ጸደይ በአማርኛው በልግ፣ የበጋን ወራት ተከትሎ መጋቢት ፳፮ ቀን ይብትና እስከ ሰኔ ፳፭ ቀን ድረስ ከቀላል ዝናብ ጋር ይዘልቃል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ወይም በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ (የዘመን አቆጣጠር) መሠረት አንድ ዓመት በአራት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላል። ከነኚህ አንዱ ክፍል ወርኀ ጸደይ ነው።
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ጸደይ የሚለውን ቃል ሲያብራሩ «ዐጨዳ፤ ያጨዳ ወራት፤ ዘመነ በልግ፤ በወዲያ መከር፣ በወዲህ በልግ የሚደርስበት የሚታጨድበት፣ ወዲያውም የሚዘራበት ወርኀ ዘርዕ። ክፍለ ዓመት፤ ያመት ርቦ ፺፩ ቀን ወይም ፫ ወር በሐጋይና በክረምት መካከል ያለ ክፍል።
የወቅት ስም | የመግቢያው ቀን | የማለቂያው ቀን |
---|---|---|
መፀው (አበባ/መኸር) | መስከረም ፳፮ | ታኅሣሥ ፳፭ |
በጋ | ታኅሣሥ ፳፮ | መጋቢት ፳፭ |
ፀደይ (በልግ) | መጋቢት ፳፮ | ሰኔ ፳፭ |
ክረምት | ሰኔ ፳፮ | መስከረም ፳፭ |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ፀደይ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.