ቤንች

የቤንች ብሔረሰብ ቋንቋ ‹‹ቤንችኛ›› ሲሆን ከምዕራብ ኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል። የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ አማርኛ፣ ካፊኖኖ እና ሸኮኛ ቋንቋዎችን ይናገራሉ።

ቋንቋ

ሕዝብ ቁጥር

መልክዓ ምድር

የቤንች ብሔረሰብ አባላት በዋናነነት በዞኑ በሰሜን ቤንች እና በደቡብ ቤንች፣በሸዋ ቤንች ወረዳዎች እንዲሁም በሸኮ እና ጉራፈርዳ ወረዳዎች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ከዞኑ ውጭም የብሔረሰቡ አባላት ኩታ ገጠም በሆኑት በከፋ ዞን በጨና እና ዳቻ ወረዳዎች፣ በሻካ ዞን በየኪ ወረዳ እንዲሁም በአዲስ አበባ ‹‹ጊሚራ›› ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ይገኛሉ፡፡ ብሔረሰቡ የሚገኝበት አቀማመጥ ሜዳማ፣ ተራራማ እና ሸለቋማ ሲሆን፤ ደጋማ፣ ቆላማ እና ወይና ደጋ የአየር ንብረት አለው፡፡ የብሔረሰቡ ዋነኛ መተዳደሪያ ጥምር ግብርና ነው፡፡ ከተክሎች፣ ከሥራሥር፣ ከጥራጥሬ፣ ከቅመማቅመም ከአገዳ እህል የሚገኙ ምርቶች ያመርታል፡፡ ቡና ዋና የገቢ ምንጭ ሲሆን፤ ቅመማቅመም፣ ቆዳ እና ሌጦ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ናቸው፡፡

ታሪክ

ቤንች ብሔረሰብ በቤንች ማጅ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ የብሔረሰቡ አሰያየም ‹‹ቤንችቲያት›› ከተባለው ጥንታዊ የብሔረሰቡ መሪ እንደተወለደ ይነገራል፡፡ ‹‹ታት›› የሚባለው ቃል ‹‹ጌታ›› ማለት ሲሆን ለብሔረሰቡና ለቋንቋው መጠሪያ ነው፡፡

በቤንች ብሔረሰብ በርካታ ጐሳዎች ቢገኙም ከምት፣ ቃም፣ ማንጃ(ባንድ) እና ማኖ(ፋቂ) ዋና ዋናዎቹ ናቸው በሐረሰቡ የራሱ የሆነ ባህላዊ አስተዳደር እና የዳኝነት ሥርዓት ያለው ሲሆን፤ ባህላዊ አስተዳደሩ የሥልጣን እርከን እና የሥራ ኃላፊነት የሚወሰነው በእርከኑ ባሉ ሽማግለዎችና በጎሳ መሪዎች ምርጫ ነው፡፡ ‹‹ከምት›› ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠው መሪ ነው፡፡ ማንኛውንም ፖለቲካዊ ማኀበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮችን በበላይነት ይመራል፡፡ የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮ ከእዚህ ጎሣ የሚሾም ሲሆን ‹‹ቤንችያት›› (ከምት) ባላባት ይባላል፡፡ የሚመረጠውም ‹‹ከባይከስ›› ጎሳ ነው፡፡ የሥልጣን ሽግግሩም የዘር ሀረግን የተከተከለ ሲሆን የመሪዎቹ ወይም የ‹‹ቲያቶት›› ሥልጣን የሚተላለፈው ከ‹‹ቲያቶች›› የመጠሪያ ሚስት ለተወለደ የበኩር ልጅ ነው፡፡ መሪው ልጅ ሳይተካ ከሞተ ወንድሙ ሥልጣኑን ይወርሳል፡፡ ለ‹‹ቲያትነት›› የሚመረጠው ልጅ ወይም ወንድም በቂ ችሎታ ያለው እና ከሌለ ወገን ያልተከቀላቀለ ቤንች መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ብሔረሰቡ ግጭቶችን የሚፈታበት የተለያዩ መንገዶች ያሉት ሲሆን፤ ግድያ ከተፈፀመ ወንጀሉ አፈፃፀም ከተጣራ በኋላ በሁለቱ ደመኞች ድንበር ላይ በሬ ታርዶ በደም ይታረቃሉ፡፡ ልጃገረድም ከገዳይ ወገን በካሳ ትሰጣለች፡፡ በብሔረሰቡ መዋሸት፣መሥረቅ፣ዝሙት መፈጸም አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡ ይህን ተግባር የፈጸመ ለቃልቻ ወይፈን ወይም ጊደር ይሰጣል፡፡ ከ1ዐ እስከ 3ዐ ጅራፍም ይገረፋል፤ በእግረሙቅ ይታሠራል፤ ለተወሰኑ ወራትም ለባላባቱ እንዲያደርስ ይደረጋል፡፡

በቤንች ብሔረሰብ የጋብቻ ሥርዓት በቤተሰብ ስምምነት፣በጠለፋ፣በማስኮብለል እና በውርስ ይፈጸማል፡፡ በብሔረሰቡ ሴት ልጅ 15 ዓመት ወንድ ልጅ ደግሞ 2ዐ ዓመት ሲሞላው የጋብቻ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ባላባቱ እስከ 4ዐ ሚስቶችን ማግባት ሲችል አንጋፋዋ ሚስት ‹‹ጌን›› ትባላለች፡፡

