አር ኤን ኤ ( RNA ) እንደ ዲ ኤን ኤ ( DNA ) ከኒክሉኢክ አሲድ ( nucleic acid ) የተሠራ ነው። እንደ ዲ ኤን ኤ አራት ቤዝ (base) አለው። እነሱም አዴናዪን ( A, adenine) ፤ ዩራሲል ( U, uracil ) ( ዲ ኤን ኤ ግን በዩራሲል ፋንታ ታያሚን ( T, thymine ) ነው ያለው) ጓኒን ( G, guanine ) እና ሳይቶሲን ( C, Cytosine )። ኑክሌይክ አሲዶች ደግሞ ሶስት መሰረታዊ አካላቶች አላቸው። ቤዝ፡ ሱካሩ ( sugar group ) እና ፎስፌት ግሩፑ ( the phosphate group ) ናቸው። አር ኤን ኤን ከዲ ኤን ኤ የሚለየዉ ሌላው ነገር የአር ኤን ኤ ስኳር ሁለተኛ ካርቦን ሀይድሮክሲል ( hydroxyl group (-OH )) ሲኖረው ዲ ኤን ኤ ግን ያለው ኤች ( H ) ብቻ ነው። ይህም አር ኤን ኤን በጣም ተለካካፊ ( reactive ) አድርጎታል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አር ኤን ኤ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.