ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍና የመንግሥት ሰው ነበሩ።

ፊታውራሪ  ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም
ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም

ለጊዜ የጅጅጋ እና የጨርጨር በአገረ ገዥነት ካገለገሉ በኋላ፣ በጅሮንድ (በኋላ ፊታውራሪ) ተክለ ሐዋርያት በ1923 ዓም ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ደራሲዎች ዋናው ሆኑ። አጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጻፉት ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ውስጥ አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ፴ «የሕገ መንግሥትን ትርጓሜ ስለ ማስረዳት።» በሙሉ ከበጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት ቃላት ጠቀሱዋቸው። በዚህም ሰዓት ለጥቂት ወሮች በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው አገለገሉ። ለጊዜም የኢትዮጵያ መላክተኛ በብሪታኒያ ሆነዋል።

ጥቅስ

ሕይወቴና ምዕራፍ ፴ ጠቃሚ የሆነ አጭር ጥቅስ ይከተላል፦

«ሰው እንዲጠቀምበት የሚፈቀድለት ነገር ሁሉ የጥቅም መብት ተብሏል። ይኸውም የጥቅም መብት በሁለት ዋና ክፍል ይለያያል።

    ፩ኛ ፡ የግል ጥቅም ለያንዳንዱ ሰው በነፍስ ወከፍነት ለየራሱ የሚሆን ነው።
    ፪ኛ ፡ የመተባበር ጥቅም ለሕዝቡ ሁሉ በሙሉ ለኢትዮጵያም ለአንድነትዋ የሚሆን ነው።
    የግልም የመተባበርም አሳብ በሦስት ዓይነት ሊሆን ይችላል።
    ፩ኛ ፡ የትዳር ጥቅም (ሀብት)
    ፪ኛ ፡ የአእምሮ ጥቅም (ዕውቀት)
    ፫ኛ ፡ የልቡና ጥቅም (ፍቅርና ሃይማኖት)

«ለነዚህ ለተነገሩት በግልም በመተባበርም ለሚሆኑት ጥቅሞች ሁሉ ለደምሳሹ አሳብ ጃንሆይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሕግ ሰጥተዋል። ዝርዝር ለሚሆነው አሳብ ግን አማካሪዎች በምክር ቤት በጉባኤ እያሰናዱ እንዲያቀርቡላቸው ከላይ እንዳሳየነው የመንግሥት አቋቋም መሠረት ሕገ መንግሥት የተባለውን ተክለዋል።»


Tags:

ኢትዮጵያ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ካናዳ2004ድኩላፊታውራሪአፋር (ብሔር)መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕኔዘርላንድሥርዓትቴወድሮስ ታደሰመንግስቱ ኃይለ ማርያምደምስታምፎርድ ብሪጅ (የእግር ኳስ ሜዳ)ሐሙስቁርአንስዊዘርላንድጋሞጐፋ ዞንአፕል ኮርፖሬሽንአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስአባይ ወንዝ (ናይል)ፖከሞንሰጎንየኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክፍትሐ ነገሥትጅቡቲ (ከተማ)ባርነትጅቡቲግሥዛጔ ሥርወ-መንግሥትአስናቀች ወርቁሞና ሊዛቀለምሴምየጋብቻ ሥነ-ስርዓትእግር ኳስስንዴበዴሳደብረ ዘይትባሕላዊ መድኃኒትየዮሐንስ ወንጌልብሳናመሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲዓለማየሁ ገላጋይቢልሃርዝያአያሌው መስፍንቀልዶችአክሱም መንግሥትጋሊልዮንግድጎልጎታገበጣደብረ ታቦር (ከተማ)1996ሊቨርፑል የእግር ኳስ ክለብየምድር እምቧይጉራጌትግራይ ክልልጉልባንፋሲካሻሜታየአሜሪካ ብሔራዊ ጦርነትእስፓንያኒንተንዶሀብቷ ቀናየአስተሳሰብ ሕግጋትስነ አምክንዮሶቅራጠስሸለምጥማጥሽፈራውሚያዝያ 27 አደባባይበ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትውዳሴ ማርያምጤፍፈሊጣዊ አነጋገርግሸን ደብረ ከርቤ ማርያምእየሩሳሌም🡆 More