ጳውሎስ: የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ

ሳውል በብሉይ የወጣለት ዕብራዊ ስሙ ሲሆን ፣ ጳውሎስ በሐዲስ የወጣለት ነው ትርጉሙም ብርሃን ማለት ነው ። በተርሴስ (ዛሬ በቱርክ ውስጥ) ከሚቀመጥ ከአንድ ሸማኔ ተወልዶ ካደገ በኋላ በኢየሩሳሌም ኦሪትን ከገማልኤል ተማረ። ስለኦሪትና ስለሙሴ ከፍ ያለ ቅናት፤ በዘመኑ ስለተፈጠረው የክርስትና ሃይማኖት የበዛ ጥላቻ ነበረው። ስለዚህ ክርስቲያኖችን ማባረር፤ ማሰር፤ ማጉላላት ሥራዬ ብሎ ይዞት ነበር።

ቅዱስ ጳውሎስ
መልክተኛው
ጳውሎስ: የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ
የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ
ስም መጀመሪያ ሳውል በኋላ ጳውሎስ
የተወለደው ቦታ ተርሴስ በሮሜ መንግሥት
የተወለደበት ዘመን በ፩ኛው ክፍለዘመን ፭ኛው ዓመት
የሚታወቀው በመልክቱ፣ ከይሁድነት ወደ ክርስቲያንነት በመቀየሩ ፣ በሰማዕትነቱ
ያረፈበት ፩ኛው ክፍለ ዘመን ፷፬፣፷፭፣ ፷፯ ዓ.ም. በሰይፍ ተሰይፎ
ሥራው ፀሐፊ ፣ ሰባኪ ፣ የክርስትና ሃይማኖት ፈላስፋ
የሚከበረው በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ
ንግሥ ሐምሌ ፭

ለዚሁ ጉዳይ ወደ ደማስቆ ሲሄድ እከተማይቱ ሊደርስ ሲል የሚያንፀባርቅ ብርሃን መታውና ወደቀ።

ጳውሎስ: የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ
ጳውሎስ በደማስቆ መንገድ

በመሬት ላይ እንደተኛ በሰማይ ካለው ከኢየሱስ ጋራ፤ አሳብ ለአሳብ እንደዚህ ሲል ተለዋወጠ።

ኢየሱስ፦ ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ ? ሳውል፦ አንተ ማነህ አቤቱ ? ኢየሱስ፦ እኔ ኢየሱስ ነኝ አንተ የምታሳድደኝ ። በተሳለ ብረት ላይ ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል ። ሳውል፦ ምን እንዳደርግ፤ ትፈቅዳለህ ? ኢየሱስ፦ ወደ ደማስቆ ከተማ ግባ፤ ልታደርገው የሚገባህን ሐናንያ ይነግርሃል ።

የሐዋ፡ሥራ፡ም፡ ፱ ፣ ቁ፡ ፬-፮

በዚህ ዓይነት ጳውሎስ ክርስትናን የተቀበለው ከክርስቶስ ነው ማለት ይቻላል። ዝርዝር ነገር ከሐናንያ ማጥናቱ እርግጥ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፍጹም ክርስቲያን፤ ትጉህ ሐዋርያ ሆነ። ያለ ዕረፍት የግሪኮችና የሮማውያን አማልክት እነዘውስ እነአርጤሚስ የአሶራውያንና የሲዶናውያን አማልክት እነአስታርት እነበዓል የገነኑባቸውን ከተሞች ያለዕረፍት እየዞረ የነዚያን ከንቱነት፤ የክርስቶስን አዳኝነት በቃልም፤ በጽሕፈትም መሰከረ። ለአባቶቹ ለዕብራውያንም በብሉይ ሐዲስ መተካቱን ለመንገር አልፈራም። ስለክርስቶስና ስለወንጌል በኢየሩሳሌም ተገረፈ፤ በቂሣርያ ታሠረ፤ በሮማ በሰይፍ አንገቱን ተቆርጦ ሞተ።

ነገር ግን በደረሰባቸው ከተሞች ሁሉ ክርስቶስን ሳያሳምን ቤተ ክርስቲያን ሳይመሠርት አያልፍም ነበር። ፲፬ መልዕክቶችንሲጽፍ፤ ከኢየሩሳሌም ግሪክ፤ ከግሪክ ሮማ፤ እየተመላለሰ የሐዋርያነት ሥራውን ሲያከናውን ራሱ ድንኳን እየሰፋ የራሱን መሮሪያ ራሱ ይችል ነበር እንጂ ከሰው ድካም የመነጨ ወይንና ምግብ በርሱ፤ ጉሮሮ አላለፉም ማለት ነው። ደንበኛ ሐዋርያነቱን ከሚያስረዱት ከብዙ ሥራዎቹ ውስጥ አንደኛው ይህ ነው።

:

Tags:

ኢየሩሳሌምኦሪት

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ሀዲያጥቅምት 13የልብ ሰንኮፍግዕዝጆርዳኖ ብሩኖሺስቶሶሚሲስየሐዋርያት ሥራ ፰ቅጽልየኣማርኛ ፊደልሙዚቃጋሊልዮኩሽ (የካም ልጅ)ኢያሱ ፭ኛብርጅታውንአንድምታእንጀራየኖህ መርከብክራርጥር ፲፰ፈሊጣዊ አነጋገርማሪቱ ለገሰየባሕል ጥናትዶሮ ወጥጣይቱ ብጡልዋናው ገጽቀጤ ነክቀዳማዊ ዓፄ ዮሐንስቀለምድልጫተረትና ምሳሌ፡ ዳንኤል አበራመዝገበ ዕውቀትራስ ጎበና ዳጨ ከ1882-188915 Augustክርስቶስ ሠምራአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነትተረት ሀጸጋዬ ገብረ መድህንአፕል ኮርፖሬሽንብሔርአንጎልግሥላአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስትንቢተ ዳንኤልፍቅርጫትዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግአሸንዳንቃተ ህሊናስቅለት (የማይክል አንጄሎ ቅርጽ)አውሮፓኦሞ ወንዝጴንጤጅቡቲ (ከተማ)በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትአበባህግ አስፈጻሚየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎችየዔድን ገነትአብዲሳ አጋቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያፀጋዬ እሸቱአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስምሥራቅ አፍሪካመዝገበ፡ቃላት፡በአምኅርኛ።ቶማስ ኤዲሶንየባቢሎን ግንብየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትየኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራዱባይ🡆 More