ሼክስፒር

ዊሊያም ሼክስፒር (ታህሳስ ወር 1564 - ታህሳስ 23 ቀን 1616 እ.ኤ.አ.) በብዙወች ዘንድ ታላቁ የእንግሊዝኛ ጸሃፊ ተብሎ የሚገመት በእንግሊዝ አገር የኖረ ገጣሚ፣ ተውኔት ደራሲ፣ ድራማ አዘጋጅ ነበር። አብዛኛው ተውኔቶቹ ትራጄዲንና ታሪክን የተመረኮዙ ነበሩ። የኮሜዲ ጽሁፎችንም አቅርቧል። የግጥሞቹና ተውኔቶቹ አንኳር ሃሳቦች የሚያጠነጥኑት የፍቅር፣ ቅናት፣ ንዴትና መሰል ጠንካራ ስሜት ያለው ሰው ሰው ስለመሆን ናቸው። ሼክስፒር ጽሁፎቹን የመዘገባቸው በ1590 እና 1613 እ.ኤ.አ.

ሼክስፒር
ዊሊያም ሼክስፒር

ህይወት

ስለሼክስፒር ህይወት ብዙ የተመዘገበ ባይኖርም ሚስቱ አና ሃዘዋይ ትባል እንደነበርና ከርሱ በ5 ወይም 6 አመት ትበልጠው እንደነበር ይነገራል። ሼክስፒር 3 ልጆች ነበሩት፣ ሱዛና ሆል፣ ሃምነት ሼክስፒርና ጁዲት ቅኔይ ። በ1592 እ.ኤ.አ. ሼክስፒር ተዋናይ የነበረ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት በተውኔት ደራሲነቱ እውቅናን እያተረፈ የመጣበት ዘመን ነበር። በ1616 እ.ኤ.አ. ሲሞት ሼክስፒር አንዳቸውንም ጽሁፉን አላሳተመመ ነበር፣ ምክንያቱም አይታወቅም። ተውኔቶቹ የታተሙት ከሞተ በኋላ ነበር።

የሼክስፒር ታዋቂ ጽሁፎች

ትራጄዲወች

  • Romeo and Juliet
  • Macbeth
  • King Lear
  • Hamlet
  • Othello
  • Titus Andronicus
  • Julius Caesar
  • Antony and Cleopatra
  • Coriolanus
  • Troilus and Cressida
  • Timon of Athens

ኮሜዲወች

  • The Comedy of Errors
  • All's Well That Ends Well
  • As You Like It
  • A Midsummer Night's Dream
  • Much Ado About Nothing
  • Measure for Measure
  • The Tempest
  • Taming of the Shrew
  • Twelfth Night or What You Will
  • The Merchant of Venice
  • The Merry Wives of Windsor
  • Love's Labour's Lost
  • The Two Gentlemen of Verona
  • Pericles Prince of Tyre
  • Cymbeline
  • The Winter's Tale

ታሪካዊ

  • Richard III
  • Richard II
  • Henry VI, part 1
  • Henry VI, part 2
  • Henry VI, part 3
  • Henry V
  • Henry IV, part 1
  • Henry IV, part 2
  • Henry VIII
  • King John

የጠፉ ጽሁፎች

  • Love's Labour's Won
  • Cardenio

"ሼክስፕሪርን" ማን ጻፈው?

ሼክስፕሪ ከሞተ 150 ዓመት በኋላ ድርሰቶቹን እርሱ አልጻፋቸውም የሚል አስተያየት ብቅ አለ። ለዚህ ምክንያቱ ሼክስፒር ከእንግሊዝ ውጭ ብዙ ስላልተዘዋወረና በድርሰቶቹ ደግሞ ሌሎች አገሮችን፣ ለምሳሌ ጣሊያንን፣ ስፔንን ወዘተ በጥልቅ እንደሚዋቅ ስለሚያሳይ ነበር። ብዙ ተመራማሪወች የሼክስፒርን ድርሰቶች ሼክስፒር እንደጻፋቸው ቢያምንም አሁን ድረስ እርሱ አልጻፈውም የሚል ክርክር ይነሳል።

ዋቢ ጽሁፍ

Tags:

ሼክስፒር ህይወትሼክስፒር የ ታዋቂ ጽሁፎችሼክስፒር ሼክስፕሪርን ማን ጻፈው?ሼክስፒር ዋቢ ጽሁፍሼክስፒር1564 እ.ኤ.አ.1590 እ.ኤ.አ.1613 እ.ኤ.አ.1616 እ.ኤ.አ.ታህሳስ 23ታሪክእንግሊዝኛእንግላንድፍቅር

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ቆርኬላፕቶፕየአሜሪካ ፕሬዚዳንትየ1930 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫቆለጥጃፓንኛቅዝቃዛው ጦርነትየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንአዳልተስፋዬ ሳህሉአማኑኤል ካንትሶቪዬት ሕብረትሣህለ ሥላሴየወፍ በሽታየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትአፈ፡ታሪክሰሜን ተራራ19ኛው ክፍለ ዘመን የግራኝና የልብነ ድንግል ታሪክ በአማርኛMቃል (የቋንቋ አካል)ጉሬዛወደፊት ገስግሺ ውድ እናት ኢትዮጵያቤተ ማርያምሕግ ገባየተፈጥሮ ሀብቶችሰምና ፈትልቼክእያሱ ፭ኛእሪያመስመርማናልሞሽ ዲቦየቢራቢሮ ክፍለመደብባርነትኤፕሪልሳማዓሣጌሤምኧሸርሰንኮፉ አልወጣምመጽሐፈ ሄኖክሆሎኮስትጸሎተ ምናሴየአፍሪቃ አገሮችትዝታየዶሮ ጉንፋንአሰላየኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርኦሮሚያ ክልልየኦሎምፒክ ጨዋታዎችኔይማርየኢትዮጵያ ሕገ መንግስትሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃከንባታድመትካይ ሃቨርትዝህብስት ጥሩነህኪዳነ ወልድ ክፍሌሐረሪ ሕዝብ ክልልረጅም ልቦለድፒያኖከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርዋሽንትአዕምሮየኢትዮጵያ ካርታቫስኮ ደጋማሄክታርቤቲንግዓፄ ሱሰኒዮስጁፒተርሞዛምቢክኣደስ🡆 More