የግሪክ አልፋቤት ቢያንስ ከ800 ዓክልበ.
ጀምሮ ግሪክኛን ለመጻፍ ተጠቅሟል። የተደረጀው ከፊንቄ ጽሕፈት ሲሆን የአንዳንዱ ፊደል ጥቅም ከተነባቢ ወደ አናባቢ በመለወጡ የግሪክ አልፋቤት መጀመርያው የአናባቢ ፊደል ጥቅም ያገኘው ጽሕፈት ሆነ። የግሪክ አልፋቤትም በተለይ ለላቲን አልፋቤትና ለቂርሎስ አልፋቤት፣ ለሌሎችም፣ ወላጅ ሆነላቸው። ከግሪክኛ በላይ የግሪኩ ጽሕፈት ለአንዳንድ ሌሎች ልሳናት ተለምዷል።
በዘመናዊ ግሪክ ቋንቋ በጥቅም ላይ የሚውሉት ፊደላት እነዚህ ናቸው።
|
|
የግሪክ አልፋቤት ከ800 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ቢታወቅም ከዚያ በፊት ከ1450 እስከ 1100 ዓክልበ. ድረስ ባለው ጊዜ በሚውኬናይ ጽሕፈት የተጻፉ ቅድመ-ግሪክኛ መዝገቦች ከሥነ ቅርስ ተገኝተዋል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article የግሪክ አልፋቤት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.