የኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነት

የኦጋዴን ጦርነት እየተባለ የሚታወቀው የ1977 እ.ኤ.አ./1978 እ.ኤ.አ.

የሶማሊያ መንግስትና ሕውሃት

የዚያድባሬ መንግስትና የሕውሃት ግንኙነት በጊዜው የሕወሓት አባል የነበረውን አሰገደ ገ/ስላሴን እንዲህ ጻፈ « ከሶማሌ መንግሥት ጋር ግንኙነት የተጀመረው ሕወሓት ሱዳን ውስጥ ጽ/ቤቷን ከከፈተችበት ከ1969 መጨረሻ ጀምሮ ነው። የግንኝነቱ አመሰራረት የተጀመረው ሱዳን ውስጥ ከነበረው የሶማሊያ ኤምባሲ ሲሆን፤ጥቂት ሳይቆይ ከሶማሊ መንግሥት ጋር በቀጥታ ግንኙነቱን መሠረተ። ግንኙነቱ እንደተመሠረተ ማንኛውም የውጭ አገር ግንኙነትና እንቅስቃሴ፤የወያኔ አባሎች ወደ ውጭ አገር ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ በሶማሌ ዜግነትና የሶማሌዎች ስም የያዘ ቪዛ እና ፓስፖርት በመያዝ ነበር የሚንቀሳቀሱት። የሶማሌ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በሃይለኛ ጦርነት ተወጥሮ እያለ፤መሳርያ እንደሚያስፈልገውና በዛ ሃይለኛ ውግያ የመሳርያ ቁጠባ ማድረግ እንዳለበትና በችግር እንደተወጠረ እያወቀም ቢሆን ለህወሓት ያደረገው ዕርዳታ ወደር ለውም። በጥቂቱ የሚተለው ነው።

1- ሁሉም የወያኔ መሪዎችም ሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ ለማስፋትና ለማጠናከር የሚላኩ ከፍተኛ የወያኔ ካድሬዎች ወደ አውሮጳ፤አሜሪካና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ሲንቀሳቀሱ ሰላማዊ የዜግነት ዓለም ዓቀፍ ሕጋዊ የመንቀሳቀሻ ሰነድ መያዝ ስለሚኖርባቸው፤ ወደ 50% የሚጠጉ የወያኔ የማዐከላዊ ኮሚቴ አባሎች እና ካድሬዎች የሶማሌ ባለሥልጣኖች / ቪ አይ ቪ/ ቪዛ ተሰጥቶአቸው ስማቸውን ቀይረው በመላው ዓለም እንዲንቀሳቀሱበት የሚያስችላቸው በመፍቀድ በውጭው ዓለም ያለ ምንም ችግር ትልእኮአቸው እንዲያከናውኑ ከፍተኛ አስዋጽኦ አድርጓል።

2- ከ15 በላይ የሚሆኑ የወያኔ ታጋዮች ምግባቸው፤መኝታቸው፤ወጪአቸውና አስፈላጊው በጀት ሁሉ የሶማሌ መንግሥት በመሸፈን አለ የተባለ የከባድ ብረት ማሣሪያዎች፤መድፎች፤ታንኮች፤ሞርታሮች፤ዓየር መቃወሚያ -ሚሳይሎች ታንከኛ፤እና ሁሉም ዓይነት ያካተተ ፀረ ታንክ ፤ፀረ ተሽከርካሪ፤ፀረ ሰው ፈንጂ ለረዢም ጊዜ አሰልጥለውልናል። (ገጽ 144) ለምሳሌ እነ ጀላኒ ወዲ ፈረጅ፤ እነ ገብረ ሓፂን፤ብርሃነ አርብጂ የመሳሰሉት ታጋዮች ለአንድ ዓመት ሙሉ 12 ሰዎች ሶማሌ ሄደው ማንኛውንም ዓይነት ከባድ መሳርያ ሰልጥነው ለድርጅቱ ከባድ መሳርያ ስልጠና ወሳኝ ሚና የተጫወተው ይኸኛው ክፍል ነበር(ገጽ18)።

3- እነኚህ ሶማሌ ውስጥ የሰለጠኑ ታጋዮች ወደ ትግራይ ሜዳ በመመለስ የወያኔ ታጋዮችን በሰለጠኑበት የዘመናዊ ከባድ መሳርያዎች ስልጠና አሰልጥነው በርከት ያሉ የከባድ ብረት መሳሪያ ተኳሽ በታሊዮን ቡድን ማነፅ ተጀመረ።

4- የሶማሌ መንግሥት ህወሓት ከውጭ አገር አምባሳደሮች ጋር እንደ አንድ ራሱን የቻለ አገር ተደርጎ እውቅና እንዲያገኝ በማለት ሶማሊያ ዋና ከተማ መቃዲሾ ከተማ ውስጥ እንደማንኛቸውም አገሮች ወያነ ትግራይም ኤምባሲ ጽ/ቤት ተከፍቶለት ከተቀሩት የመላ ዓለም አገሮች አምባሳደሮች ጋር ጎን ለጎን በማስቀመጥ እንዲታወቅ አጽተዋጽኦ አድርጓል።

