ቢል ክሊንተን

ዊልያም ጄፈርሰን «ቢል» ክሊንተን (እንግሊዘኛ፡ William Jefferson Bill Clinton) (የትውልድ ስም፦ ዊልያም ጄፈርስን ብላይዝ ፬ኛ፣ እንግሊዘኛ፡ William Jefferson Blythe IV) በነሐሴ 13 ቀን፣ 1938 ዓ.ም.

(= 1946 እ.ኤ.አ.) በሆፕ አርካንሳው የተወለዱ ሲሆን ከ1993 እስከ 2001 እ.ኤ.ኣ. ድረስ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸዉ በፊት አምስት ጊዜ የአርካንሳው ስቴት አስተዳዳሪ ነበሩ።

ቢል ክሊንተን
ቢል ክሊንተን

ቢል ክሊንተን ያደጉት በሆት ስፕሪንግስ፣ አርካንሳው ነው። የቢል ክሊንተን አባት ዊሊያም ጄፈርሰን ብላይዝ ጁኚየር፣ ቢል ክሊንተን ከመወለዱ ሶስት ወር በፊት በመኪና አደጋ ሞተዋል። የቢል ክሊንተን እናት ቨርጂኒያ ክሊንተን ኬሊ፣ በ1950 እ.ኤ.ኣ. ሮጀር ክሊንተን የሚባል ሰዉ አገባች። 14 ዓመቱ ሲሆን ቢል ክሊንተን የመጨረሻ ስሙን ወደ ክሊንተን ለወጠ። ክሊንተን በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ፥ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲኢንግላንድ፣ እና ዬል ዩኒቨርሲቲ፥ ኮነቲኬት ተምረዋል። በ1975 እ.ኤ.ኣ. ሂለሪ ሮድሃምን አገቡና በሊትል ሮክ፥ አርካንሳው መኖር ጀመሩ። ከዚያም በዩኒቨርሲቴ ኦፍ አርካንሳው የሕግ ፐሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ቢል ክሊንተን የአርካንሳው አስተዳዳሪ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በ1978 እ.ኤ.ኣ. ነው። በዛ ጊዜ ከአሜሪካ በዕድሜ ትንሹ አስተዳዳሪ ነበሩ። በ1980 እ.ኤ.ኣ. በፍራንክ ዲ ዋይት ከተሸነፉ በኋላ በ1982 እ.ኤ.ኣ. እንደገና ተመረጡ። ከዛ ጀምሮ እስከ 1992 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ለአራት ጊዜ አስተዳዳሪ ሆነው መርተዋል። በ1984 እ.ኤ.ኣ. የአስተዳዳሪ የስልጣን ዕድሜ ከ2 ዓመት ወደ 4 ዓመት አራዝመዋል። በ1992 እ.ኤ.ኣ. ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድርው አሸንፈዋል። በ1996 እንደገና ተወዳድረው አሸንፈዋል።

Tags:

19381946 እ.ኤ.አ.2001 እ.ኤ.ኣ.ነሐሴ 13አርካንሳውእንግሊዘኛየአሜሪካ ፕሬዝዳንት

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ቅንጭብዛጔ ሥርወ-መንግሥትጂዎሜትሪደቂቅ ዘአካላትሰለሞንሀጫሉሁንዴሳአቡነ ተክለ ሃይማኖትወይን ጠጅ (ቀለም)ከበደ ሚካኤልአኒሜዶናልድ ጆን ትራምፕኒንተንዶሜድትራኒያን ባሕርኒው ዮርክ ከተማአዋሽ ወንዝኦሞአዊሰርቢያራስ ዳሸንትንቢተ ዳንኤልአበራ ለማየአራዳ ቋንቋኦማንበርየባቢሎን ግንብየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግቶማስ ኤዲሶንሙሴእቴጌ ምንትዋብኢትኤልእየሱስ ክርስቶስመጽሐፈ ሲራክፊኒክስ፥ አሪዞናየኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነትኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንቀልዶችየኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራአትክልትግራኝ አህመድጥላሁን ገሠሠወንጌልኃይለማሪያም ደሳለኝአረቄስልጤአቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞየኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርፖሊስሰዋስውሮቦትጉሬዛኮሶ በሽታከፍታ (ቶፖግራፊ)ዝግመተ ለውጥግስሀብቷ ቀናየተባበሩት የሀገር ንጉሳዊ አገዛዝየተባበሩት የዓረብ ግዛቶችፍርድ ቤትወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጥጥባርነትፀደይንግድገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስሰንኮፉ አልወጣምመሀንዲስነትአስናቀች ወርቁኦክሲጅንኢንዶኔዥኛኮልካታስንዴአፄዋሺንግተን ዲሲፍቅርኢትዮጵያ🡆 More