ተቃራኒ

ተቃራኒዎች ማለት የማይጣጣም ሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ነገሮች ማለት ነው። በለት ተለት ልማድ፣ ሁለት ነገሮች ወይንም ቃላቶች ተቃራኒ ናቸው ሲባል፡ ተቃርኖዋቸው ካላቸው ዝምድና አንጻር ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ የድመት ተቃራኒ አይጥ ይሆናል። ሌላኛው ዓይነት ተቃርኖ፣ ሁለት ሆነው፣ ግን ከሁለት አንዱ ብቻ ባንድ ጊዜ ሊሆን ሲችል ይሆናል። ለምሳሌ የመግፋት ተቃራኒ መሳብ እንደሆነ። ሦስተኛው የመቃረን አይነት ቀስ ብሎ በሚቀያየር ባህርይ ላይ ጫፍና ጫፍ የያዙ ሁለት ነገሮች ማለት ነው። ለምሳሌ ሙቅና ቀዝቃዛ ተቃራኒ እንደሆኑ ነገር ግን በመካከላቸው የተለያየ የሙቀት ዓይነት እንዳለ ማለት ነው።

በተለምዶ የሚሰራበት የተቃርኖ ሃሳብ፣ ለዕለት ተለት ንግግርና ግንዛቤ ቢረዳም፣ ለፍልስፍና እና ለሂሳብ ለመሳሰሉ ዕውቀቶች ግን የማምታታት እና የማደናቀፍ ችግር ይፈጥራል። ስለሆነም ከዘመናዊ ሥነ አምክንዮ አንጻር፣ ተቃርኖ ማለት መጣረስ ማለትን ይወክላል። በሌላ አነጋገር፣ የአንድ ነገር ተቃራኒ፣ ያ ነገር ያልሆነ የሚል ትርጓሜን ይይዛል። ስለሆነ የድመት ተቃራኒ፣ ድመት ያልሆነ ነው ማለት ነው። በዚህ አስተሳሰብ፣ ድንጋይ ድመት ስላልሆነ፣ አይጥ ብቻ ሳይሆን ድንጋይም የድመት ተቃራኒ ነው ይባላል። የሙቅ ተቃራኒ ሙቅ ያልሆነ ስለሆነ፣ ለምሳሌ ሰማያዊ ቀለም ሙቅ ስላልሆነ ሰማያዊ የሙቅ ተቃራኒ ነው ይባላል።

Tags:

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

የኣማርኛ ፊደልወላይታየወላይታ ዘመን አቆጣጠርአበበ በሶ በላ።ይስማዕከ ወርቁአዲስ ኪዳንልብነ ድንግልየፈጠራዎች ታሪክፕላቶእባብሰሜን ተራራየዮሐንስ ወንጌልጉግልቶማስ ኤዲሶንኅብረተሰብቤተ ጎለጎታቢዮንሴቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅአሕጉርክርስቶስኩሻዊ ቋንቋዎችቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያሻይግራዋዝሆንጾመ ፍልሰታቅዱስ ጴጥሮስቅዱስ ገብርኤልመለስ ዜናዊየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንተረት ሀገበያእንግሊዝኛፀሐይህግ አስፈጻሚየእብድ ውሻ በሽታኢያሱ ፭ኛሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴየሥነ፡ልቡና ትምህርትአጥናፍሰገድ ኪዳኔሚያዝያጋብቻየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርየኢትዮጵያ ወረዳዎችየበዓላት ቀኖችሚላኖባሕላዊ መድኃኒትወይራሰንበትአበበ ቢቂላትግራይ ክልልሞስኮፕሩሲያሊቢያኦሮሚያ ክልልመካከለኛ ዘመንየዓለም ዋንጫስልጤየሐዋርያት ሥራ ፰ቤተ አባ ሊባኖስሽኮኮአኩሪ አተርቀንድ አውጣየወባ ትንኝደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅንሙሴድኩላውክፔዲያጌዴኦ🡆 More