ቡዲስም

ቡዲስም በጎታማ ቡዳ ትምህርቶች የተመሠረተ እምነት ነው። ይህም በ፮ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.

የኖረ የሕንድ አገር መስፍን ነበረ። ቡዲስም በካምቦዲያ እና በቡታን በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ነው።

ቡዲስም
ጎታማ ቡዳ ሃይማኖቱን ሲያስተምር

የቡዲስም መጀመርያ እንደ አንድ የሕንድ አገር ፍልስፍና ነበረ። በጎታማ ትምህርት የጽድቅ ኑሮ የሚይዙ ሰዎች ወደ ከፍተኛ ደረጃ ደርሰው ከሰምሳረ ወይም ከተመላሽ-ትስብዕት ማምለጥ፣ ከሕልውና ወደ «ኒርቫና» (ኢ-ሕልውና) ማምለጥ የሚፈለግ ዒላማ ነው። ስለ አምላክ ወይም ስለ እግዚአብሔር ግን አያስተምርም፤ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱት እንደ ጎታማ ቡዳ አማልክቱ ወይም «ቡዳዎች» ይባላሉ። ለቡዳዎችም ምስል ተቀርጾ መሥራትና የምስሎች አምልኮት እንደ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች (አስርቱ ቃላት) ኃጢአት ሳይባል፣ እንደ ጽድቅ ይቆጠራል፤ ይህም ልማድ የተገኘው በባክትሪያ (አፍጋኒስታን) ከታላቁ እስክንድር ዘመቻ ጀምሮ ከኖሩት ግሪክ-ቡዲስቶች ነበር። በዚህ ዓለም ሀዘን ከደስታ ጋር ሲፈራረቅ ለመንፈስ ወይም ነፍስ ሕልውና ባለውለታ በመሆን ፈንታ፣ ነፍስ የሚባለው ወይም ነጻ ፈቃድ ምታቶች ናቸው ይላሉ።

ከነዚህ ልዩነቶች በቀር፣ በተለይ ከአስርቱ ቃላት መጀመርያ 4 ቃላት ቢለዩም፣ በተረፈ ግን በአጠቃላይ ከመጨረሾች 6 ቃላት ጋር ይስማማሉ። በተለይም፦

  • «የባልንጀራህን ሀብት አትመኝ» - በቡዲስም ዘንድ ደግሞ መመኘትን ሁሉ ማጥፋት፣ እንዲሁም ገዳም ገብቶ መኖኩሴ መሆን እንደ ጽድቅ ነው።
  • «እናትህንና አባትህን አክበር» - በቡዲስም ደግሞ ቁም ነገር ነው፤ እንዲሁም ለችግረኞች ምጽዋትና ልግሥና ማድረግ ጽድቅ ነው።

ቡዲስም በእስያ አገራት ተስፋፍቶ ሁለት ዋና ክፍሎቹ ጤራቫዳ ቡዲስምና ማሃያና ቡዲስም ይባላሉ። በጤራቫዳ ቡዲስም ዘንድ፣ ሳንስክሪትና ፓሊኛ እንደ ተቀደሱ ቋንቋዎች ይቆጠራሉ።

ፓሊኛ በተለይ ለቡዲስም ፍልስፍና ጽሑፎች ለመጻፍ ከሳንስክሪት የተደረጀው የልጆች ቋንቋ ይመስላል፤ ስለዚህ እንደ ሳንስክሪት የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። የፓሊኛ ሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቃላት ድምጽ ወደ «ኒርቫና» ደረጃ እንደሚመራ ያምናሉ።

በቡዲዝም እምነት አስተምሮት መሠረት ፈጣሪ ሚባለውን አካል ከውስጥ መፈለግ እና በሁሉም ነገር ሊተካ የሚችል ነው!!

:

Tags:

ሕንድቡታንካምቦዲያየመንግሥት ሃይማኖትጎታማ ቡዳ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

የዓለም ዋንጫኤርምያስ ለገሰ ዋቅጅራኢንግላንድጉልባንዋናው ገጽ/ለጀማሪወች/መልመጃ ገጽ ፪መቅመቆበገናገብረ ክርስቶስ ደስታየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንሮቦትወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስፌስቡክወላይታስፖርትዴርቶጋዳወርቅእጸ ፋርስላትቪያዓለም-አቀፍ መደበኛ የመጽሐፍ ቁጥር13ኛው ምዕተ ዓመትየኢትዮጵያ እጽዋትምሳሌቅዱስ ሩፋኤልመለስ ዜናዊፀደይመፈንቅልኔዘርላንድአንዶራ ላ ቬላጦስኝአይን (ሥነ አካል)አቡነ ጴጥሮስመሐሙድ አህመድጂፕሲዎችአስራት ወልደየስአብዮትሴቶችሮበርት ሙጋቤሰርቢያፊልምዩ ቱብናስ ዘመንነጋሽቅዱስ ያሬድየጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርገብስቅዱስ ራጉኤልየአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤትተውሳከ ግሥግዕዝፍስሓ አጥላውሀብቷ ቀናአንጎልሰዓሊሞልዶቫባሕላዊ መድኃኒት2 Mayየተባበሩት ግዛቶችቀንድ አውጣአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)ሙላቱ አስታጥቄቅኝ ግዛትፍራፍሬየኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርጠጣር ጂዎሜትሪሀመርወይራኩላሊትታሪክአራት ማዕዘንL🡆 More