ጓጉንቸር የአምፊቢያን ዓይነት እንስሳ ስትሆን በውሃ አካባቢ ኑሮዋን ትመራለች። ከእንቁራሪት እና ጉርጥ ይልቅ ሰውነቷ የለሰለሰ ነው። የኋላ እግሮቿም ረዣዥም ስለሆኑ ከመራመድ ይልቅ መዝለል ማለት ይቀናታል።
?ጓጉንቸር | ||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|
የዛፍ ጓጉንቸር | ||||||||
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||
| ||||||||
የጓጉንቸሮች ስብጥር ካርታ |
ጓጉንቸር፣ እንደማንኛውም አምፊቢያን፣ በውሃ ውስጥና እና በደረቅ ምድር ላይ መኖር ትችላለች። የሆኖ ሆኖ ጓጉንቸር ጨው ባለበት ውሃ፣ ለምሳሌ በውቅያኖስ ውስጥ መኖር አትችልም፤ ትሞታለች።
ጓጉንቸርን መግድል ጠንቅ አለው፤ ምክንያቱም ጓጉንቸር በሽታ አስተላላፊ ትንኞችን ስለምትመገብ፣ እርሷ ስትሞት፣ እንደ ወባ አስተላላፊ ያሉ ትንኞች በብዛት መራባት ይችላሉና። ስለሆነም፣ የጓጉንቸር መኖር ጥቅሙ ከፍተኛ ነው።
በዘመናዊ ሥነ ሕይወት ረገድ፣ ክፍለመደቡ ሁሉ «ጓጉንቸር» ተብሏል፤ ከዚህም ውስጥ ብዙ አስተኔዎች በተለመደ «እንቁራሪት» እና ከነርሱም አንዱ አስተኔ «ጉርጥ» ይባላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጓጉንቸር, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.