ሳተርን፡ (ምልክት፦) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት 6ኛ ( ስድስተኛ ) ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ መሬት፣ ማርስ እና ጁፒተር የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።
ይህ ፕላኔት በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የሁለተኛነትን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የ ጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። በ ረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፕላኔቶች ጁፒተር፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ራሱ ሳተርን ናቸው። በዚህም የተነሳ ጆቪያን ወይም ጁፒተርን መሳይ እየተባለ ይጠራል። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን ከተባለ ጋዝ እና በ ጥቂት መጠን ሂሊየም ከተባለ ንጥረነገር የተሰራ ነው።
ፕላኔቱ በተለይም ዙሪያውን በሚገኙ በቀለበቶቹ ይታወቃል። እነዚህ ቀለበቶች ከሳተርን ወገብ ከ6630 ኪ.ሜ. እስከ 120700 ኪ.ሜ. ርቀት ድረስ ይገኛሉ። በአማካይ እያንዳንዳቸው እስከ 20 ሜ. ድረስ ወፍረት ያላቸው ቀለበቶች ናቸው። የተሰሩት በአብዛሃኛው ከውሃ፣ ከበረዶ እና ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ማህፈድ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.