ጣልያንኛ የጣልያን ሃገር ብሄራዊ የመግባቢያ ቋንቋ ነው። በጣልያን ብቻ 60 ሚሊዮን ዋና ተናጋሪዎች ሲኖሩት በውጭ ሃገር 10 ሚሊዮን ተናጋሪዎች አሉት። በአጠቃላይ 70 ሚሊዮን ዋና ተናጋሪዎች እና ከ125 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንደ የውጭ ቋንቋቸው ይናገሩታል። ለምሳሌ በዋናነት ስዊትዘርላንድ ውስጥ ከሚነገሩ አራት ትልልቅ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ቋንቋው በግሪክ፣ ሊቢያ፣ ክሮሽያ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች በጣልያን ቅኝ ግዛት ውስጥ የነበሩ ሃገሮችም ውስጥ ቀላል የማይባሉ ተናጋሪዎች አሉት። በዋና ተናጋሪ ብዛት ከአለማችን 20ኛ ደረጃን ይይዛል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጣልያንኛ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.