ፕሩሲያ

ፕሩሲያ ከ1517 እስከ 1939 ዓም ድረስ የጀርመን ድሮ ክፍላገር ነበር።

ፕሩሲያ
ጥንታዊ ፕሩሲያ, 1200 ዓም ግድም
ፕሩሲያ
ፕሩሲያ ክፍላገር በግዛቱ ጫፍ - 1863-1910 ዓም

ከዚያ በፊት ጥንታዊ ፕሩሲያ ከ500 ዓም ያህል (በትውፊት ዘንድ) ጀምሮ እስከ 1216 ዓም ድረስ የተገኘ አረመኔ አገር ሆኖ ነበር። ቋንቋቸው ጥንታዊ ፕሩስኛ የባልቲክ ቋንቋዎች አባል ነበር። ከ1216 እስከ 1275 ዓም ያህል ድረስ፣ ቴውቶኒክ ሥርዓት የተባለው የመስቀለኞች ሥራዊት በጦርነት አሸነፋቸው፣ በክርስትና እንዲጠመቁ አስገደዳቸውና መሬታቸውን ያዙ። አገሩ እስከ 1517 ዓም ድረስ ቴውቶኒክ ግዛት ተባለ።

በ1517 ዓም በፕሮቴስታንት ተሃድሶ ንቅናቄ ዘመን፣ የቴውቶኒክ ግዛት አለቃ አልቤርት ዘፕሩሲያ የፕሮቴስታንት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ሆነና ከሮሜ ፓፓ ነጻነት ስለ አዋጀ፣ ግዛቱ ያንጊዜ የፕሩሲያ መስፍንነት ተባለ። ይህ በ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት» (ጀርመን) ውስጥ ክፍላገር ነበረ። ፕሮቴስታንቶች ከብዙ አገራት በስደት ወደ ፕሩሲያ ፈለሱ፤ የክፍላገሩም ዋና ቋንቋ ጀርመንኛ ነበር። ጥንታዊ ፕሩስኛ ቀስ በቀስ እየጠፋ ከ1700 ዓም በኋላ በሙሉ ተረሳ።

የፕሩሲያ ጀርመናዊ አለቆች ደግሞ ግዛታቸውን በጀርመን ውስጥ እጅግ ለማስፋፋት ስለ ቻሉ፣ ከ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት» ዘመን ቀጥሎ ጀርመን እንደ ዘመናዊ መንግሥት በማዋኸድ አንጋፋ ሚና ያለው ክፍላገር ሆነ።

ናዚ ጀርመን አዶልፍ ሂትለር በ1925 ዓም ወደ ሥላን ሲመጣ የክፍላገሩን ነጻ መንግሥት አጠፋ፤ ሆኖም በይፋ እንደ ክፍላገር እስከ 1939 ዓም ቆየ፤ በ1939 ዓም በጦር ጓደኞቹ አዋጅ ፕሩሲያ በይፋ ተጨረሰ።

Tags:

ጀርመን

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ስእላዊ መዝገበ ቃላትየተባበሩት መንግሥታት ድርጅትቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅመጠነ ዙሪያሥርዓተ ነጥቦችሳንክት ፔቴርቡርግየኮንትራክት ሕግሮማየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችየጋብቻ ሥነ-ስርዓትማሌዢያባቲ ቅኝትየዮሐንስ ወንጌልየቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎችመጽሐፈ ዕዝራ ካልዕስብሃት ገብረእግዚአብሔርየንቅያ ጸሎተ ሃይማኖትዘመነ መሳፍንትብጉንጅኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያንየማቴዎስ ወንጌልንግድአበበ ቢቂላደብረ ታቦር (ከተማ)የአስተሳሰብ ሕግጋትየትነበርሽ ንጉሴሚካኤልደቡብ ሱዳንኤፍራጥስ ወንዝሰንበትየቅርጫት ኳስየተባበሩት ግዛቶችጠላሞንቴቪዴዮ ዋንደረረስሀብቷ ቀናቀስተ ደመናከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርፊሊፒንስዝንዠሮአክሱም ጽዮንተራጋሚ ራሱን ደርጋሚየሮበርት ሙጋቤ ቀልዶችሥነ ዕውቀትብርጅታውን2ኛው ዓለማዊ ጦርነትአክሊሉ ለማ።ሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታኦሪት ዘፍጥረትስልጤአልበርት አይንስታይንቻይናአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስየኮርያ ጦርነትዕድል ጥናትቀይ ሽንኩርትሳዑዲ አረቢያየኣማርኛ ፊደልውዳሴ ማርያምግብፅአናናስመጽሐፍ ቅዱስረጅም ልቦለድመጋቢትልብዶሮ ወጥግመልተውሳከ ግሥሣራባሕር-ዳርነጭ ሽንኩርትመጽሐፈ ጦቢትግዕዝብርሃንገድሎ ማንሣት🡆 More