ህዋስ (እንግሊዝኛ ሴል) መሰረታዊ የሆነ የህይወት ትንሹ ክፋይ ነው። ሴል በሰወነታችን ውስጥ የሚገኝ ፍጥረት እና ሰውነታችንን ለመገንባት የሚያስፈልግ ነገር ነው። ሴል የሚለው ቃል የመጣው ሴሉላ cellula ከተሰኘ የላቲን ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ትንሽ ክፍል ማለት ነው።
ሕዋስ የሕይወት መሠረት ነው፡፡እንደ ባክቴሪያ፣ ኘሮቶዞዋ እና እርሾ ያሉት ባለአንድ ሕዋስ ዘአካላት አንድ ሕዋስ ብቻ አላቸው፡፡ይህ የህይወት ያላቸው ነገሮች መስራች ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ሮበርት ሁክ በተባለ እንግሊዛዊ ሳይንቲስት ነበር።
በባለብዙ ሕዋስ ዘአካል(organism) ውስጥ የተለያዩ ሕዋሶች የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በተግባር የሚመሳሰሉ ሕዋሳት ሕብረ ሕዋስ በመፍጠር ተመሳሳይ ተግባር ያከናውናሉ፡፡ምሳሌ የጡንቻ ህብረ ህዋሳት ተመሳሳይ ተግባር ይፈፅማሉ፡፡ እንዲሁም የሸንዳ ሕብረ ሕዋስ አንድ አይነት ተግባር አላቸው፡፡
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ህዋስ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.