ሉዊ ፓስቴ (Louis Pasteur) (1815 – 1888 ዓ.ም.) ፈረንሳያዊ የረቂቅ ህዋሳትና የኬሚስትሪ ሊቅ ነበሩ። እሳቸውና ሚስታቸው ማሪ ፓስቴ በተለይ በበሽታዎች ጀርም ቲዎሪ ስላደረጉት ሙከራዎች ይታወቃሉ። እንዲሁም በክትባት ስለ መስራታቸው ይታወቃል። በተለይም በውሻ በሽታ የሚከላከል መጀመርያው ክትባት በማግኘቱ ስመ ጥሩ ናቸው። በኬሚስትሪ በኩል የቡረሌ ኢምጥጥናዊ አቀራረጽ አሳወቁ። ከዚህም በላይ ወተትና ወይን ጠጅ ቶሎ እንዳይበላሽ ዘዴ አገኙ። ይህም ሂደት ፕስተራ (pasteurization) ይባላል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ሉዊ ፓስቴ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.