የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን (ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.) በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሥነምግባር መከታተያ ኮሚሽን ነው። የኮሚሽኑ ተጠሪነት በቀጥታ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዓሊ ሱለይማን ሲሆኑ ም/ኮሚሽነሩ ደግሞ ክቡር አቶ ወዶ አጦ ናቸው። ኮሚሽኑ «ሥነምግባር» (እንግሊዝኛ፦ Ethics) የተባለ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም መፅሄት እና «መስታወት» (እንግሊዝኛ፦ Insight) የተባለ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚወጣ ኒውስሌተር አለው።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን
የኮሚሽኑ ምልክት

አመሠራረት

እ.ኤ.አ. በ1996 በብሔራዊ ደረጃ የተጀመረው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የሥነምግባር ንዑስ ፕሮግራምን በውስጡ የያዘ ነበር። የስነምግባር ንዑስ ፕሮግራም አንድ ፕሮጀክት ኮሚሽኑን ማቋቋም ነበር። የፕሮጀክቱም ስም የስነምግባር መከታተያና ማዕከላዊ አካል ማቋቋሚያ ፕሮጀክት የሚል ነበር። በዚህም መሰረት የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ግንቦት 16 ቀን 1993 ዓ.ም. በአዋጅ ተቋቋመ።

መዋቅር

ኮሚሽኑ ዘጠኝ ዳይሬክቶሬቶችና ሁለት አገልግሎቶች አሉት። በተጨማሪም የኮሚሽኑን ውስጣዊ አሠራርን የሚከታተል የሥነምግባር መከታተያ ጽ/ቤት አለ። ይህም ጽህፈት ቤት በአቶ ሃረጎት አብርሃ ይመራል። የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እስከ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ድረስ 315 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 101 ሴቶች ናቸው።

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ይገኛል። በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተመረቀው በመጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ሲሆን በአሁኑ ወቅት 21 ሠራተኞች አሉት።

ዳይሬክቶሬቶች

ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
የሀብት ማሳወቂያ እና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት አቶ ግርማ ወርቁ
የሙስና ወንጀል ምርመራ እና ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት አቶ ገብሩ ገበየሁ
የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት አቶ አክልሉ ሙሉጌታ
የሥነ ምግባር ትምህርት እና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አቶ ብርሃኑ አሰፋ
የሥነ ምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት አቶ ብርሃኑ ክፈተው
የሰው ሀብት ሥራ አመራር አቶ መኮንን ዘገዬ
ዕቅድ፣ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት አቶ ሙላት ሸዋታጠቅ
የጥናት እና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ (ተጠባባቂ)
የኦዲት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አቶ ፋኖሴ ሀሰን

አገልግሎቶች

አገልግሎት ኃላፊ
የህግ አገልግሎት አቶ ብሌን ግርማይ (ተጠባባቂ)
ጠቅላላ አገልግሎት ጥላዬ የትዋለ

በጀት

ኮሚሽኑ ከመንግስት በ፳፻፪ ዓ.ም. 16.23 ሚሊዮን ብር፣ በ፳፻፫ ዓ.ም. 26 ሚሊዮን 93 ሺህ 930 ብር፣ በ፳፻፬ ዓ.ም. ደግሞ 34 ሚሊዮን 840 ሺህ ብር የተመደበለት ሲሆን ከሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት በየዓመቱ የሚያገኘው ገንዘብም አለ።

ማመዛገቢያ

የውጭ መያያዣ

Tags:

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመሠራረትየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መዋቅርየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በጀትየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማመዛገቢያየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የውጭ መያያዣየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንኢትዮጵያእንግሊዝኛ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ታላቁ እስክንድርፋኖየአፍሪቃ አገሮችሜትርሣህለ ሥላሴአክሊሉ ለማ።ድንቅ ነሽስፖርትየልብ ሰንኮፍየወባ ትንኝዓረፍተ-ነገርቤተ መድኃኔ ዓለምባቲ ቅኝትየጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማጎንደር ከተማየሰው ልጅ ጥናትአሰላአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነትሄሮይንክርስቶስ ሠምራየወታደሮች መዝሙርዝሆንፈሊጣዊ አነጋገር አወዳጄ ልቤኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንጋምቤላ (ከተማ)ኤፕሪልሥራእቴጌ ምንትዋብነብርውሃዝግመተ ለውጥመሬትሰምና ፈትልኦሮማይሼክስፒርስእላዊ መዝገበ ቃላትእንቆቅልሽየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንመሐሙድ አህመድ1960 እ.ኤ.አ.ተስፋዬ ሳህሉየስልክ መግቢያየአውርስያ ዋሪእሪያማሲንቆቅፅልየደም መፍሰስ አለማቆምየተባበሩት የሀገር ንጉሳዊ አገዛዝአዳም ረታጊዜዋወገርትአቡነ ሰላማሀዲያዮሐንስሰዶምየአድዋ ጦርነትእስራኤልሲዳምኛመጽሐፈ ጦቢትሰርቨር ኮምፒዩተርዐምደ ጽዮንጥሩነሽ ዲባባበላይ ዘለቀጅቡቲ (ከተማ)ጉራጌክርስትናዲ ኤን ኤሃይማኖትበ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችበላ ልበልሃ🡆 More