መሰንቆ (ወይም ጭራ ዋጣ) ባለ አንድ ክር የሙዚቃ መጫወቻ ሲሆን እንደ ቫዮሊን በደጋን ሲመታ የሙዚቃ ቃና ይሰጣል።
አንድ የፍየል ወይንም የበግ ቆዳ ያስፈልጋል፤ እንዲሁም የወይራ እንጨት እንዲሁም የፈረስ ወይንም የበሬ ጅማት ያስፈልጋል።
የመሰንቆን ከየት መጣ በቅጡ ለመረዳት አዳጋች ቢሆንም በአንድአንድ የምዕራብ አፍሪካ እና መካከለኛ ምሥራቅ ሀገራት በድምጽ የሚመሳሰሉ አካላዊ ቅርጻቸው ግን ልዩነት ያላቸው መሣሪያዎች አሉ። መሰንቆ በቤተ መንግሥት መኳንንትን ለማስደሰት፣ ጦርነት የሆነ እንደሆነ ደግሞ ወታደሩን በስሜት ለመቀስቀስ ይጠቀሙበት ነበር። በማዕረግ ደረጃም ሊቀ መኳስ በሚል ስያሜ ሹመት ይሰጣቸው ነበር። ለምሳሌ ያህል በዓድዋ ጦርነት ተሳትፈው የነበሩት፤ የወሎው ንጉሥ የራስ ሚካኤል ባለሟል ሀሰን አማኑ ጥይት ባይተኩሱም በግጥሞቻቸው ጣልያንን መደቆሳቸውን ታሪክ ይመሰክራል። ወታደሩን ከማነሳሳት አንጻር የአዝማሪዎቹ ድርሻ ከፍተኛ ነበር። ለዚያም ነው በሁለተኛው የኢጣሊያ ወረራ አዝማሪዎች ከያሉበት ተሰብስበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረገው።
መሰንቆ ሀገር አቀፋዊ የአሠራር ስታንዳርድ የለውም። በመሆኑም የጭራው ብዛት እና ርዝመት፣ የተሠራበት የእንጨት ዓይነት፣ የተጠቀምነው የቆዳ ዓይነት እና የጭራውን ፍሪክሽን ለመቀነስ የተጠቀምንበት ዕጣን ለድምጹ መለዋወጥ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ማሲንቆ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.