5- ህወሓት የሶማሌ መንግሥት የሰጠውን ሰፊ የመንቀሳቀስ ዕድል ተጠቅሞ አስፋሃ ሓጎስ የሚባል የወያኔ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ከመላው ዓለም ጋር ለመገናኘት የሚያስችለው የራዲዩ ግንኙነት መስመር በመዘርጋት ከነረዳቶቹ ጋር ሶማሌ ውስጥ አስፈላጊው ግንኙነት ማድረግ ቻለ።


6- ያ ሶማሊያ ውስጥ አምባሲ ተከፍቶለት የነበረው የወያነ ትግራይ አምባሳደር ጽ/ቤቱን እንደ የዘመቻ መምሪያ (ቤዝ/መዋፈሪ) በመጠቀም የደርግን የዕለት ተለት ሁኔታ ዘገባ በማግኘት ብዙ ሥራዎችን እንዲከናወኑ ትልቅ ዕርዳታ አድርገውልናል።

7- ህወሓት ከቻይና መሣርያዎችን በመግዛትም ሆነ የግዢውን ገንዘብ ማስተላለፍ በኩል ሶማሌዎች ዕርዳታ አድርገዋል። መሣሪያዎቹ ከቻይና ተጭነው ወደ ሶማሌ ካቀኑ በሗላ ጭነቱን ተመልሰው የሶማሊ መኮንኖችና ሠራዊቶች እስከ ፖርትሱዳን በመሸኘት ያስረክቡን ነበር። ያ በጥቁር ገበያ /ኮንትሮባንድ ግዢ የተገኘው መሣርያ ግን በጋህዲ ቁጥር 1 እንደገለጽኩት ሻዕቢያዎች ሆን ብለው በሌብነት ዘርፈውታል። “ሆኖም ተጀምሮ ደርግ እስከ ተደመሰሰበት ድረስ በሕግም በኮንትሮባንድም በሶማሌ ስም ከውጭ ዓለም መሳርያ እየተገዛ በኤርትራ በኩል ይተላለፍልን ነበር። ሶማሌ ያደረገልን ዕርዳታ መተኪያ የሌለው ነበር።(ገጽ 16)

8- ለምሳሌ በሶማሌ ቪዛ ዜግነታቸው “ሶማሊያዊ” ተብለው በሶማሊ ቪዛ ሲጠቀሙ ከነበሩት

1- ግደይ ዘርአፅዮን

2- ስብሓት ነጋ

3- አስፋሃ ሓጎስ

4- አደም

5- ካሕሳይ በርሀ/ዶክተር ምስግና

- 6- ገብረመድህን መሐመድ ያሲን

- 7- ሥዩም መስፍን

- 8- መለስ ዜናዊ

- 9- ወረደ ገሠሠ

- 10- ጃማይካ ኪዳነ

- 11- ፀጋይ ጦማለው እና ብዙ በርከት ያሉ ታጋዮችና መሪዎች ነበሩ።

- -

Tags:

1977 እ.ኤ.አ.1978 እ.ኤ.አ.ሶማሊያሶቪየት ህብረትአሜሪካኢትዮጵያኦጋዴን

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

የፀሐይ ግርዶሽውቅያኖስግራዋኢንዶኔዥያዓረብኛየሒሳብ ምልክቶችየሐበሻ ተረት 1899ቃል (የቋንቋ አካል)ጥላሁን ገሠሠእንጀራገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችቅዱስ ጴጥሮስአኩሪ አተርዐቢይ አህመድዘጠኙ ቅዱሳንጂፕሲዎችዓፄ ዘርአ ያዕቆብልብየስነቃል ተግባራትአሜሪካዎችሻይየሰው ልጅአገውአፕል ኮርፖሬሽንየቅርጫት ኳስጥቅምት 13ስልክብጉርየባሕል ጥናትሀጫሉሁንዴሳፔትሮሊየምብጉንጅዛፍጸጋዬ ገብረ መድህንኣቦ ሸማኔአልበርት አይንስታይንተረት ሀየወላይታ ዞንግብፅፕላቲነምሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚትኤቲኤምእንስላልአዳም ረታአማርኛንዋይ ደበበሮማይስጥመኪናተረትና ምሳሌ፡ ዳንኤል አበራአማራ ክልልቀስተ ደመናኦሞ ወንዝዋናው ገጽሸዋካዛክስታንግራኝ አህመድየኢትዮጵያ ወረዳዎችመካከለኛ ዘመንመንግስቱ ኃይለ ማርያምስሜን አሜሪካየአፍሪካ ኅብረትሰዋስውኦርቶዶክስየንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥቬት ናምፍቅር እስከ መቃብርድሬዳዋሥነ ጥበብፋርስኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንድመትሆንግ ኮንግብሔርሰጎንመሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ🡆 More