እግዚአብሔር: አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ

እግዚአብሔር የግዕዝ ቋንቋ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም እግዚእ ማለት ገዢ ወይም ጌታ ሲሆን፤ ብሔር ማለት ደግሞ ስብሰባ /ብሄር ወይም አገር ማለት ነው። የተሟላ ትርጉም ፡ የብሔር ገዢ ከሁሉ በላይ የሆነ ፡ ዓለምን የፈጠረ ፡ ብቸኛ አለቃ ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተጻፉት በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል በዕብራይስጥና በአረማይክ እንዲሁም የኋለኛው በግሪክ መሆኑ ይታወቃል። እግዚአብሔር በሚለው የግዕዝ ቃል የተተካው ስም በዋነኞቹ እና በመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች የፈጣሪን ስም የሚወክሉት አራት የእብራይስጥ ፊደላት (יהוה) ተጽፎ የነበረ ሲሆን አጠራራቸውም ዮድ ሄ ዋው ሄ ነው። በቀድሞ ዘመን ተነባቢዎች ብቻ የሚጻፉ ሲሆን አናባቢዎችን የሚጨምረው አንባቢው በመሆኑ በዘመናችን የእነዚህን አራት ፊደላት ትክክለኛ አነባበብ በእርግጠኛነት የሚያውቅ የለም። ሆኖም ወደ ትክክለኛው በእጅጉ የሚቀርቡ ሁለት የአማርኛ አጠራሮች ይገኛሉ። እነሱም ይሖዋ እና ያህዌህ የሚሉት ሲሆኑ በ1879 የአማርኛ ትርጉም መፅሓፍ ቅዱስ አንድ ጊዜ (ይሆዋ)፣ በ1941 ትርጉም ሁለት ጊዜ (ያህዌ) አንዲሁም በአዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ በርካታ ቦታ ላይ (ያህዌ) በሚል ተጽፈው ይገኛሉ።

ግዕዝ ፍልስፍና B-H-R (𐩧𐩢𐩨) የሚለው ሥር ብሔር ወይም ባሕር ከመስጠት በላይ ትርጉሙ ማናቸውም ባሕር ዓይነት፣ የዓለም፣ የሀሣብ፣ የድምጽ፣ የጠፈር፣ ወይም የመንፈስ ባሕር ቢሆን፤ ባሕሩ የባሕሩም ክፍሎች ሁሉ ወሰኖች እንዳሉባቸው በቀላል ሊገለጽ የሚችል ነው። እንግዲህ ወሰኖቹን የሚወስነው አወሳኝ ወይም ገዢው ኃይል «ብሔሩን የሚገዛ» ወይም በግዕዝ «እግዚአብሔር» በመባል ሊታወቅ ይቻላል። ይህ ላይኛ ፈቃድ ፈጣሪው ጸባይ የሰማዩ አባታችን ሲሆን ያለ እርሱ ረድኤት ምንም አለመቻሉን የሚል ግንዛቤ ነው። ስለዚህ የማናቸውም ተቃዋሚ ወይም ጋኔን ፈቃድ ቢኖር በእግዚአብሔር ፈቃድና ትግዕስት ብቻ ነው ስንኳ ለጊዜው ሊቃወሙት የሚቻለው (ኩፋሌ 10:5-7)።

Tags:

ግዕዝጠፈር

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ንዋይ ደበበአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)አሊ ቢራግብረ ስጋ ግንኙነትስብሃት ገብረእግዚአብሔርዓመት በዓላት እና ታሪካዊ ማስታወሻዎችማኅበረ ቅዱሳን2ኛው ዓለማዊ ጦርነትፕላቲነምሶቅራጠስክራርየኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራ19ኛው ክፍለ ዘመን የግራኝና የልብነ ድንግል ታሪክ በአማርኛቅዱስ ላሊበላአንሻንጤፍዓለማየሁ ገላጋይገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽመጽሐፈ ዕዝራ ካልዕወርቅ በሜዳየጊዛ ታላቅ ፒራሚድከበሮ (ድረም)ጉጉትአስናቀች ወርቁኤችአይቪኣቦ ሸማኔየሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንማርያምየወንዶች ጉዳይአለማየሁ እሸቴየሮበርት ሙጋቤ ቀልዶችየንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥሳንክት ፔቴርቡርግሴቶችረጅም ልቦለድዓለም-አቀፍ መደበኛ የመጽሐፍ ቁጥርየዮሐንስ ራዕይየልብ ሰንኮፍዋና ከተማመጽሐፈ ሲራክንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያወፍየኮንትራክት ሕግቀስተ ደመናየኢትዮጵያ ካርታ 1936ቦብ ማርሊሥነ ውበትአናናስጦጣሜሪ አርምዴቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴሞና ሊዛአሪደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅንየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንስእላዊ መዝገበ ቃላትቀይ ሽንኩርትእግር ኳስወሎብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትኢንግላንድገብርኤል (መልዐክ)ድሬዳዋአሸናፊ ከበደእባብየወታደሮች መዝሙርኢንጅነር ቅጣው እጅጉነጭ ሽንኩርትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክመጽሐፈ ሄኖክኦጋዴንሂሩት በቀለፕላቶየዓለም ዋንጫ🡆 More