በብሔረሰቡ ከወቅቶች ጋር ተያይዞ ምርት እንዲሰጥ፣ በሽታ እንዲጠፋ፣ ሰላም እንዲሰፍን በዓመት 3 ጊዜ የሚከበሩ በዓላት አሉ፡፡ በዓላቶቹ በቃልቻዎችና በባለአባቱ የሚመሩ ሲሆን፤ቦርዴ ተጠምቆ ልዩ ልዩ መልክ ያላቸው ዶሮዎች እና ከ5ዐ እስከ 6ዐ ያህል ከብቶች ታርደው እንዲከበር ይደረጋል፡፡ ቤንቾች በዓላትን፣ የዘመንና የወቅት አቆጣጠርን የጨረቃ መውጣትና መግባትን ተከትለው ከአዝመራ ወቅቶች ጋር በማዛመደ ያከብራል፡፡

ብሔረሰቡ ባህላዊ ቤቶችን ከእንጨት፣ ከጭቃ እና ከሣር የሚሠራ ሲሆን፤ጣራቸው በጭቃ የተሸፈነው ነው፡፡ የጎሣ መሪዎቹ ቤቶች ከፍታ ያላቸውና ሰፊ ናቸው፡፡ በብሔረሰቡ ከበቆሎ ወይም ከጤፍ የተሠራ ዳቦ፣ እንሰት(አምቾ)፣ ጎደሬ፣ እና የጎደሬ ገንፎ ይበላል፡፡ የቆጮ ቅቅል፣በቆሎ ተቆልቶ ከተፈጨ በኋላ የተዘጋጀ ጎመን ተጨምሮ በገንፎ መልክ ተዘጋጅቶ ይበላል፡፡ በብሔረሰቡ ወንዶች ሆዳቸውን በቀኝ እና በግራ ክንዳቸው አማካኝነት ቀጠን ያለ ‹‹ጋሱ›› የተባለ መስመር በመሥራት ያስውቡታል፡፡ ወንዶቹም ሆነ ሴቶቹ ለጉትቻ ጆሮአቸውን ይበሳሉ፡፡ አዛውንቶቹ ቁምጣ ሱሪ አንዳንዴም በላሌ፣ኩታ፣ ሹራብና ረጃጅም ልብሶችን ይለብሳሉ፡፡ ጦር መያዝም ልምዳቸው ነው፡፡

በብሔረሰቡ የለቅሶና የሀዘን ሥርዓት መሠረት ባለውቃቢ(ቃልቻ) ሲሞት አስከሬኑ ከመቀበሩ በፊት ውቃቢው በልጁ ወይም በዘመዱ ላይ እንዲወርድ በሚል በዋናው ቃልቻ ይለመናል፡፡ ባለአባቱ ወይም መሪ ሲሞት የሟች የቤተሰብ ቀብርን ከፈጸመ ከወር በኋላ መልዕክቱ ይተላለፋል፡፡ እየተደገሰ ሁለት ወር ይለቀሳል፡፡ ወጣት ሲሞት ለሳምንት ተለቅሶ በሦስተኛው ወሩ ልብሶቹ መቃብሩ ላይ ይጣላሉ፡፡ ንብረቱም እንዲወድም ይደረጋል፡፡

ታዋቂ ሰዎች

ቤንች የኢትዮጵያ ብሔር ነው።

https://www.duhoctrungquoc.vn/wiki/am/ቤንች

Tags:

ቤንች ቋንቋቤንች ሕዝብ ቁጥርቤንች መልክዓ ምድርቤንች ታሪክቤንች ታዋቂ ሰዎችቤንችሸኮኛቤንችኛአማርኛ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ገናከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርሂሩት በቀለሆሣዕና በዓልፍቅርህሊናሊቢያይስማዕከ ወርቁየቅርጫት ኳስሕገ ሙሴኦሪት ዘኊልቊበርሊንወላይታመተሬየመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነትጋምቤላ (ከተማ)ቆለጥአቡነ ተክለ ሃይማኖትየኩላሊት ጠጠርአልባኒያዛጔ ሥርወ-መንግሥትአበበ ቢቂላጃቫፕሮቴስታንትየሕገ መንግሥት ታሪክቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለችፋሲካእንጀራቤንችመልከ ጼዴቅወንጪየአገሮች ገንዘብ ምንዛሪአቡጊዳኢንግላንድከፋወጋየሁ ደግነቱትግራይ ክልልተውላጠ ስምንግሥት ዘውዲቱሣህለ ሥላሴዩክሬንእንደምን አደራችሁንግድቦሌ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያቻቺ ታደሰሐመልማል አባተስም (ሰዋስው)በዓሉ ግርማየስልክ መግቢያፍቅር እስከ መቃብርሊያ ከበደእምስታምራት ደስታሀይሉ ዲሣሣየዮሐንስ ራዕይአሜሪካየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማአቡነ ጴጥሮስአቡነ ቴዎፍሎስጃፓንየትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴርኢንጅነር ቅጣው እጅጉየሲዳማ ባሕላዊ ሐይማኖትወሲባዊ ግንኙነትዓፄ ቴዎድሮስመኪናይስሐቅዮሐንስ ፬ኛNon-governmental organizationየራይት ወንድማማችጋብቻየዮሐንስ ወንጌልዳግማዊ አባ ጅፋርየከለዳውያን ዑርየኢትዮጵያ ካርታ 1690የኢትዮጵያ ሕግጋምቤላ ሕዝቦች ክልል🡆 More