አብርሐም

አብርሃም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በዑር ከላውዴዎን አብራም ተብሎ ተወልዶ በኋላ ወደ ካራንና ወደ ከነዓን ግብፅም የሄደው የዕብራውያንና፣ የእስማኤላውያን የብዙ ሕዝቦች አባት ነበረ።

አብርሃም
አብርሐም
ሥላሴ በአብርሃምና በሳራ ቤት እንደተስተናገዱ

ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚገኝ የመስኮት ሥዕል አዲስ አበባ
የብዙ ሕዝብ አባት
የመጀመሪያ ስሙ አብራም በኋላ አብርሃም
አባቱ ታራ
ባለቤቶቹ ሳራ
አጋር ዕቁባቱ
በመጨረሻም ኩትራ
ልጆቹ እስማኤል
ይስሐቅ
ዝምራን
ጆክሻን
ሜዳን
ሚዲያን
ኢሽባክ
ሹሃ
ወንድሞቹ ሃራን
ነሆር
የአጎቱ ልጅ ሎጥ
የትውልድ ቦታ ዑር ከላውዴዎን
ያረፈበት ቦታ ኬብሮን
ያስከተለው የአይሁድ ክርስትናና እስልምና ሃይማኖት
አብርሐም
አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ሊሰዋ ሲል


የአብርሃም ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ አብርሃም ሕይወት ብዙ ምዕራፍ ይሰጣል።

የአብርሃም ዕድሜ በመጽሐፈ ኩፋሌ

  • 1876 ዓመተ ዓለም (ዓ.ዓ.) - አብራም ለአባቱ ታራ እና ለእናቱ ኤድና በዑር ከላውዴዎን ተወለደ።
  • 1886 ዓ.ዓ. - ሦራ (በኋላ ሣራ) ተወለደች (?)።
  • 1891 ዓ.ዓ. - አብራም ወጣት ሆኖ በከብት የሚስብ ማረሻ ፈጠረ።
  • 1903 ዓ.ዓ. - አብራም አባቱን ታራን በጣኦታት ለምን ታምናለህ ብሎ ጠየቀው።
  • 1925 ዓ.ዓ. - አብራም ሦራንን አገባት።
  • 1932 ዓ.ዓ. - ሎጥ ተወለደ።
  • 1936 ዓ.ዓ. - አብራም የዑርን አረመኔ መቅደስ አቃጠለና ወደ ካራን ሸሸ።
  • 1950 ዓ.ዓ. - የሰናዖር ንጉሥ አምራፌልና የኤላም ንጉሥ ኮሎዶጎምር የሰዶምን አካባቢ በከነዓን ያዙ።
  • 1951 ዓ.ዓ. - እግዚአብሔር አብርሃምን ባረከው፣ አብርሃምም ሰማያዊ ቋንቋ ለመማር ጀመረ።
  • 1953 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከካራን ወደ ከነዓን ተጓዛ።
  • 1954 ዓ.ዓ. - ኬብሮን በከነዓን ተሠራ።
  • 1956 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ግብፅ ሄደ።
  • 1961 ዓ.ዓ. - ጣይናስ በግብጽ ተሠራ።
  • 1963 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ከነዓን ወደ ቤቴል ተመለሰ። ሰዶም በኤላም ላይ አመጸ።
  • 1964 ዓ.ዓ. - የነገስታት ጦርነት፦ የአብርሃም ሠራዊት አምራፌልን ወዘተ. አሸነፉ። አብርሃምም በምላሽ ስንኳ አንዳችም ሲባጎ ከሰዶም ንጉሥ እንዳይወስድ አሻፈረኝ ነገረለት ። መልከ ሴዴቅ አብርሃምን ባረከው።
  • 1965 ዓ.ዓ. - እስማኤል ተወለደ።
  • 1979 ዓ.ዓ. - እሳት ከሰማይ ወርዶ ሰዶምንና ገሞራን አጠፋ። አብርሃም ወደ ቤርሳቤ ሄደ፣ ይስሐቅ ተወለደ።
  • 1982 ዓ.ዓ. - እስማኤልና እናቱ ሀጋር ወደ ፋራን ምድረ በዳ ተሰደዱ።
  • 2003 ዓ.ዓ. - አብርሃምና ይስሐቅ ወደ ደብረ ጽዮን ተጓዙ፤ ወደ ቤርሳቤ ተመለሱ።
  • 2010 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከቤርሳቤ ወደ ኬብሮን ተመለሰ።
  • 2024 ዓ.ዓ. - ሣራ ዐረፈች፤ ለመቃበርዋም አብርሃም ዋሻ ከኬጢያውያን ሰው ከኤፍሮን ገዛ።
  • 2027 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ርብቃን አገባት፣ አብርሃምም ከጡራን አገባት።
  • 2046 ዓ.ዓ. - ያዕቆብና ኤሳው ለይስሐቅ ተወለዱ።
  • 2060 ዓ.ዓ. - አብርሃም አረፈ።
:

Tags:

መጽሐፍ ቅዱስከነዓን (ጥንታዊ አገር)ካራንዑር ከላውዴዎንግብፅ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ኣበራ ሞላድልጫደበበ እሸቱስቅለት (የማይክል አንጄሎ ቅርጽ)ገንዘብየዓለም የህዝብ ብዛትጣልያንፕላቶውሻአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭማህበራዊ ሚዲያበእንግሊዝ የሚገኙ የእግር ኳስ ሜዳዎች ዝርዝርየምኒልክ ድኩላህንድመጽሐፈ ሲራክመስተዋድድየተፈጥሮ ሀብቶችአለቃ ገብረሐና እና አስቂኝ ቀልዶቻቸውሊቨርፑል፣ እንግሊዝየሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንአንሻንየሰው ልጅስታምፎርድ ብሪጅ (የእግር ኳስ ሜዳ)ኢትዮ ቴሌኮምትንሳዔመንፈስ ቅዱስስልጤፈላስፋቴወድሮስ ታደሰፖለቲካአርባ ምንጭኣለብላቢትአለቃ ገብረ ሐናየኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክለድካም የጣፈኝ ብነግድ አይተርፈኝጊልጋመሽየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችሸለምጥማጥሙቀትየሥነ፡ልቡና ትምህርትፈሊጣዊ አነጋገር ገጤፍግሥላፀሐይየባቢሎን ግንብኤርትራገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችፕላኔትጥምቀትደራርቱ ቱሉሽፈራውሴምወንዝእያሱ ፭ኛየዓለም ዋንጫቀስተ ደመናንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያአበበ ቢቂላህዝብኮልፌ ቀራንዮዳጉሳኤሌክትሪክ ምድጃ ፡ እራስህ ስራጴንጤኦሮሞማሲንቆስብሃት ገብረእግዚአብሔርአማርኛትዝታፕሮቴስታንትክራር2ኛው ዓለማዊ ጦርነትኢንግላንድጌሾ🡆 More