ኩክ ደሴቶች

ኩክ ደሴቶች Cook Islands በፓሲፊክ ውቅያኖስ የሚገኝ የኒው ዚላንድ ራስ-ገዥ ደሴቶች አገር ነው።

ኩክ ደሴቶች
Kūki 'Āirani
Cook Islands

የኩክ ደሴቶች ሰንደቅ ዓላማ የኩክ ደሴቶች አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Te Atua Mou E
የኩክ ደሴቶችመገኛ
የኩክ ደሴቶችመገኛ
ዋና ከተማ ኣቫሩኣ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ
ኩክ ደሴቶች ማዖሪኛ
መንግሥት

ንግሥት

ጠቅላይ ሚኒስትር
ህገ መንግስታዊ ንጉሳዊ አገዛዝ (ኒው ዚላንድ ግዛት)
ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ
ሄንሪ ፐና
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
240
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2011 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
21,000
14,974
ገንዘብ የኒው ዚላንድ ዶላር
ኩክ ደሴቶች ዶላር
ሰዓት ክልል UTC –10
የስልክ መግቢያ +682
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .ck

ደሴቶቹ መጀመርያ በእስፓንያ መርከበኞች በ1587 ዓም ተዘገቡ። የክርስትና ሰባኪዎች ከ1813 ዓም ጀምሮ ደርሰው የኗሪዎቹ ብዛት የክርስትና ምዕመናን ሆነዋል። በ1880 ዓም የፈረንሳይ ቅኝ አገር እንዳይሆኑ ፈርተው በራሳቸው ልመና በዩናይትድ ኪንግደም ጥብቅና ሥር ገቡ፤ በ1893 ዓም ጥብቅናው ወደ ኒው ዚላንድ ተዛውሮ እስካሁን ድረስ ከኒው ዚላንድ ጋር ተባባሪነት አላቸው። ሕዝቡ ግን ምንጊዜም በተግባር ራስ ገዥ ሆነዋል።

ይፋዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ እና የኩክ ደሴቶች ማዖሪኛ ናቸው፤ ፑካፑካኛ ደግሞ ይነገራል።

ትንሽ ኮኮነት፣ ፓፓያሎሚቡና፣ ወዘተ. ለአለም ገበያ ይመረታሉ። በባህላዊ ሥነ ጥበብ፣ የእንጨት እጅ ሥራዎች፣ የሽመና ዕቃዎች፣ የሽመና ባርኔጣ፣ ትርዒት የሚያሳይ ድሪቶ፣ ወዘተ. ይሠራሉ። ራግቢ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ጨዋታ ነው። ባህላዊ ጭፈራዎች አሉ።

በኩክ ደሴቶች አበሳሰል ስምንት-እግር፣ ዛጎል ለበስ፣ የአሳማ ግልገል፣ የፖሊኔዥያ አሮውሩት፣ ጎደሬ ይበላሉ። ለቅመሞች ዝንጅብል፣ ሎሚ፣ በሶብላነጭ ሽንኩርት፣ ኮኮነት ይጨመራሉ። በምግብ አሠራሮቹ መካከል፦

  • ሩካው - የገደሬ ቅጠል በኮኮነት ወጥና ሽንኩርት
  • ኢካ ማታ - ጥሬ አሣ በሎሚ ተዘፍዝፎ በኮኮነት ቅባት
  • ፖኬ - በሙዝና በኮኮነት ወተት ወይም በፓፓያ የሚሠራ ጣፋጭ

አሉ። የአምበሾክ፣ የብርቱካንና የማንጎ ጭማቂዎች ይጠጣሉ፣ እንዲሁም የኮኮነት ውሃ፣ ቢራቡና የሚወደዱ መጠጦች ናቸው።

Tags:

ኒው ዚላንድፓሲፊክ ውቅያኖስ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ጌዴኦጫማ (የርዝመት አሀድ)ተራራፈረንሣይህግ ተርጓሚአውስትራልያመስተፃምርዚምባብዌአንድምታየሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል (ኢትዮጵያ)ሥርአተ ምደባቃል (የቋንቋ አካል)ህዋስደብረ ዳሞአዋሳ ከተማ የእግር ኳስ ክለብክራርጎንደር ከተማጋሞየመስቀል ጦርነቶችተመስገን ተካራስወሲባዊ ግንኙነትደናሊ ተራራካረንታንማይጨውየትነበርሽ ንጉሴአዊ ብሄረሰብ ዞንአልበርት አይንስታይንባሕር-ዳርእቴጌ ምንትዋብስም (ሰዋስው)ቋንቋ አይነትአፈ፡ታሪክየዓለም መሞቅሻይ ቅጠልሊዮኔል ሜሲእንቆቅልሽሶፍ-ዑመርትምህርተ፡ጤናአለማየሁ እሸቴየዋና ከተማዎች ዝርዝርየሂንዱ ሃይማኖትቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)ክርስትናፋሲል ግቢምሥራቅ አፍሪካማሲንቆቦሌ ክፍለ ከተማሰዋስውሰለሞንፈተና፤ የዕንባ ጉዞዎች እና ሌሎች ግጥሞችየአድዋ ጦርነትሞቄ ወቅትየፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንውዝዋዜየርሻ ተግባርመርየም የእየሱስ (አ.ሰ) እናትየማርያም ቅዳሴየማርያም ቅዳሴ ገፅ ፱አሸናፊ ከበደተረትና ምሳሌዓረብኛናምሩድበእንግሊዝ የሚገኙ የእግር ኳስ ሜዳዎች ዝርዝርመስቀልሰንደቅ ዓላማአቡጊዳተውሳከ ግሥስዕልገጠርሶማልኛአልሞት ባይ ተጋዳይንግድኢትዮጲያጅብ ከማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላልባቲ ቅኝት🡆 More