ድመት አንስተኛ ስጋ በሊታ እንስሳ ስትሆን እቤት ውስጥ አይጥና የመሳሰሉትን ተውሳኮች ለመያዝ ታገለግላለች።
ድመት በአሁኑ ጊዜ ከሁሉም እንስሳ በላይ በቤት እንስሳነቱዋ ተፈላጊነትን ያላት ናት። ተመራማሪወች የድመትን ለማዳነት ቢያንስ ቢያንስ 9500 ዓመት እንደሚሞላው ሊያረጋግጡ ችለዋል።
የቤት እንስሳ ድመቶች እንዳሉ ሁሉ በየዱሩም የሚላወሱ፣ ምግባቸውን አድነው መብላት የሚችሉ ድመቶችም አሉ። ለማደን እንዲረዳቸውም አይናቸው የሰው ልጅ ማየት ከሚችልበት 1/6ኛ ብርሃን ውስጥ እንኳ ይሰራል፣ ጆሮዋቸውም ከሰውና ከውሻ ይልቅ በጣም ሃይለኛ ነው፣ አፍንጫቸውም እንዲሁ። የድመቶች ድክመት ምንድን ነው፣ ስኳር ስኳር የሚልን ነገር መቅመስ አይችሉም፣ ከዚ በተረፈ አይናቸው ከአረንጓዴና ሰማያዊ ቀለማት ውጭ መለየት አይችልም። ለምሳሌ ቀይና አረንጓዴ ለድመት አንድ አይነት ቀለም ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ድመት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.