ይስማዕከ ወርቁ ኢትዮጵያዊ ወጣት ደራሲ ሲሆን ዴርቶጋዳ በተባለዉ መፅሀፉ በአንባቢዎቹ ዘንድ ታዋቂነትን አግኝቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዴርቶጋዳ በአንድ አመት ብቻ 10 ጊዜ በመታተም እና በመጀመሪያ እትሙ ከ 200,000 (ሁለት ሠቶ ሽህ) በላይ ኮፒወች በመሸጥ በኢትዮጵያ የመፅሀፍ ሽያጭ ታሪክ የመጀመሪያው መፅሀፍ ነው። ይስማዕከ እስካሁን አስራ አምስት መፅሀፍትን ለህትመት አብቅቷል (የመጀመርያ መፅሀፉ)፣ የወንድ ምጥ የተሰኜው የግጥም መድብል ነው። የቀንድ አውጣ ኑሮ ዴርቶጋዳ ራማቶሓራ ዣንቶዣራ ዮራቶራድ ዮቶድ ሜሎስ ተልሚድ ክቡር ድንጋይ፣ የኦጋዴን ድመቶች፣ ደህንነቱ ተከርቼም እና ዛምራ የተሰኘ ልቦለድ ያበረከተልን ሲሆን የመጨረሻ ስራው ደግሞ በ አምሓራ ክልል ንፁሀን ህዝብ እና ሀገሪቱን እመራታለሁ በሚለው መንግስት መካከል ባለው አለመግባባት እንዲሁም በትግራይ ፣ በኦሮሚያእና በአማራ መካከል የሚሞቱትን ሰዎች በግልፅ ቋንቋ ግፉዓንበሚል ኢ ልቦለድ ድርሰት አቅርቦልናል። ከ መጋቢት 2010 ዓ.ም ወዲህ በሀገሪቱ ላይ እየታዬ ያለው ኢ-ፍትሐዊነትና የተበላሼ የመንግስት አስተዳደር የብዙ ንፁሀንን ህይወት እያሳጣን መሆኑን ይስማዕከ በ ግፉዓን ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል።
Hello,ሚሊዮን .
References:
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ይስማዕከ ወርቁ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.