በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት

በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት

የሕዝቡ መብቶች ክፍል

  • አንቀጽ 37። ማንም ሰው በሕግ እኩል ሆኖ ይጠበቃል።
  • አንቀጽ 38። በብሔራዊ (ሲቪል) መብቶች በመጠቀም ረገድ፡ በኢትዮጵያውያኖች (የኢትዮጵያ ተገዦች) መካከል ምንም ልዩነት አይኑር።
  • አንቀጽ 39። የኢትዮጵያ ተወላጅነትንና የኢትዮጵያ ዜግነትን ለማግኘትና ለማጣት የሚያስችሉ ኹኔታዎችን ሕጉ ይቀምራል (ይወስናል)።
  • አንቀጽ 40። የሕዝቡን መልካም ጠባይ ወይም ፀጥታን ወይም በፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር፡ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት የሚኖሩ ሰዎች በሕግ መሠረት የሃይማኖታቸውን ሥርዓት አክብረው በነፃ ከመፈጸም አይከለከሉም።
  • አንቀጽ 41። በመላው የንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ በሕግ መሠረት የንግግርና የጋዜጣ ነፃነት የተፈቀደ ነው።
  • አንቀጽ 43። ማንኛውም ሰው ከንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት ውስጥ ሕይወቱን ነፃነቱን ወይም ንብረቱን ያለ ሕግ አያጣም።
  • አንቀጽ 45። የኢትዮጵያ ዜጎች በሕጉ ተዘርዝሮ በሚወስነው መሠረት የጦር መሣሪያ ሳይዙ ሰላማዊ ስብሰባ ለማድረግ መብት አላቸው።
  • አንቀጽ 46። በሕግ ካልተከላከለ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ውስጥ ከሥፍራ ወደ ሥፍራ የመዛወርና መኖሪያ ሥፍራን የመለወጥ ነፃነት ለንጉሠ ነገሥት መንግሥት ዜጎች ሁሉ ተረጋግጧል።
  • አንቀጽ 47። ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በሕግ መሠረት ማናቸውም ዓይነት ሥራ እየሠራ ለመኖር፤ ማናቸውም የሥራ ማኅበር ለማቋቋምና በማናቸውም ማኅበር አባል ለመሆን መብት አለው።
  • አንቀጽ 49። ማንኛውም የኢትዮጵያ ተገዥ ከንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውጭ ለመሳደድ (ሌቅቆ እንዲወጣ) ሊገደድ አይችልም።

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ተድባበ ማርያምወላይታዘጠኙ ቅዱሳንጠጣር ጂዎሜትሪየባቢሎን ግንብቁልቋልሳማሂሩት በቀለኩልዒዛናየማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላትየኢትዮጵያ ካርታ 1690ቅፅልንጉሥአርሰናል የእግር ኳስ ክለብሥነ ንዋይሶሀባ (sahabah)/ኡሙ አይመን በረካ(ረ.ዐንሁ)ታፈሪ ቢንቲቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ቡድንገዳም ሰፈርሀጫሉሁንዴሳዳማ ከሴመሠረተ ልማትአሸንድየሙዚቃቤተ ጊዮርጊስደቡብ አፍሪካአቡጊዳየኢትዮጵያ ካርታ 1459 በዝርዝርአቡነ ቴዎፍሎስአቡነ ተክለ ሃይማኖትገብርኤል (መልዐክ)ጋስጫ አባ ጊዮርጊስግራዋርዕዮተ ዓለምግሪክ (አገር)ሀዲስ ዓለማየሁማንጎድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳገናስቲቭ ጆብስእንጀራደበበ ሰይፉሲዳማአሦርሙሉቀን መለሰአፈ፡ታሪክአንዶራወለተ ጴጥሮስዓርብተምርቻቺ ታደሰአቡነ ባስልዮስሊቨርፑል የእግር ኳስ ክለብቢዮንሴመጽሐፈ መቃብያን ሣልስጋሊልዮትግራይ ክልልመንግሥትአዋሽ ወንዝጥላሁን ገሠሠወርጂኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ)ትምህርትበላይ ዘለቀየተባበሩት የሀገር ንጉሳዊ አገዛዝኡዝቤኪስታንመብረቅMetshafe henokዐቢይ አህመድሕግገንፎቦትስዋናየሺጥላ ኮከብየአፍሪቃ አገሮች🡆 More