ፖታሺየም (ፖታሲየም) የንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥ ውስጥ ኬሚካዊ ውክሉ K ነው። አቶማዊ ቁጥሩም 19 ነው።
ስሙ ፖታሺየም (potassium) ከእንግሊዝኛው ቃል «potash» /ፖታሽ/ ሲሆን እሱም ከቃሎቹ pot /ፖት/ (ድስት) እና ash /አሽ/ (አመድ) ወይም «የድስት አመድ» እንደ ማለት ነው።
ኬሚካላዊ ውክሉ K ከሮማይስጥ ስሙ Kalium /ካሊዩም/ ሲሆን ይህ ዘመናዊ ቃል ከ«alkali» አልካሊ መጣ፤ ፖታሺየም ለጥንታዊ ሮማውያን አልታወቀም ነበርና ቃሉ (ካሊዩም) «አዲስ ሮማይስጥ» ይባላል። አልካሊ የሚለው ቃል ደግሞ ከአረብኛ «አል-ቃልያህ» («የአትክልት አመድ») ተወሰደ። ፖታሺየም መጀመርያው የታወቀው የአትክልት አመድ በድስት ውስጥ በመስጠም ሲፈጠር ነበርና።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ፖታሺየም, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.