ሥልጣኔ ማለት የሠለጠነ ባህል ወይም ኅብረተሠብ ነው። ይህም ምን ማለት እንደ ሆነ ለመግለጽ በታሪክ ልዩ ልዩ ሀሣቦች ቀርበዋል። ባጠቃላይ የሠለጠነ ትርጉም በአማርኛ በጥበብ፣ በባለሙያነት ወይም በዕውቀት የተመጠነ የተለመደ ማለት ነው። የስልጣኔ ተቃራኒ አንትረቢ፣ አውሬነት ወይም ነውር ተብሏል።
አልቤርት ሽቫይፀር በ1915 ዓም በጻፈው «የሥልጣኔ ፍልስፍና» (ዘ ፊሎሶፊ ኦቭ ሲቪላይዜሽን)፦ «በያንዳንዱ ሙያ፣ ከያንዳንዱም አስተያየት፣ በሰው ልጅ የተደረገው እርምጃ ሁሉ ድምር ነው፣ ድምሩ የእርምጃ ሁሉ እርምጃ ሆኖ ወደ ግለሠቡ መንፈሳዊ ፍጻሜ እስከሚረዳው ድረስ።» በማለት «ስልጣኔ»ን አስተርጒሟል። በአጭሩ፣ ወደ መንፈሳዊ ፍጻሜ የሚመራው የሰው ልጅ እርምጃ ሁሉ ድምሩ ሥልጣኔ ሊባል ይችላል።
ላለፉት ጊዜዎች እርምጃ፣ ብዙ ጊዜ «ስልጣኔ» እንደ «ባህል» ወይም «ኅብረተሠብ» በመለዋወጥ ለማናቸውም ሊወከል ይችላል፤ ለምሳሌ «የማልታ-ቡረት ሥልጣኔ» በቅድመ ታሪክ በሳይቤሪያ ተገኘ፤ ወይም የማያ ሥልጣኔ ከ2000 ዓክልበ. እስከ 1690 ዓም ድረስ በዩካታን፣ ሜክሲኮ አካባቢ ቆየ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ሥልጣኔ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.