ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት

እስጢፋኖስ (በግሪክ: Στέφανος ሲነበብ ፡ Stéphanos ስቴፋኖስ ፤ በዕብራይስጥ ፡ הקדוש סטפנוס ፤ በእንግሊዘኛ ፡ Stephen ሲነበብ ፡ ስቴፈን) በሕገ ወንጌል (በክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው ።

ቅዱስ እስጢፋኖስ
ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት
የቅዱስ እስጢፋኖስን ውግረት የሚያሳይ ስዕል
ቀዳሚ ሰማዕት
የተወለደው በ፩ኛው ክፍለ ዘመን
የትውልድ ቦታ ኢየሩሳሌም
የእናት ስም ማርያም
የአባት ስም ስምዖን
የሚከበረው በመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ሥንክሳር
በዓለ ንግሥ ሲመቱ ጥቅምት ፲፭ ቀን
ዕረፍቱ ጥር ፩ ቀን
ፍልሰቱ መስከረም ፲፯ ቀን
በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ቶቢ ፩ ቀን
በምዕራባውያን ዲሴምበር ፳፮ ቀን
ያረፈበት ቀን ጥር ፩ ቀን በመናፍቃን በድንጋይ ተወግሮ

ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር ። ይህም በወጣትነት ያለፈችው ሕይወቱ ስትሠራ የነበረው ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ ይመሠክራል ።

የመጀመሪያው ሕይወቱ በአጭሩ

የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ ። (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ ። የወቅቱ ታላቅ መምህር ገማልያል ይባል ነበር። ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፭፥፴፫ ላይ ተጠቅሷል ። በትውፊት ትምህርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን፣ ጳውሎስን ፣ ናትናኤልን፣ ኒቆዲሞስን...) አስተምሯል ። በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር ፤ በፍጻሜውም አምኗል ። ቅዱስ እስጢፋኖስም ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ ። ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር ።

ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ ጋር

በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ ። ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ። ለስድስት ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ ። ለስድስት ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በኋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ ። በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምህሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው ። "ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው ።" በሚል ላከው ። ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ እጅ ነስቶ ተማረ ። (ሉቃ. ፯፥፲፰) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ ።

ወንጌል ስለማጥናቱ

ጌታም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው ፤ አጋንንትም ተገዙለት ። (ሉቃ. ፲፥፲፯) ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ ፤ ምሥጢር አስተረጐመ ። ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኳል ። በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ጵጵስናን) ተሹሟል ። በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት፣ ምሥጢርም የተገለጠለት የለም ። በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ ።

በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ሰባቱ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር ። አልፎም የስድስቱ ዲያቆናት አለቃ እና የስምንት ሺው ማኅበር መሪ(አስተዳዳሪ) ሆኑዋል ።  ስምንት ሺህ ሰውን ከአጋንንት መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አባቶቻችን መጠየቅ ነው ። አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለደኅንነት ማብቃት እንኳን እጅግ ፈተና ነው ። መጸሐፍ እንደሚል ግን መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ማኅደር እግዚአብሔር ነውና ለርሱ ተቻለው ። (ሐዋር፣ሥ፡፮ ቁ፡፭)

አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ሲባል እንደዘመኑ ይመስለን ይሆናል ። እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው ። ዲቁና ለእርሱ " በራት ላይ ዳርጎት" እንጂ እንዲሁ ድቁና አይደለም ።

ከጌታችን እርገት በኋላ

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺውን ማኅበር እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት "እጠፋ እጠፋ" አለች ። በዚህ ጊዜ "ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው  ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው " ብለው አይሁድ በማመናቸው አልቀረም ገደሉት ። እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው ። በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት ። ደቀ መዝሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት ።

ከአረፈ በኋላ 

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከአረፈ ከሦስት መቶ ዓመት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበረ ስሙም ሉኪያኖስ ይባላል ። በተደጋጋሚ በራዕዪ ቅዱሱ እየተገለጠለት "ሥጋዬን አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለጳጳሱ ነገረው ። ጳጳሱም ደስ ብሎት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አፀደ ገማልያል ማለት ወደ መምህሩ ሄደ ። ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ ። መላዕክት ሲያጥኑም በጎ መዓዛ ሸተተ ። ዝማሬ መላዕክትም ተሰማ ። ሕዝቡና ጳጳሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው በታላቅ ዝማሬና በሐሴት ዐፅሙን ከዚያ አውጥተው በጽርሐ ጽዮን (በተቀደሰችው ቤት) አኖሩት ። እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተክርስቲያን አነጸለት ወደዚያ  አገቡት ።

ከአምስት ዓመታት በኋላም እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጎን አኖሩት ። የእስክንድሮስ ባለቤት ግን ወደ ሀገሩዋ ቁስጥንጥኒያ ስትመለስ የባሏ ሥጋ መስሉዋት የእስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው ። መንገድላይም ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው ። እጅግም ደስ አላት አምላክ ለዚህ አድሉዋታልና ። እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጥንጢኖስ አስረከበችው ። በከተማው ታላቅ ሐሴት ተደረገ ። ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች ። በዚያም ላይ ትልቅ ቤተክርስቲያን ታንጾለታል ።

ማጣቀሻ

ቅዱስ እስጢፋኖስ

  • ሲመቱ ጥቅምት ፲፯ ቀን
  • ዕረፍቱ ጥር ፩ ቀን
  • ፍልሰቱ መስከረም ፲፭ ቀን ነው ።

Tags:

ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት የመጀመሪያው ሕይወቱ በአጭሩቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ ጋርቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ወንጌል ስለማጥናቱቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ከጌታችን እርገት በኋላቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ከአረፈ በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ማጣቀሻቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕትክርስትናዕብራይስጥግሪክ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ስዊዘርላንድየሥነ፡ልቡና ትምህርትተውላጠ ስም2ኛው ዓለማዊ ጦርነትዒዛናመልከ ጼዴቅማሪቱ ለገሰሶፍ-ዑመርአስርቱ ቃላትስምኩንታልደብረ-ዕንቁ ወይብላ ማርያምአባይ ወንዝ (ናይል)ክራርማኅበረ ቅዱሳንየወባ ትንኝዋናው ገጽፊልምጥድንጉሥመንግሥተ አክሱምየወፍ በሽታቁጥርየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዱባይፋሲለደስጂጂእምስሽፈራውከተማአባ ጅፋር IIየቃል ክፍሎችቀዳማዊ ምኒልክየትነበርሽ ንጉሴኩሽቲክ እና ኒሎቲክ ሕዝቦችፍርድ ቤትመለስ ዜናዊያማርኛ ሰዋስው (1948)የሉቃስ ወንጌልየፈጠራዎች ታሪክኩዌትጸሎተ ምናሴዶሮሲሳይ ንጉሱጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊደብረ ዳሞአልበርት አይንስታይንቅዱስ ሩፋኤልቁላአክሱምህዋስየሲስተም አሰሪፈቃድፍቅር እስከ መቃብርሥነ ጽሑፍአውግስጦስአቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞዶሮ ወጥየይሖዋ ምስክሮችየአድዋ ጦርነትአንዶራኃይሌ ገብረ ሥላሴዓለም-አቀፍ መደበኛ የመጽሐፍ ቁጥርሕገ መንግሥትየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችስልጤሸዋንግሥት ኤልሣቤጥ ዳግማዊትየሺጥላ ኮከብዩናይትድ ኪንግደምኢያሱ ፭ኛስልጆአትላንቲክ ውቅያኖስየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግጤፍቡርኪና ፋሶ🡆 More