ባሽኪርኛ (башҡорт теле /ባሽቆርት ትለ/) በባሽኮርቶስታንና በጎረቤት ክፍላገሮች በሩስያ ውስጥ በ1.2 ሚሊዮን ያሕል ተናጋሪዎች የሚነገር የቱርኪክ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው።
በባሽኮርቶስታን ውስጥ እስከ 914 ዓም በኦርኾን ሩን ጽሕፈት፤ ከ914 እስከ 1922 ዓም ድረስ በአረብኛ ጽሕፈት (በቱርክኛ አልፋቤት) ይጻፍ ነበር፤ ከ1922 እስከ 1931 ዓም ድረስ በላቲን ጽሕፈት (የአንድ አይነት ቱርኪክ አልፋቤት) ተጻፈ፣ ከ1931 ዓም እስካሁን በቂርሎስ ጽሕፈት (የባሽኪርኛ አልፋቤት) ተጽፏል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ባሽኪርኛ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.