ኤሌክትሪካል ምህንድስና፣ ኤሌክትሪካል ኤንጂነሪንግ በመባል የሚታወቀዉ የምህንድስና ክፍል ስለ ኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ ኤልክትሮ-መግነጢዝምነት የሚያወሳ የትምህርት የትግበራ ዘርፍ ነው። ይህ የምህንድስና ክፍል ተለይቶ የተጠራዉ እንደ ቴሌግራፍ ፤ ስልክ እና የኤልክትሪክ ኀይል ጥቅም ተገኝቶ ትግበር ላይ ከዋለ በኋላ ነዉ፤ ወደ ታሪኩ ስንመጣ ኤሌክትሪሲቲ ኮረንቲነት በሳይንሳዊ አስተሳሰብ መታሰብ ምንአልባትም ዊሊያም ጊልበርት ስታቲካሊ ቻርጅድ(የማይለዋወጥ የሀይል ሙል) የሆኑ ቁሶች የሚለይ መሳሪያ በመፈልሰፉ ነው። ከ1830ዎቹ ጀምሮ የቴሌግራፍ ጥቅም ላይ መዋል ሙከራ ተደርጎም መሳካት ዐለምን ወደ ፈጣን ግኑኝነት እንዳስገባዉ ይታመናል።
የሚከተሉትን በዘርፉ ልብ ይሏቸዋል፣ ባትሪ (የኀይል ሙል)፤ የኀይል ፍሰት ጥርቅም እና ማስተላለፊያው፤ ኤሌክትሮ መግነጢዝም፤ ተለዋዋጭ የማይለዋወጥ የኀይል ፍሰት፤ ትራንስፎርመር፤ ሞተር፤ ራዲዮ፤ መስመር አልባ ግንኙነት፤ ሞገድ፤ የጨረር ቱቦዎች፤ ቴሌቪዥን፤ ቫኪዉም ቱቦዎች፤ ትራንዚስተሮች፤ የተቀናጁ ሽቦዎች፤ ፕሮሰሰሮች፤ አስተላላፊዎች ተቀባዮች፤ መንሰላስል(ኮምፒውተር)… የኀይል ምህንድስና Power Engineering፤ የመቆጣጠር ምህንድስና Control Engineering፤ ኤሌክትሮኒክስ Electronics፤ የመረጃ ትንተና Signal Processing፤ የግንኙነት ምህንድስና (Tele) Communication Engineering ፤ የመሳሪያዎች ምህንድና Instrumentation Engineering ፤ የመንሰላስል ምህንድስና Computer Engineering፤ እንዲሁም ኤሌክትሮ መካኒክስ፣ ስነህይወት Mechanotronics, Biomedics,…
ከዘርፉ ተያያዥነት ካላቸዉ ታዋቂ ሊቆች መካከልም ዊሊያም ጊልበርት፣ ቮልታ፤ ፋራዳይ፤ ኦህም፣ ማክስዌል፤ ኤዲሰን፤ ስታንሌይ፤ ቴስላ፤ ስቴይንሜትዝ፤ ዶቦሎቮሎስኪይ፤ ሀርትዝ፤ ማርኮኒ፤ ፍሌሚንግ፤ ሾክሌይ፡ ይጠቀሳሉ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ኤሌክትሪክ ምህንድስና, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.