የወባ ትንኝ ወይንም ቢንቢ የዝንብ አይነት እንስሳ ናት። የትንኝ ሴቶች ተዋህስያን ስለሆኑ በደመ ሙቅ እንስሳት ላይ አርፈው፣ የእንስሳውን ቆዳ በሹል አፋቸው ከበሱ በኋላ፣ ምራቃቸውን ይረጩበታል። ይህን እሚያደርጉት የበሱት እንስሳ ደም እንዳይረጋ ነው። በእዚህ ሁኔታ ነገሮችን ካመቻቹ በኋላ፣ የአረፉበትን እንስሳ ደም ይመገባሉ ማለት ነው።
?የወባ ትንኝ | ||||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
የቢጫ ወባ ቢንቢ ሰውን ስትነክስ | ||||||||||||||||
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||||
|
በሽታ የሚያጋቡት፣ ቆዳ ሲበሱ ወይንም ደም ሲመጡ ሳይሆን፣ ምራቃቸውን ሲረጩ ነው። ለእዚህ ምክንያቱ በምራቃቸው ውስጥ አደገኛ ተውሳኮች ጎጆአቸውን ቀልሰው ስለሚኖሩ ነው ። በመገቡበት ቦታ ላይ እከክ የተነሣበት ምክንያት ምራቃቸው ቆዳውን ስለሚያሳውከው ነው።
ወንዶች ትንኞች የአበባ ጣዝማ ነው ምግባቸው። ሴቶቹም እንዲሁ የአበባ ጣዝማ ይመገባሉ፣ ሆኖም እንቁላል ሊጥሉ ሲሉ ብዙ ፕሮቲን ስለሚያስፈልጋቸው፣ የግዴታ ደም መምጠጥ አለባቸው። አለበለዚያ እንቁላል መጣል አይችሉም።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article የወባ ትንኝ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.