ቅርንፉድ (Syzygium aromaticum) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ዛፍ ተክል ነው።
ተክሉ ሁሌ ለም ዛፍ ነው፣ እስከ 8-12 ሜትር ድረስ ይቆማል፣ ታላላቅ ቅጠሎችና በጫፉ ላይ ክፍት ቀይ ኅብረ-አበቦች አሉት። አበቦቹ አረንጓዴ ሆነው ሲጀምሩ፣ በምርት ጊዜ ክፍት ቀይ ይሆናሉ። የአበባው አቃፊዎች ለቅመም የሚመረቱ ናቸው።
የቅርንፉድ ዛፍ መጀመርያ መናኸሪያ እስከ 1760 ዓም ድረስ የማሉኩ ደሴቶች ኢንዶኔዥያ ብቻ ነበር። ሆኖም ከነዚህ ደሴቶች የቅርንፉድ ንግድ እስከ ሶርያ በ1730 ዓክልበ. እንደ ደረሰ በሥነ ቅርስ ታውቋል። በ1760 ዓም ግድም አንድ የፈረንሳይ ዜጋ ፒዬር ፗቭር የዛፉን ቡቃያ ሰርቆ በዛንዚባር እንዳስተከለው ይባላል፤ ይህም የደሴቶቹን ምኖፖል አስጨረሰው። አሁንም በተለይ እንደ ሰብለ ገበያ በባንግላዴሽ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሕንድ፣ ማዳጋስካር፣ ፓኪስታን፣ ስሪ ላንካ፣ ታንዛኒያ ይታረሳል።
ለሳል እና ጉንፋን በሽታዎች፡፡
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ቅርንፉድ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.