረት ያጠናል፤ ሥነ-ህይወታዊ መዋቅር ደግሞ የሰውነት ክፍሎች ከከባቢያቸው ጋር እንዴት እንደሚሰሩና እንደሚግባቡ ያጠናል።

ናሙና ዝርዮች ፎቶዎች

Tags:

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ግስበትተረት ሀሶፍ-ዑመርየጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርሥርዓት አልበኝነትፍቅር እስከ መቃብርየኢትዮጵያ አየር መንገድፈረንሣይአስርቱ ቃላትአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነትአጥናፍሰገድ ኪዳኔኣለብላቢትእጸ ፋርስግሥላጅቡቲ (ከተማ)ዳዊትምሳሌፊሊፒንስህግ ተርጓሚአማርኛ ልብ ወለድ መፃህፍትሸዋዓለማየሁ ገላጋይኢል-ደ-ፍራንስሶቪዬት ሕብረትቋንቋግብርሞንቴቪዴዮ ዋንደረረስጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊኒንተንዶካዛክስታንየተፈጥሮ ሀብቶችመለስ ዜናዊጃቫቀነኒሳ በቀለመስቃንእስራኤልቤተ ማርያምአገውሙሴፍቅር በዘመነ ሽብርውዝዋዜኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ)ሰባአዊ መብቶችሰዓት ክልልረጅም ልቦለድጆርዳኖ ብሩኖካይዘንሙዚቃየሜዳ አህያየዓለም የህዝብ ብዛትምግብሀጫሉሁንዴሳሚያዝያአብዲሳ አጋሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚትጠላአረቄአፋር (ክልል)ሲንጋፖርጉልባንማሌዢያፍትሐ ነገሥትአዳማበላይ ዘለቀመጽሐፍ ቅዱስግሪክ (አገር)የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችኢንዶኔዥያጂፕሲዎችየሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንደበበ ሰይፉጉጉትየኦቶማን መንግሥትዛጔ ሥርወ-መንግሥትጣልያን🡆 More