ጦስኝ (Thymus serpyllum) በኢትዮጵያ የሚበቅል እጽ ሲሆን ለተለያዩ የጤና መታወኮች እንደ መድሃኒት ያገለግላል።
እንደ ሻይ ቅጠል በማገልገል ሻይ ለማፍላት ያገልግላል።
በጦስኝ ወገን ብዙ ተመሳሳይ ዝርያዎች አሉ፣ በብዙ አገራት አበሳሰሎች እንደ ቅመሞች ይጠቀማሉ።
እንደ ቅመም፣ ጦስኝ ተደርቆ ተደቅቆ ከሌሎች ቅመሞች ጋር ተቀላቅሎ ለበርበሬና ለሽሮ ይጠቅማል።
ጨብጡ ለማከም እንደ ጠቀመ ተዝግቧል።
በሻይ ለጉንፋንና ለጉበት በሽታ ያከማል። አንዳንዶች እንደ ሲጃራ አጭሰውታል።
የቅጠሉና የአገዳው ሻይ ደግሞ ለስኳር በሽታ እንደ ተጠጣ ተዘገበ።
ደጋ
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጦስኝ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.